>

የመድረኳ ልእልት እቴጌ አለም ጸሀይ ወዳጆ! (ክፍል 2፤ አለባቸው ደሳለኝ - ለንደን)

ተዋናይ፣ አዘጋጅ፣ ተውኔት ደራሲ፣ ገጣሚ፣ መሪና የጥበብ ሥራ ተቆርቋሪ

ክፍል 2

 በቅድሚያ ለሁሉም ወዳጆቼ መግለፅ የምፈልገው ቁም ነገር ቢኖር ባቀረብኳቸው ሁለት ተከታታ ዝግጅቶቼ ላይ ስለዚች  ታላቅ  የቲያትር ተዋናይ ደራሲና አዘጋጅ የምትመኙትን ያህል አግኝታችሁ ተደስታችዃል ብየ ባልገምትም የእያንዳችን እለታዊ አጋጣሚዎች
ከምንገኛቸው የትውስታ መደብሎቻችን ውስጥ ያለችውን ቆንጠር አድርጌ ማካፈሌ እንጅ አለም ፀሐይ ወዳጆ ፣ ያሳለፈችውን የህይወት ውጣ ውረድ በሷ በግል ብዕሯ ካላሰፈረችና ለታሪክ ካልተወችልን  በስተቀር  የኛ ድካም አባይ በጭልፋ ነው ::
ምክኒያቱም አለም ፀሐይ ወዳጆ እንደዚህ ናት ብሎ ለመመስከር የሷን በሳል አዕምሮ ስፋትና ጥልቀት መታደልን ይጠይቃል ::
አለምን ለማዎቅ ስለሷም ለመመስከር እንደሷ የሀሳብ ውቂያኖስ መሆን ይጠይቃል ::
አለምን ለማወቅ እንደሷ ደፋር ሐቀኛ መሆን ያስፈልጋል :: ከዚህ በተጨማሪ የበሰለ አስተዋይነትና ትዕግስትን መታደል ያስፈልጋል::
 2005 እ.ኤ.አ. የብላቴን ጌታ ሎሬት ፀጋዬ ገ/ መድህንን የህይወት  ታሪክ ለመጠየቅና  በፊልም   ቀርጨ ለታሪክ ለማስቀመጥ ወደ ኒወርክ በተጏዝኩበት ወቅት እግረ መንገዴን ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ጎራ ብዬ የተወሰኑ ቀናቶች ባሳለፍኩባቸው አጋጣሚ  ከአለም ፀሐይ ወዳጆ ጋር ለመገናኜትና የህይወት ታሪኳን ለመቅረፅ  እድል አጋጥሞኝ ነበር ::
አለም ስለሞያዋ ስጠይቃት እራሷን ስትገልፅ  በተለይ ከአንስታይ ፃታ ከማናቸውም የሞያ ባልደረቦቿ ፊት እንዳለች እንኳን እያወቀች ቅድሚያ  እነሱ በታሪክ የሚወደሱበትን ከመግለፅ በስተቀር ስለሷ ችሎታ ስትናገር በጣም ቁጥብ ናት ::  ችሎታዋን ታውቀዋለች በማንነቷም ትኮራለች  ነገርግን  እሷ የትም ብትቀመጥ የፈለገው ደረጃ ቢሰጣት ምርጫውን ለተመልካቹ ህዝብ እንደተወችው ተገንዝቢያለሁ ::
በግል እምነቷ እንደነገረችኝ ከሆነ ከምንም በላይ ጥቃት አትወድም ::  ጥቃትን ፈርታ ከመንገዷ ውጭ እንደማትሄድ አረጋግጣልኛለች ::
በተቻላት መጠን ጏደኞቿን እንደራሷ አድርጋ ለማፍቁር ትጥራለች ::
የምንም ብልጭልጭ ሸቀጥ ምርኮኛም አይደለችም  ግን እንደማንኛውም ሴት  ወይዘሮ ጥሩ መልበስንና ማጌጥን  ጥሩ ለብሳ ሸጋ ሁና መታየትን ትመርጣለች :: ሁሉም በልክ ሲሆን ጥሩ ነው ትላላች ::
የዘመኑ ወጣቶች የሚጎትቱትን አይነት ውራጅ ባህል ግን ነፍሷ ጭምር እንደሚፀየፈው በኩራት ትናገራለች ::
በምግብ አመጋገቧ በኩል እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንጀራ ና ወጥ ትመርጣለች  ::  በተለይ ጥሩ ጥሬ ስጋ መመገብን ትወዳለች :: አስደናቂው ነገር ግን ምንም አይነት ምግብ ስትመገብ  ውሐም እንኳን ቢሆን  አትጎነጭም ትንሽ  ፈሳሽ ነገሮች  ከጠጣች መመገቧን ታቆማለች :: ካጣችም ብዙ.ለሆዷ አትጨነቅም ::
መጠጥ ጨርሶ  መጠጣት አትወድም አንዳንድ ጌዜ ብቻ  የተለያዩ ዝግጅቶች  ስትሄድ ከሰዎች ጋር ለመመሳሰል ስትል ቀይ ወይን እድምትመርጥና የተቀዳላትንም  ወይን ላትጨርሰው እንደምችል  ከቅርብ ወዳጆቿ ሰምቻለሁ ::  በተለይም ከጏደኞቿ ጋር  በምትዝናናበት ስአት ለሰከንድ እንኳን መጨነቅ የሚባልን ነገር እንደማትወድ  መሳቅ መጫወት ደስ እንደሚላት: ትናገራለች ::
አለም ፀሐይ በተፈጥሮ ግልፅ አፍቃሪ ናት : : ሁለት ግዜ ተሞሽራ አለሟን አይታለች  ::  ሆኖም ግን ትዳሯ እሷ እንደምትፈልገው ሳይሆን ቀርቶ አልሰመረላትም ::
ከሁለቱም  ባለ ቤቶቿ  የተለያየችው በሚያስገርም እና በፍቅር ነው ::
ከሁለቱም አንዳንድ ፍሬ አፍርታ የአንድ ወንድና የአንዲት ሴት ልጅ እናት ናት :: ልጆቿም  ወንዱ ትውልድ ታደሰ  ሲባል ሴቷ ደግሞ አይናለም ደጀኔ ትባላለች ::
ሌላው ከዚች ታላቅ ተዋናይ የታዘብኩት ነገር ቢኖር ከሰዎች ጋር የሐሳብ ልውውጥ ስታደርግ  እሷ እራሷ መከራዋን አይታ በከፈተችው   በጣይቱ ምአከል ጋብዛኝ ተገኝቼ ነበር :: ለሁሉም ሰው ከፍተኛ ዋጋ ወይም ክብር በመስጠት ነው ውይይቷን የምትጀምረው ::
ከሰዎች ጋር ስትነጋገር በፈገግታ ነው :: ፈገግታዋም ከአድ ሽህ ቃላት በላይ ሀይል አላቸው ::
ለኔ እንደገባኝ ከሆነ አለም ይህን ችሎታ በተፈጥሮ ብቻ ያገኜችው ሳይሆን በከፍተኛ ልምምድ ያዳበረችው ይመስለኛል ::ይህም ችሎታዋ ከሷ ከራሷ የተፈጥሮ ድፍረት ተጨምሮ ከፍ ወዳለ የሞያ እርከን እንዳሸጋገራት መገመት  ይቻላል :: በዚህ ጠንካራ አስቱሳሰቧ ደግሞ ያሰበችበት ደረጃ ለመድረስ  አስቸጋሪውን የህይወት
ውጣ ውረድ እንቅፋቶችን እንዴት ማለፍ እንደሚገባት ጠንቅቃ የወቀች ይመስለኛን ::
በመጨረሻ ልነግራችሁ የምፈልገው ግን ፣ አለም ፀሐይ በምኞት እራሷን የምታነቃቃ አይደለችም :: ለስራዋ ጥንካሬ ስትል የራሷ የሆነ
አዕምሯዊ ልምምድ የምታደርግ ጠንካራ ሰው መሆኗን ተረድቻለሁ :: አለምን ስለህይወት ታሪኳ  ስለስራዎቿ  ስጠይቃት እጅግ በጣም ትመሰጥና  በሐገሯ የታሪክ ማስታዎሻ የተሞላች ዶሴ በመሆኗ ከትዝታ ማህደሯ የምትፈለቅቃቸው የግጥም ስራዎቿ የስሜት ፈውሶች ናቸው ::  ቀደም ባሉት አመታ ለሙሉቀን መለሰ ከሰጠችው የዘፈን ግጥሞች አንዱን ልንገራችሁና እናንተም ሙዚቃውን  ከሙሉቀን  መለሰ ጋር አብራችሁ ለስለስ ባለ ሙዚቃ እያንጎራጎራችሁ በክፍል አራት እስከምንገናኝ እኔ በዚሁ፣ልሰናበት !!::
ቁመትሽ ፣ ሎጋ ነው ፣ ሰንደቅ ያሰቅላል፣
የሰላም ፣ የፍቅር ፣ምልክት፣ ያሳያል ፣
አይኗ ሲንፀባረቅ ፣ እንደ ኮኮብ :ደምቆ
ሽንጧ :ሲውረገረግ :በአካሒዷ ልቆ
ከጠሩት : አይኖቿ ብርሐን :ይመነጫል
ሽንጧ : ሲተራመስ : ፀጉሯ ይወራጫል
በውበት ብርሐን : በመውደድ  ብልጭታ
ገድላ  :ታስነሳለች : በጥርሷ ፈገግታ
ከንፈሯ ተላቆ : ድምፅዋን : ለሚሰማ
ጭራሽ :ሙዚቃ ነው : የአዕዋፍ ዜማ
ሊታይ : ፈልጎ : እግፘ : ሲንጠራራ
ባቷን : ገላመጠው፣ ዳሌዋ እየኮራ
ያን ሁሉ : ቁንጅና : ለኔ ይሁን ብሎ
ዳሌዋን : ይዞታል : ሽንጧ ገባ ብሎ
አቤቱ ነው : እንጅ ለቁንጅናሽ : ዳሩ
ተወርቶ : አልቆለታል : ቁመናሽ ማማሩ
አንገትሽ  :መቃ ነው : ሸንበቆ ይመስላል
ለሐብሉም : ለዲሪው : እንደልብ : ይበቃል
አሸንክታብ : ድሪ አልቦ:  ወለባ ቀርቶ
ሽመል :ሰውነትሽ : ይታያል : አብርቶ
ድሪውን : ጠልሰሙን : ገላሽ ባያደርግም
የእፍኝ እኩሌታ:  ውበትሽን : አይነፍግም
ለምድና : ጎፈሬ ይሁነኝ : ብለሽ
ጌጤ መድመቂያዬ : እራስ  ወርቄ አንች ነሽ
የእኔ በትረ :ሙሴ:  መጥፎሽን : አልወድም
ጠንበለል ነሽ : ሎጋ ይህንን : አልክድም ::
ድምፃዊ ሙሉ ቀን መለሰ (ድርሰት አለም ፀሐይ ወዳጆ)
በሰው ልጆች የአዕምሮ እድገት ታሪክ ውስጥ ስነፅሁፍ ወይንም ትወና በግዜና በቦታ ልዩነት ያላቸው ቢሆንም በአጠቃላይ ግን ከሰው ልጆች ጋር የተገናኙ ናቸው ::
በተለይ ስነ ግጥም ጥልቅ ሐሳብ ሲሆን የሰውነትን ሙቀት ከፍና ዝቅ ሊያደርግ ጅማትና የነርቭ ጫፎችን ሊያዝናና የልብ ምትን ከፍና ዝቅ ሊያደርግ የሚችል የጥበብ መንገድ ነው ::
ተወዳጇ የጥበብ ሰው አልም ፀሐይ ወዳጆም አዳዲስ ሐሳቦችን አፍላቂና ተንታኝ በመሆኗ በስፋትና በጥልቀት  ተመራማሪ ስትሆን
የምትፅፋቸው የዘፈን ግጥሞች ስሜትን አልፈው አጥንት ድረስ ዘልቀው የሚገቡ ዘመን ተሻጋሪ  በመሆናቸው  በሁላችንም ዘንድ አሁን ድረስ ትዝታዎቻቸው የራሳችንን ታሪክ ፈጥረው ይገኛሉ::
የአለም ፀሐይ ወዳጆ ስራዎች 
ግጥም ርእስ                           አቀንቃኝ
አንቺ የሌለሽበት ………..         ኃይልዬ ታደሰ
ሆዴም ሸፈተብኝ ………..         ሂሩት በቀለ
ይዤው እዞራለሁ ……….         ሂሩት በቀለ
ልሂድ ልሰደደው  …………..      ሂሩት ግርማ
እንዴት ከረማችሁ …………..      ሂሩት ግርማ
ምኑን ፍቅር ሆነ  ………….         መሐሙድ አህመድ
ሰላም      …………..                 መሐሙድ አህመድ
ላኪልኝ   ………………………....ሙሉቀን መለሰ
ሌቦ ነይ …………………………..ሙሉቀን መለሰ
ልመላለስበት…………………..… ሙሉቀን መለሰ
መውደዴን ወደድኩት …………….ሙሉቀን መለሰ
ቁመትሽ ሎጋ ነው………………….ሙሉቀን መለሰ
ቁረጥልኝ ሆዴ ………………………ሙሉቀን መለሰ
ተወራርጃለሁ ……………………….ሙሉቀን መለሰ
ትዘዝ በገላዬ ………………………..ሙሉቀን መለሰ
አልረፈደብሽም ………………….  . ሙሉቀን መለሰ
አትከብደኝም ………   ……………. ሙሉቀን መለሰ
ገላዬዋ …………………………….  ሙሉቀን መለሰ
ወይ ያኔ  …………………………..  ሰለሞን ተካልኝ
የሀገሬ ወጣት …………………….  ሰለሞን ተካልኝ
ቸሩ አምላክ ይመስገን ……………..ሰላማዊት ነጋ
ነፍሳችን ትደሰት…………………… ሰላማዊት ነጋ
ጨረቃ  ……………………………..ሰላማዊት ነጋ
ፀበል በወሰዱህ ………………….ሰላማዊት ነጋ
ማፍቀሬን ማን ነክቶ ……………  ሰዩም ዘውዱ
ሸዋ ሰጠኝ ……………………….አጠናው
ዙማዬ  ………………………..   ሰጠኝ አጠናው
የዓባይ ልጅ ………………….    ሰጠኝ አጠናው
ደጅሽ ተሰለፈ ………………….. ሰጠኝ አጠናው
ጐንደር……………………...      ሰጠኝ አጠናው
አባቴ  …………………….        ስንቄ አሰፋ
ልበሽ ካባውን ………………     ሻምበል በላይነህ
ምነው  ……………………….    ሻምበል በላይነህ
ምንጃር ላይ ሰርታ ቤቷን ………..ሻምበል በላይነህ
ኑሪልኝ ሀገሬ …………………… ሻምበል በላይነህ
እርም የለኝ ………………………..ሻምበል በላይነህ
የጊዜ ግልባጭ ………………….ሻምበል በላይነህ
አይመች ለወሬ ………………… በኃይሉ አጐናፍር
ትዝታ ……………………………  በዛወርቅ አስፋው
የማነሽ ይሉኛል ………………    በዛወርቅ አስፋው
ትዝታ  ………………………….   ብዙአየሁ ደምሴ
ተይ ድማም ተይ ድማም…………ታምራት አበበ
ሁለመናሽ ሙሉ ………………….ቴዎድሮስ ታደሰ
ቀለመወርቅ ናት ………………….ቴዎድሮስ ታደሰ
በዓይኔ መጣሽ …………………..ቴዎድሮስ ታደሰ
አንቺንም ላይደላሽ ………………..ቴዎድሮስ ታደሰ
ኧረ ምነው   ………………………..ቴዎድሮስ ታደሰ
ዝምታ ምን ሊሆን …………………ቴዎድሮስ ታደሰ
ግርማ ሞገሴ ………………………ቴዎድሮስ ታደሰ
ጤና አዳም ………………………….ቴዎድሮስ ታደሰ
ጥፋተኛው ገላ……………………… ቴዎድሮስ ታደሰ
ፍቅር አስተሳሰረን …………………….ትዕግሥት በቀለ
ስጦታ ነው ለኔ ………………………. ነፃነት መለሰ
መለል ያለው መጣ……………………. አሰፉ ደባልቄ
ስሚኝ እናት ዓለም…………………….. አሰፉ ደባልቄ
ወለላ ቀምሼ …………………………….አሰፉ ደባልቄ
ወሎ     ………………………..……. አሰፉ ደባልቄ
ጉማዬ ……………………………. አሰፉ ደባልቄ
ሰው …………………………………የለኝ አሳየ ዘገየ
የትዳር ሰው ……………………… ነኝ አሳየ ዘገየ
ለመድክ ወይ ……………………. አስቴር አወቀ
ምን አለደሞ ……………………… አስቴር አወቀ
አታድርገኝ ክፉ  …………………..አስቴር አወቀ
የአባይ ልቡ አይፈራም ……………አስቴር አወቀ
ፍቅር ሽሙንሙኑ ……………….አስቴር አወቀ
ባሕሌን አቦነሽ ………………….. አድነው
እወድሃለሁኝ …………………አቦነሽ አድነው
ዝም አልልም ………………..አቦነሽ አድነው
ሆዴን ሆድ አይባስህ ………… ዓለም ከበደ
ባይልልኝ ነው …………………ዓለም ከበደ
ተው ስልህ ………………….ዓለም ከበደ
ናፈቀኝ እንደሰው ……………ዓለም ከበደ
ክንፍሽን ልዋሰው …………… ዓለም ከበደ
ወሎ   ……………………..ዓለም ከበደ
ይሰለፍሺ ሞት …………… ዓለም ከበደ
ይቻላል ወይ………………… ኤፍሬም ታምሩ
ባለማማዬ  …………………….ኩኩ ሰብስቤ
እንዴት ነህ   ……………………ኩኩ ሰብስቤ
ደኔ በለው በለው  ………………ኩኩ ሰብስቤ
ትዳር መርጫለሁ  …………….ዘላለም
ወግ አማረኝ  ………………….ዘመነ መለሰ
ስምሽን እጠራለሁ  ……………ዜና ምትኩ
ጥሩነት ውበትሽ  ………………….ዜና ምትኩ
ያገር ልጅ    ………………………ደሳለኝ መላኩ
ጐጃም  …………………………..ደሳለኝ መላኩ
ልለፍ በደጅሽ  …………………ደረጀ ደገፋው
መሄድ መሄድ አለኝ  …………..ደረጀ ደገፋው
ተማሪ ነኝ  …………………….ደረጀ ደገፋው
ትዝታው አይጠፋም………….. ዲጄ ማሙሽ
ምን ይሻለኛል ……………….ዳዊት መለሰ
ሱሴ ነሽ ዳዊት …………….መለሰ
ቅጣቴ አልበዛም ወይ ……….. ዳዊት መለሰ
አይሰማሽም …………………. ዳዊት መለሰ
እራበው ዓየኔን ……………..ዳዊት መለሰ
እንዴት ልቻል ………………. ዳዊት መለሰ
አስቤውም አላውቅ …………ጌራወርቅ ነቃጥበብ
እኔ አደለሁማ ……………… ግርማ ተፈራ ካሳ
ተረጋጋሽ ወይ  ………………. ጐሳዬ ተስፋዬ
ለወረት ነው እንጂ ……………..ጠለላ ከበደ
ትዳር ጥሩ ነው ………………..ጠለላ ከበደ
የጥበብ አበባ ………………….ጠለላ ከበደ
ኢትዮጵያ                               ጥላሁን ገሠሠ
ፍጻሜ ያጣ ህልም   …………….ጥላዬ ገብሬ
ስለ እትየ  ………………………ፀሐዬ ዮሐንስ
አታምርም ወይ ………………..ፀሐዬ ዮሐንስ
የአምላክ እጅ ሥራ ……………..ፀሐዬ ዮሐንስ
ጀመረች   ……………………….ፀሐዬ ዮሐንስ
ሐይቅ ዳር ነው ቤቷ  ………….ፋንታሁን ሸዋንቆጨው
መውደዴ     …………………….ፋንታሁን ሸዋንቆጨው
በባህሪ ዕዳ  ……………………..ፋንታሁን ሸዋንቆጨው
አደራ   ………………………..…ፋንታሁን ሸዋንቆጨው
እሺ ይሁን  ……………………….ፋንታሁን ሸዋንቆጨው
ያምራል    ………………………..ፋንታሁን ሸዋንቆጨው
መከታዬ  ………………………….ፋንትሽ በቀለ
ነገ ብራ ሲሆን  …………………….ፋንትሽ በቀለ
አበጀሁ   ………………………....ፋንትሽ በቀለ
እንባ ስንቅ አይሆንም  ……………ፋንትሽ በቀለ
እንዳማረህ ይቅር  …………………ፋንትሽ በቀለ
የሔዋን ልጅ ፈተና   ………………..ፋንትሽ በቀለ
የእኔ ሸጋ …………………………… ፋንትሽ በቀለ
ጉም ጉም  ………………………..ፋንትሽ በቀለ
እስካሁን ያልተሰሩ የዘፈን ግጥሞች
ሕይወቴ ነሽ   ………   ያልተሠራ
በአንቺ አየሁ ………….ያልተሠራ
በክብር አነሳሃለሁ …… ያልተሠራ
ብናልፍም እልፍ ነን ……..ያልተሠራ
ትምጣ እመቤቲቱ ……….ያልተሠራ
ትዝታ ያልተሠራ………    ያልተሰራ
አሁን ምን አለበት  ……… ያልተሠራ
አጥንቱ ለምኔ …………….ያልተሠራ
ፍቅር እንዲ ነው …………..ያልተሠራ
የአለም ፀሐይ ወዳጆ  ስራዎች ሲመረመሩ በከፊል  ይህን ይመስላሉ ለኔ ማድነቅ የሚባለው ቃል አልመጠነልኝም እናንተ ስራዎቿን አይታችሁ  ደረጃውን ስጧት ::
 የምደነቅበት ምክኒያት ግን ስለዚች ታላቅ የኪነጥበብ ሰው ስራዎች  በጥልቀት ለማወቅ የማደርገው መፍጨርጨር ገና ልደርስበት አለመቻሌ ነው :: የአለም ፀሐይ ወዳጆ ህይወትም ሆነ ታሪኳ ድብቅ ሆኖ ሳይሆን የብዙ ሰዎችን አቅም የሚፈታተን ስራዎች በመስራቷ ፣ ልዩ አድርጏታል ::
 ስለ ታዋቂዋ የጥበብ ሰው ደራሲ፣ ተዋናይና ፣ አዘጋጅ በሰሜን አሜሪካ የጣይቱ የትምህርትና የስነ ጥበብ ማእከል መስራች አለም ፀሐይ ወዳጆ  ስራዎችና የህይወት ጉዞ ጨዋትችን እየተገባደደ  ነው ::
የሰው ልጅ ይህንን አላፊውን አለም ንቆ ስለማያልፈው አለም የሚያስብና የሚጨነቅ ሲሆን የማይኖርበትንና ነገ ጥሎት የሚሔደውን ቤት ከመስራት ይልቅ በወገኖቹ ዘንድ ለዘላለም ስምን ሲያስጠራ የሚኖር ታሪክ ሰርቶ ማለፍ ጥቂት ሰዎች የሚያገኙት  እድል ብቻ ነው ::
የመጅመሪያዋ ሴት ፕሬዝዳንት ለመሆን መመኜት ቂልነት ነበር ::
 ” ለጎልድ ማይር ” ግን ይህ ቂልነት ሆኖ አልተሰማትም ::
አለም ፀሐይ ወዳጆም ከጧቱ  በለጋ እድሜዋ የቀሰቀሳት ህልም ይህው ነበር ::  አለም ፀሐይ ወዳጆ በኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ታሪክ ውስጥ   ደረጃ የሚሰጣት ሳይሆን የደረጃ ክልሉን ጣራ ጥሳ ቀድማ በመድረኩ ላይ የዘበነችበት” እቴጌ”  ናት :: የዚችን  ታላቅ ተዋናይ ልብ ለሐገራቸው ባበረከቱት አስተዋፅዎ ማርከው እንቅልፍ ያሳጧት
በኢትዮጵያ ፓለቲካ ወታደራዊና ማህበራዊ ኑሮ ውስጥ ከፍተኛ ብሩህ ሚና ለመጫወት የቻሉት በአለም ላይ ዝናቸው የገነነው እቴጌ ጣይቱ ብጡል ብርሐን ዘኢትዮጵያ አንዷ ናቸው ::
ብርሀን ዘኢትዮጵያ ጣይቱ ብጡል ከምኒሊክ ቀጥለው የኢትዮጵያ ምርኩዝ ሀይል የበሩ ቃላቸውንና ፣አቋማቸውን፣ የማይለወጠው  ብልህና ፣ ጀግናዋ አይበገሬዋ ፣.ሐይማኖተኛዋ ፣ በገና ደርዳሪዋ ” እቴጌ ጣይቱ ብጡል ብርሐን ዘ ኢትዮጵያ ” የገናናዋን ተዋናይ ደራሲና አዘጋጅ ልብ ማርከው  ይችን መከረኛ አለም ከተሰናበቱ 100 አመት ሞላቸው ::
በኢትዮጵያ የነገስታት ታሪክ ውስጥ  እስከ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መግስት ድረስ 225 ነገስታቶች በትረ ስልጣናቸው እየ ተቀባቡሉ ቢነግሱም  :: ለግዜው ባለኝ መረጃ መሰረት ስማቸውን ለታሪክ ጥለው ካለፉት ታላላቅ እቴጌዎች ውስጥ የቀዳማዊ ምን ይልክ እናት ንግስት ሳባ ፣ ከሀድያ ጎሳ ከተገኙት ንግስት ፣ኢለኒ ከአፄ ልብነድግል ሚስት ፣ ንግስት ሠብለ ወንጌል ፣ ከንጉስ ላሊበላ ሚስት መስቁል ክብሯ ፣እንዲሁም  ከ18ኛው ክፍለ ዘመን እቴጌ ተዋበች ፣ የአፄ ቴውድሮስ ሚስት በገናናነትና አለምን ባስደመመ ብልሀት ጀግንነት የአድዋውን ዘመቻ ከምንሊክ ጋር  እኩል የመሩት ብርሐን ዘ ኢትዮጵያ ጣይቱ ብጡል ለሴት እህቶቻችን ያስተላለፉት ተምሳሌነት የአለም ፀሐይ ወዳጆን ሞራል ደረጃ በደረጃ አሳድጎ
የሳቸውን ማዕከል ከማቋቋም አልፎ እሳቸው፣በመሰረቷት የአፍሪካ መዲና በአድስ አበባ ከተማ ለስማቸው መጠሪያ ለታሪካቸው ማስታወሻ ክብራቸውን በሚመጥን ደረጃ ሐውልታቸውን ለማቆም የግል ህይወቷን ገደል ግባ ብላ  የተስፋ ስንቅ ስንቃ ሌትና ቀን እንደምትሮጥ ነግራኝ አለች :: አለም ይህ ስታረጋግጥልኝ ወንድሜ ሆይ !!  ለማንም የማይታሰብ  ሊመስል ይችላል ::
ግን እግዚአብሔርንና የኢትዮጵያን ሕዝብ የያዘ ምንግዜም አሸናፊ ነው ትላላች ::
 ሲሆን ሲሆን  የኢትዮጵያ ህዝብ ለዚያች ገናና የአድዋ ጀግና አዲስ አበባ ላይ ብቻ ሳይሆን በትውልድ ሐገሯ በደብረ ታቦር አብሮኝ ከጎኔ ቆሞ ሁለተኛውን ሐውልቷን ያቆምላታል :: የኢትዮጵያ ህዝብ ውለታ የማይረሳ ሕዝብ ነው ከመሞቴ በፊት ይህ ሐውልት ቆሞ ማየት እመኛለሁ ትላለች :: በእርግጥ በማንኛውም ነገር ድል መቀዳጄት የተሰጠን መብት ቢሆንም እንዴት መቼ እነማን እንደሚያገኙት መገመት ግን ብዙም አስቸጋሪም አይሆንም ::  ከዚህ አንፃር  ኢትዮጵያዊነት ልዩ ትርጉም ይሰጣታል :: የራሳችንን ክብርና  ታሪክ
 ስንጠብቅ ፣ የትብብርና የማህበራዊ ተቆርቋሪነት ፣ ሐላፊነትን ስንቀበልና ስንሰጥ ፣ ማለታችን :ነው  ትላለች :: ኢትዮጵያዊነት የበላበት ወጭት ሰብሮ መወርወርና አካባቢብ ማበላሸት አይደለም ኢትዮጵያዊነት የራስ ክብርና የራስ መተማመን ብቃት ነው ትላለች ::
አለም ፀሐይ በሰሜን አሜሪካን ሳይቀር በጀግነቷ የአለምን ህዝብ
ያሰደመችውን የአድዋ ጀግና ብርሐን ዘ ኢትዮጵያ ” የጣይቱ ማእከል ብትመሰርትም ከስራው አድካሚነትና ማህበረሰቡን ከማሰባሰብ አኳያ ከባድ ፈተና ቢሆንም በስደት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ መሳቅ የሩቅ ግዜ ትዝታ አድርጎ ማሰብ በጀመረበት ወቅት የትዝታን ቀልድና ቁምነገሮች
እያዋዛች በአይነትም ሆነ በጥራታቸው በወር አንድ ጊዜ በጣይቱ ማአከል ያለመታከት ሁሉንምእንደችሎታውና እንደዝንባሊያው  ይዛ እየቀረበች ታዝናናቸውአለች  ::  ከዚህ በተጨማሪም
 ሁለት ሥራ እየሠራች፣ ልጆቿን ታሳድጋለች :: አሁን ባለችበት እድሜዋ    ት/ቤት ገብታ፣ በ Business Administration Degree ተቀብላለች :: ይህ አይበገሬ ፅኑ እምነቷ ለብዙ ወጣት ሴቶች  መልካም ምሣሌ ይሆናል ብየ እገምታለሁ ።
በመጨረሻም የአዲስ አበባ ከተማ ቆርቋሪ ፣የውጫሌ 17 አንቀፅ ደምሳሽ ብርሐን ዘኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ ብጡል እስካሁን ድረስ ስማቸውን የሚያስጠራ የአካል ክፍይ ልጅ ባይወልዱም  ህይወታቸው ካለፈ ከመቶ አመት በዃላ ሐውልቷታቸውን ለማቆም ለስማቸው መታሰቢ ማእከል ለማቋቋም ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች እጅ ለእጅ ተያይዘው  ከአለም ፀሐይ ወዳጆ ጎን እንደሚቆሙ ምንም ጥርጥር የለኝም ::
እኔም  ለአለም ፀሐይ ወዳጆ መልካሙን ሁሉ እየተመኜሁ
በዚሁ አበቃሁ .::
በሌላ ዝግጅት እስከምንገናኝ ቸር ይግጠመን 
አለባቸው ደሳለኝ አበሻ (ለንደን)
Filed in: Amharic