>

የዛሬይቱ ኢትዮጵያችን ለአማራና ለትግሬ ያላት ክብር  (ዘመድኩን በቀለ) 

ኦሮሞስ በቄሮ ትግል ተከበረ አማራውስ አዳኙ ማን ይሆን?!?
የዛሬይቱ ኢትዮጵያችን 
 ለዐማራና ለትግሬ ያላት ክብር  
               ዘመድኩን በቀለ
~ በአምካኝ መርፌ ፣ በተበላሸ ኪኒን ፣ በህገወጥ እስር፣ በአስጨናቂ ገፊ ምክንያት የሚፈጠር ስደት ፣ በተበላሸ ማዳበሪያ በሚፈጠር ረሃብ ፣ በቀላሉ በሚፈለፈልና በሚራባ ወባ ፣ በተቀናጀ ተንኮል በኤድስ በመበከል፣ በጤናና በትምህርት ጥራት ፣ በጫትና በአልኮል ሱስ ፣ በወረርሽኝ ፣ በሽፍታ ስም በሚደረግ ግድያ ፣ በሙስና ስም ሀብቱን በመውረስ ፣ ዘብጥያ በማበስበስ ፣ በህግ ከላላ ስር ያሉትንም ፣ ብልት በማኮላሸትና ዘሩን ለማጥፋት በእቅድ ተሠርቷል። ባለፉት 27 ዓመታት ብቻ በሚሊየን የሚቆጠር ዐማራ ከኢትዮጵያ ምድር ጠፍቷል። ፓርላማው ራሱ ይኼንኑ አረጋግጧል ።
ይኼ የሆነው ደግሞ በትግሬው ወኪል ነኝ በዩ ህውሓትና በአማራው ላይ የተመረገው የአርማታ ምርጊት በህውሓት ኮንደሞሙ በአማርኛ ተናጋሪ ኤርትራውያንና በትግራይ ልጆች በሚመራው ብአዴን የተባለ ባንዳ ፊት አውራሪነት ነው። አሁን ብአዴን ጥርሱ እየተነቃነቀ መሆኑ እያየን እየሰማንም ነው ። ነገር ግን ብአዴን መጠበቁ አያዋጣም። ብአዴን እንደ ኦህዴድ ኦነግ ለመሆን ብዙ ዘመን ፣ ብዙ ማገዶም ይፈጃል ።
~ ተመልከቱ ህውሓት ከዐማራው ላይ ከጎጃም ምድር ቆርሳ ጠፍጥፋ በፈጠረችው የቤንሻንጉል ክልል ላይ የትግራይ ልጆችን አምጥታ አስፍራለች። እናም የቤንሻንጉል ክልል ተብዬው የሚመራው ደግሞ በአማካሪነት በተቀመጡ የህውሓት ጀነራሎች ነው። የሚገርመው የክልሉ መንግሥት የዐማራውን ነገድ እስኪደክመው ይጨፈጭፍ፣ ይጨፈጭፍ ፣ ይጨፈጭፍና ሲበቃው መግለጫ ያወጣል። ቀደም ሲል መመሪያ ሰጪው አቶ መለስ ነበር በፓርላማ የዐማራውን መጨፍጨፍ ” ከደን ውድመት ” ጋር አያይዞ የሚያለግጠው ። አሁን ግን ለጭፍጨፋው ማስተባበያ እንኳን አላስፈለጋቸውም። በዓዋጅ ፣ በማስታወቂያ ፣ በደብዳቤ ነው በሃላል ዐማራውን የሚያፈናቅሉት ፣ የሚገድሉት ፣ የሚጨፈጭፉት።
በነገራችን ላይ ዐማራው ለቤኒሻንጉሎቹ አንሶ አይደለም። በቤኒሻንጉሎቹ ካባ ስር የህውሓት የአግአዚ ጦር ከኋላ ጃስ እያለ እስከአፍንጫው በታጠቀው ጦር ስለሚታገዝ እንጂ። ለማንኛውም በዐማሮቹ ላይ የሚፈጸመው ዘግናኝ ግፍ ነግ በእኔ ነው ያሉ #የትግራይ ልጆችም ወደመጡበት ወደ ትግራይ መመለስ ይፈልጋሉ ፣ የክልሉ መንግሥት እናንተን የሚነካ የለም አርፋችሁ ተቀመጡ ቡሎ ቢለምን ቢያስለምናቸው #አቡነ_አረጋዊን፣ #አደይ_ማርያም_ጽዮንን እምቢኝ አሻፈረኝም አሉ ። እናም ትግሬዎቹ መሔዳቸው ካልቀረማ እንደ ዐማራው ባዶ እጃቸውን መሔድ የለባቸውም ተባለና ከሥር ያስቀመጥኩላችሁ አሸኛኘት ተደረገላቸው። #የወርቅ_ዘር የሚለው የጠሚዶኮ ዐብይ አህመድና የሟቹ ጠሚ መለስ አማርኛ በዘፈቀደ የተነገረች አለመሆኗን ይታወቅ ።
አሁን ነገሮች እየተቀየሩ መጥተዋል። ሳይወዱ በግዳቸው እነ  #ETVም  እንኳ ሳይቀሩ የዐማራውን መፈናቀል ለመዘገብ ተገድዋል ። #መክት_ዐማራ !
~ ወዳጄ ስትደራጅ እንደ ትግሬዎቹ ሰሚ ታገኛለህ ፣ ስትፈናቀል የአውሮፕላን ትኬት ተቆርጦ ውሻና ድመትህ ሳይቀር ፣ ፖፖና ቁምሳጥንህ ጭምር በክብር መቐለ ይገባልሃል። ስትደራጅ እንደ ኦሮሞዎቹ ቄሮዎች የመንግሥትን እጅ ጠምዝዘህ ትደራደራለህ። ስትደራጅ ሁሉንም ጠላቶችህን ታሸንፋለህ። ስትደራጅ ትፈራለህ። ስትደራጅ ትከበራለህ ። መደራጀቱን ደግሞ ህገመንግሥቱም ይፈቅድልሃል። አከተመ።
~ አንተ ዘመዴ ግን የሃይማኖት መምህር ሆነህ እንዴት #ዐማራ ፣ #ዐማራ ትላለህ የምትሉኝን በጭባጫ ሰገጤ ሁላ አልሰማችሁም። እንኳን ለዐማራ ለአጥንቴ ፍላጭ ፣ ለሥጋዬ ክፋይ ፣ ለፍልስጤም ህጻናት ፣ ለበርማ ሙስሊሞች ፣ ለግብጽ ክርስቲያኖችስ እጮህ የለም እንዴ?  አንተስ በፓሪስ ለፈነዳ ቦንብ የፌስቡክ ፕሮፋይልህን ቀይረህ ለማታውቃት ፈረንሳይ ገመድ በጉሮሮዬ ካላጠለኩ ትል የለ እንዴ?  እና ምኑላይ ነው ለተበደለ መጮኽ ኢ ክርስቲያናዊ ተግባር የሚሆነው? አዳሜ ቁርጥህን እወቅ ። በቃ አከተመ ዐማራውም እንደ ሌሎቹ መደራጀት አለበት ።
~ በዐማራው ግብር ኢትዮጵያ ትልማ ዐማራው ይድማ ፣ ዘሩ ይጥፋ ማለት ኃጢአትም ፣ በደልም ፣ ወንጀልም ነው ።
~ አንተ ዐማራውም ነቅነቅ በል። አትተኛ ። ከምር ነግሬሃለሁ አትፍዘዝ ። ተረታ ተረቱን ማውራትህን ተውና ተሰባሰብ። በህጋዊ መንገድ ተደራጅ ፣ አትሽርኮርመም ፣ አትግደርደር ፣ የይልኙታ ካባህን አሽቀንጥረህ ወዲያ ጣል ። ፕሮፌሰር ዶክተር የሚልህን አትስማ ። አንተ ስትፈናቀል ፣ አንተ ስትገደል ፕሮፌሰሩ አይደርስልህም ።አከተመ በቃኝ በል። ይውጣላቸው ዐማራ ነኝ በል።
~ እኔ ዘመዴ ግን ከእውነት ጋር እንደተጋባሁ ፣ ከእውነት ጋር ሳልፋታ ወደ መቃብር እወርዳለሁ ። ባለኝ አቅም ሁሉ  ከተጠቁ ወገኖች ጎን መቆሜን ለአፍታም ታህል አላቋርጥም ። በዚህ መንገድ እንዳልፍ የረዳኸኝ አምላክ ተመስገንልኝ ። አሜን ።
~ ዐማራው በኢትዮጵያ ውስጥ እንደሰው እስኪቆጠር ድረስ፣ በደሉን ሰሚ እስኪያገኝ ድረስ ፣ ግድያ እስራቱ ፣ የዘር መጥፋቱ እስኪቆምለት ድረስ እጮኽለታለሁ ።
~ በዐማራው ላይ የሚደርሱ ዘግናኝ ግፎችን ለዓለም ህዝብ እንዲያሳይ ዓለም አቀፍ የዐማራ የቴሌቭዥንና የራድዮ ፕሮግራም የሚያስተላልፍበትን የቴሌቭዥንና የራድዮ ጣቢያ ከፍቶ ሥራ እንዲጀምር የበኩሌን ጥረት አደርጋለሁ። አስተባብራለሁ ፣ እቀሰቅሳለሁ ፣ ደሜን እሰጣለሁ ።
~ በአንድነት ሰበብ ዐማሮች ዘራቸው ከምድረገጽ እስኪጠፋ ድረስ እያዩ የደነዘዙትን ሁሉ አነቃለሁ ። እቀሰቅሳለሁ፣ ቅድሚያ ለማንነታቸው እንዲሰጡ እወተውታለሁ። በዚህ በኩል እየተሳካ ይመስላል። እስከ አሁን እኔን ጨምሮ ዐማራውን በግድ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ካላልክ ብለን ስንነዘንዘው የኖርን በሙሉ በዐማራው መደራጀት ስምም እየሆን መጥተናል ። ታዋቂው ብዕረኛ አቶ Edwardo Bayerno ፣ ዶር ደመቀ ገሠሠ የመሳሰሉ የፌስቡክ ጦማርያን በአንድነት ሥም ዘሩ ከምድረገጽ እንዲጠፋ ከተበየነበት ዐማራው ዘንድ በይፋ ተቀላቅለዋል። ወጣቱ ዐማራ ነኝ ማለቱን በይፋ ጀምሯል። ብራቮ ዐማራ።
~ መቼም አልጸድቅም እንጂ የምጸድቅም ከሆነ ይኼን ሥራ ሠርቼ ፣ ዐማራው ተደራጅቶ ፣ ልክ እንደቄሮ ጉልበት አግኝቶ ቀና ብሎሲሔድ ዐይቼ ብሞትም አይቆጨኝም ። ዐማራ ስል ዐማራ ነው ። #እስላም ዐማራ ፣ #ፕሮቴስታንት ዐማራ ፣ የፈለገው ይሁን #ዐማራ_ዐማራ ነው። አትለያዩ። አከተመ። አጼ ዮሐንስ ወሎ ላይ የረሸኑት እስላም ዐማራን ነው ። ጎጃም ላይ ያጸዱት ኦርቶዶክስ ዐማራን ነው። ዐማራ ዐማራ ነው ፣ እኔ እስላም ኦርቶዶክስ አላልኮም ፣ ዐማራ የሆንክ ተደራጅ ፣ ተነጋገር ፣ ወሎ፣ሸዋ፣ጎንደር፣ ጎጃም አትባባል ፣ ዐማራ ፣ ዐማራ ነው ።
ሰሞኑን በዐማራ ክልል ቴሌቭዥንና በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከመተከል በግፍ ተፈናቅለው ቤኒሻንጉል ጉምዝ ስለፈሰሱት ምስኪን ዐማሮች በግድ ተዘግቧል ። በግድ አልኩህ ። እደግመዋለሁ በግድ ። ይኽ ዘገባ የመጣው ዐማራው ፣ ዐማራ ፣ ዐማራ ብለህ በአንድነት በመጮኽኽ ነው። እናም ይኽን የመሰለ ዘገባ እያየህ አታለቃቅስ። ይልቅ ዘገባውን ለቁጭትህ ፣ ለመደራጀትህ ፣ ለመሰባሰብህ ፣ ለመረዳዳትህ ፣ ለክብርህ ፣ ለተዋረደው ማንነትህ በግብአትነት ተጠቀምበት። ለዐማራ ማንነት ምስረታ እንደ ማቀጣጠያ ቤንዚንም ተጠቀምበት። ነግሬሃለሁ ! ከምር ነግሬሃለሁ ተጠቀምበት ።
አንት ከርሳም ዐማራ ግን ፣ አንት ሆዳም ዐማራ ግን ፣ አንት ባንዳ ዐማራ ግን ፣ አንት የውስጥ አስጠቋሪ ዐማራ ግን ፣ አንት ገለልተኛ ነኝ ባይ ፈሪና ቦቁባቃ ዐማራ ግን ፣ አንት በአንድነት ሰበብ ወገንህን የምታስፈጅ ዐማራ ግን ራስህን ጠይቀው። ዐማራው ብቻ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ እንዲያልቅ ነው የምትፈልገው ?  ቢያንስ ይሔን ግፍ እንኳ አይተህ ሃሳብህን መርምረው። ባታስቆመውም እንኳ ቢያንስ እንዳይደራጅ እንቅፋት ፣ ሳንካም አትሁነው ። ከነ ተረቱስ መጀመሪያ መቀመጫዬን አለች ዝንጀሮ አይደል የሚባለው። እናም መጀመሪያ #ክብረ_ዐማራነትህን አስመልስ። የበዪ ተመልካች አትሁን ። መብትህን ተደራጅተህ አስከብር።
የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሳይወድ በግዱ የዐማራውን ከመተከል መፈናቀል ለመዘገብ ተገዷል። ገና ሲኤን ኤን ይዘግበዋል፣ ገና ቢቢሲ ይዘግበዋል ። እናም አንተ ባለቤቱ ያቀለልከውን ዐማራነት ባለዕዳ እንዲያከብርልህ ተቀምጠህ ጣራ ጣራውን ስታይ አትደር። ወዳጄ መጀመሪያ አንተው ዐማራው ዐማራነትህን አክብረህ ሌላው እንዲያከብርልህ አስደርገው። መታወቂያህ ላይ ዐማራ አትበልብኝ እያልክ ስትጋተት የከረምክ ሁሉ አሁን ሔደህ የቀበሌውን ሊቀመንበር መታወቂያዬ ላይ በትልቁ #ዐማራ በልልኝ በለው። ያን ጊዜ ማን እንደሚነስረው ታያለህ ። ቱ ምንአለ ዘመዴ በለኝ ሁሉም ዐማራ መታወቂያዬን ዐማራ በልልኝ ማለት ሲጀምር በአንድ ጀንበር አገዛዙ ብሔራዊ መታወቂያ ያላዘጋጀ እንደሆን ምን አለ በሉኝ። ስንትና ስንት ሰው አለ መሰላችሁ ለመኖር ሲል መታወቂያው ላይ ትግሬ ፣ ኦሮሞ ብሎ ዐማራነቱን የካደ ። እናም ክብረ ዐማራ ይመለስ።
 ከ35 ሚልየን ኦሮሞ 11 ሚልየኑ ዐማራ ነው። በአክሱም ፣ በመቐለ ፣ በሽሬና በዐድዋ የሚኖረው አብዛኛው ትግሬም ወይ በእናቱ ወይ በአባቱ ትግሬ ነው ። መለስ ዜናዊ አድዋ ይወለድ እንጂ ፣ አባ ጳውሎስም አድዋ ይወለዱ እንጂ በግማሽ የጎጃም ዐማሮች ናቸው። ከዐማራ ያልተጋባ ፣ ያልተዋለደ ፣ ያልተዛመደ የለም ። ጀዋር መሃመድ በእናቱ የሰሜን ሸዋ ዐማራ ነው። ሌላም መጥቀስ ይቻላል።
እናም የዐማራውን መደራጀት፣ ኦሮሞውም፣ ትግሬውም፣ ደቡቡም ፣ ሱማሌውም ሊደግፈው ይገባል ። ባይደግፉትም ግን እንደ ጭዳ ዶሮ አብሾአቸውና ዛራቸው በተነሳ ቁጥር እየመረጡ የሚያርዱህን ከእንግዲህ ወዲህ አትፍቀድላቸው ። 1 ዐማራ ሲሞት ፣ ያለ አግባብ ሲገደል ፣ ሲፈናቀልም ለምን ብለህ ጠይቅ ፣ ጎንደር ጎጃም ፣ ወሎ ሸዋ ማለትህንም አሁኑኑ አቁም ። አሁን ሁላችሁም …………….
Filed in: Amharic