>
5:28 pm - Monday October 9, 6609

"ኢትዮጵያውያን አንዳችን ለአንዳችን ጸጋ እንጂ እዳ አይደለንም" (አንዱ አለም አራጌ) 

የኢትዮጵያችን የቁርጥ ቀን ልጆች ከሆኑት አንዱ እና ከዋንኞቹ ተርታ የምናቆመው ስለኢትዮጵያ ሲባል እርሱነቱን ቤተሰቡን ሰውቶ በሰላማዊው የትግል መድረክ ታላቅ ተጋድሎን ያደረገው
ስለ ሁላችን ሲል የህወሀትን እስከፊ የእስር ቤት ስቃይ ሰቆቃን ተቋቁሞ ከእስር ቢወጣም ዛሬም “… እኛ እንጂ ኢትዮጵያችን መቼ ነጻ ወጣች እና ነው እጃችንን አጣጥፈን የምንቀመጠው ትግሉ ይቀጥላል…” የሚለው አንዱ አለም በጀርመን አገር ደማቅ አቀባበል ላደረጉለት በዴያስፖራ ላሉ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ልብ የሚነካ ንግግር አድርጓል።
“…. እንዲህ አይነት አቀባበል ስላደረጋችሁልኝ እጅግ በጣም ደስ ብሎኛል እግዚአብሔር ያክብርልኝ ይሄ ሁሉ ለእኔ አይገባኝም ….” ቢልም ህዝቡ “ይገባሀል !!!” እያለ በአንድ ድምጽ ሲጮህ ያለፈበትን የስቃይ እና የመከራ ዘመን ቁልጭ አድርገው የሚያስነብቡ
አይኖቹ የደስታ እንባ አወረዙ ፤ በታላቅ ትህትና ዝቅ ብሎ ንባቡን ቀጠለ።
“… ለአመታት በባጀሁባት እንደ ቀበሮ ጉድጓድ ጠበብ እና ዝቅ ብላ በተሰራችው መስኮት አልባ ጉረኖ ውስጥ ሆኜ የዛሬን ቀን ማሰብ ከባድ ነበር…..
“…. ያንን ሁሉ ስቃይ ብናልፍም እንኳ በመከባበር እና በመተባበር ወደ ሰብአዊነት ከፍታ እንወጣለን እንጂ ወደ ኢ ሰብአዊነት አዘቅት አንወርድም…..
“… ሰውን በመጥላት እንጂ ሰውን በመውደድ የተዋረደ ማንም የለም …. ለፍትህ ለዴሞክራሲ የሚደረግ ትግል ሁሉ በጥላቻ ላይ መመስረት የለበትም…. ደማቅ ጭብጨባ አቋረጠው
“…. እኛ ስንተሳሰብ ስንዋደድ የችግሮቻችን ኮረብታዎች ይደረመሳሉ… ኢትዮጵያውያን አንዳችን ለአንዳችን ጸጋ እንጂ እዳ አይደለንም… ደማቅ ጭብጨባ
… የኢትዮጵያ ህዝብ በእኔ እና በቤተሰቤ የደረሰውን ግፍ የእኔ ብሎ ስቃያችንን ስለተጋራን ከልብ አመሰግናለሁ…..
…ዛሬ ሌላ ቀን ነው። የትግላችን ውጤት ብልጭታው በጥቂቱ ይታያል ፤ ነገር ግን አንዳች የተጨበጠ ነገር በሌለበት እጃችንን አጣምረን መቀመጥ እንኳንስ የዴሞክራሲ ሽታ በሌለባት በእኛዋ አገር ይቅር እና የዴሞክራሲ መፍለቂያ ምንጮች በሚባሉት አገርም ትግል አይቆምም ….
እንዱ አለም ይህንን እና ብዙ ቁም ነገር ያዘሉ መልእክቶችን አስተላልፏል ሊንኩን ተጭነው ያድምጡ።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=1718038061611802&id=100002168745973

Filed in: Amharic