>
5:30 pm - Sunday November 2, 6155

የቀናተኛነት መንፈስ በተጋሩዎች መንደር!?! (ቬሮኒካ መላኩ)

1~እንግሊዛዊው ፈላስፋ በርትራንድ ራስል ስለ  Envy ወይም ቅናት ሲፅፍ ” ቅናት Envy አእምሯችንን ሊመርዝ የሚችል አደገኛ መርዝ ነው ” ይልና ። በመቀጠልም በመፅሀፉ
” ናፖሊዮን በቄሳር ይቀና ነበር፤ ቄሳር ደግሞ በታላቁ እስክንድር ይቀና ነበር፤ እስክንድርም ቢሆን በሕይወት ኖሮ በማያውቀው በሄርኩለስ ይቀና ነበር ።” ይላል ።
2~ በአንድ ወቅት እስክንድር ነጋ ደሞ  በፃፈው ፅሁፍ ” መለስ ዜናዊ በአፄ ምኒልክ እጅግ በጣም ይቀና እንደነበርና ሚስቱ አዜብ መስፍን ደሞ በእቴጌ ጣይቱ በቅናት  እርር  እንደምትል  ፅፎ አንብቤአለሁኝ።
3~ ደራሲ ስብሃት ገ/እግዚአብሄርም ትግራይ ያለውን የፉከራና የሽለላ  ስነስርአት በአንድ ወቅት ሲናገር ” እኔ የጀግናው የአማራ ልጅ! ” እያሉ እንደሚሸልሉ  ሲናገር ሰምተናል። ( አሁንም የስብሃት ቃለምልልስ You Tube ስላለ አውርዶ ማዳመጥ ይቻላል) ።
ወያኔ ትግሬዎች በአማራ ባህል ፣ ወግ  ፣ ልማድና ታሪክ ፣ እንደሚቀኑ የአደባባይ ምስጢር ነው። የአማራ የሆነ ሁሉ ነገር የቀን ቅዤት እንደሚለቅባቸውና በፍርሃት እንደሚያርዳቸው  ይታወቃል። ነገር ግን ይሄ የቅናት መንፈስ ድንበሩን ተሻግሮ በተቸገረ አማራ ሁሉ እንደሚቀኑ አላውቅም ነበር።
4~ ሰሞኑን ከቤኒሻንጉል ክልል የተፈናቀሉ አማሮችን ጉዳይ አንስተን  ስንፅፍ  የተመለከቱት የተከዜ ማዶ ሰዎች በቅናት እርር ድብን ብለው ከሁለት አመት በፊት በቦይንግ እና በላንድሮቨር ከጎንደር ወደ ሱዳን  ለሽርሽር የሄዱ ትግሬዎችን ጉዳይ አንስተው አሁንም ለሁለተኛ ዙር ወደ  ሱዳን ለመሄድ ዝግጅታቸውን እንደአጠናቀቁ  ዛሬ የአረናው ሊቀመንበር  የፃፈውን ሲዘዋወር ተመለከትኩ።
ስለዚህ ገደብ የለሽ  ቅናት ምን ይባላል?  ምንም! ! ኦ አንተ አማራ እንደት ያለ የዮቶር መንፈስ ቢያድርብህ ነው ተቸግረህ እንኳን የሚቀኑብህ ?    ይገርመኛልም። ያስደንቀኛልም።

ተፈናቃይ ተጋሩዎች ወደ ሱድን ሊሄዱ ነው

አብርሀ ደስታ
ከአማራ ክልል ተፈናቅለው በምዕራብ ትግራይ ዞን ማይካድራ አከባቢ ከተጠለሉ ተጋሩ 920 የሚሆኑ አስቸኳይ እርዳታ የሚፈልጉ ናቸው። ከነዚህ ተፈናቃዮች ወደ 200 የሚሆኑ ለክልል መንግስት የእርዳታ ጥሪ አቅርበው በቂ መልስ ባለማግኘታው ምክንያት ነገ ዓርብ ግንቦት 3, 2010 ዓም ወደ ሱዳን በመጓዝ የቀይ መስቀል እርዳታ ለማግኘት አቅደዋል። ሽረ አከባቢ የሚኖሩ ተፈናቃዮችም እንደሚቀላቀሉ ይጠበቃል። ወደ ሱዳን የሚጓዙት በድብቅ ሳይሆን የትግራይ ክልል መንግስት፣ ዓረና ፓርቲ፣ የVOA እና የDW Amharic ሪፖርተሮችን በይፋ አሳውቀው ነው። በእርዳታ እጦት ምክንያት ባለፈው ሳምንት ሁለት ተፈናቃዮች የሞቱ ሲሆን ዛሬ ደግሞ የአንድ ሴት ተፈናቃይ ህይወት ማለፉ ተሰምቷል። ተፈናቃዮቹ ከምንም ግዜ በላይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።
Filed in: Amharic