አፄ ዮሀንስ በሞራልም በመንፈስም ዝቅታ ላይ የሚገኝ “መሪ ” ነበር ።
ይሄን ጉዳይ ስም ማጥፋት ነው እንዳይባልብኝ በጣም በአጭሩ አንድ ፣ሁለት ፣ ሶስት ብዬ ላስረዳ ይከተሉኝ ።
…
1~ ዮሀንስ ኢትዮጵያን ሊወርር የመጣውን የእንግሊዝ 35,000 ዘመናዊ ጦር ከምፅዋ ጀምሮ ተቀብሎ ሰንጋ እያረደ ጠጅ እያጠጣ ጓዙን ተሸክሞ መንገድ እየመራ ኢትዮጵያን እንድትወረር ያደረገና ለአፄ ቴዎድሮስም አሳዛኝና የሚያስቆጭ ፍፃሜ ዋና ተዋናይ የነበረ በአገር ክህደት ( Treason) ወንጀል መጠየቅ የነበረበት ሰው ነው ።
…
2 ~ አፄ ዮሀንስ የወሎ ሙስሊሞችን በአሰቃቂ ሁኔታ የጨፈጨፈ መሪ ነው ። ይሄ ጉዳይ መቼም አለም የሚያውቀው ብዙም የተፃፈበት ስለሆነ ለማስረዳት ብዙ መድከም የለብኝም። በኢትዮጵያ ታሪክ በመንግስት አዋጅ እስልምናንና እስላምን ለማጥፋት አዋጅ ያስነገረ መሪ ዮሀንስ ብቻ ነው ። (ስለ ቦሩ ሜዳ ኮንፈረንስ ማንበብ የፈለገ እስኪሰለቸው አሰቃቂውን የዮሀንስ ወንጀል ማንበብ ይችላል)
…
3 ~ << በላይኛው ጌታ በባልንጀራዎ ፣
በቅዱስ ሚካኤል በጋሻ ጃግሬዎ ፣
ጎጃምን ይማሩት ፈሪም አንልዎ። >>
ተብሎ ግጥም እስኪገጠም ድረስ የጎጃምን ህዝብ በደም ያጨቀየ ነው።
…
4~ የራያ ህዝብ ላይ የዘር ፍጅት ፈፅሟል ።
…
5 ~ ከእሱ በፊት ንጉስ የነበረውን ዋግሹም ጎበዜን ወይም አፄ ተክለጊዮርጊስን በጦርነት ተሸንፎ ሲማርከው በክብር ይዞ በህጉ እንደመዳኘት በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም በማያውቅ ሁኔታ አፄ ተክለጊዮርጊስን ሁለት አይኑን በብረት ጉጠት ፈንቅሎ አውጥቶ የገደለ Sadist ነው።
…
ዮሀንስ እንደሚወራለት ለኦርቶዶክስ ክርስትናም ደንታ ያለው መሪ አልነበረም ። ጎጃም ውስጥ ያሉ ታቦታትንም እያወጣ ያቃጠለ ፀረ ኦርቶዶስም እንደነበር መታወቅ አለበት። ቅዱስ ታቦታትን ከመንበሩ እያወጣ እያስፈለጠ ያነደደና ያጋዬ መሪ ዮሀንስ ብቻ ነው።
…
ሌላው የዮሀንስ የግል ህይወትም የሚያስገርም፣ የሚቀፍና ለትውልድ ሞዴል የማይሆን ነበር። ዮሀንስ በንግስና ዘመኑ ህጋዊ ሚስት የሚባል አልነበረውም። የዮሀንስ ቤተ መንግስት ውስጥ የነበረችውን “እቴጌ ” የሚነግረኝ ሰው ካለ በጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርድስ አስመዘግበዋለሁኝ።
…
ዮሀንስ ሁለት ልጆች ነበሩት ። የመጀመሪያ ልጁ አርአያ ስላሴ ሲሆን ሁለተኛው ልጁ መንገሻ የሚባሉ ነበሩ ። የመጀመሪያ ልጁ አርአያስላሴ ገና በ9ኝ አመቱ በታይፎይድ ሞቶበታል ። ሁለተኛ ልጁ ራስ መንገሻ በተደጋጋሚ ጊዜ ከጣሊያንም እየገባ እየከዳ ሌላም ጥፋት በመፈፀሙ በምኒልክ አንኮበር ውስጥ ታስሮ ኖሯል።
የመጀመሪያ ልጁን አርአያ ስላሴን የወለደው ከቴዎድሮስ ሸሽቶ አፋር በርሃ ውስጥ ቤቱ ደብቆ ያስጠጋውን የአፋር ባላባት ሴት ልጅ ሀሊማ የምትባለውን አስገድዶ ደፍሮ ነው።
ሁለተኛ ልጁን መንገሻን ደሞ የወለደው ከወንድሙን ሚስት ነው።
ይሄ የምፅፈው ሁሉ ስም ለማጥፋት የተደረገ ተረት ተረት አይደለም በማስረጃ የተደገፈ ነው።
ታዲያ ይሄ በሞራልም በምንም አርአያ የማይሆን ሰው አማራ ክልል ለምንድነው ሙዚየም የሚሰራለት። ይሄ ፈፅሞ ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ነው።
…
ማጣቀሻ መፅሀፍት
1 ~ አፄ ዮሀንስና የኢትዮጵያ አንድነት (ተክለፃድቅ መኩሪያ)
2~ Mordicaie Abir (ethiooia and red sea)
3~ British expedition to Ethiopia.