>

ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ. . . (አቻምየለህ ታምሩ)

በፍቅረ ሥልጣንና በፍቅረ ንዋይ የናወዘው «ያ ትውልድ» በሥልጣንና በንዋይ እየተደለለ  የማይሽረው ስምምነት፣ የማያጥፈው ቃል፣ የማይበጥሰው ማተብ እንደሌለው ብናውቅም  for the record ግን  ትናንትና በሕዝብ ፊት በተነገረውና  በዛሬው የODF  መግለጫ መካከል ያለውን ልዩነት ለመታዘብ የትናንትናውን ንግግር እነሆ።
በቪዲዮው ላይ እንደሚታየው  የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ምክትል ሊቀመንበር  ዶክተር ዲማ ነገ ባለፈው ሕዳር ወር ጀርመን አገር በሙኑክ ከተማ  በተካሄደ «የኢትዮጵያ አገራዊ ንቅሳቄ» ጉባኤ ላይ «ወያኔ ለድርድር ቢጠራችሁ  ትቀበላላችሁ ወይ?»  ተብለው ለተጠየቁት ጥያቄ  በሰጡት መልስ  «ካሁን በኋላ እንደ አገራዊ ንቅናቄ እንጂ እንደ ኦዴግ ወይንም ODF ከወያኔ ጋር አንደራደርም» ብለውን ነበር።
ይህንን ቃላቸውን ግን  ዛሬ ባፍ ጢሙ ደፍተውት   እንደ ኦዴግ ወይንም ODF ከወያኔ ጋር ለመደራደር ወደ አዲስ አበባ  በሚቀጥለው ሳምንት እንደሚያቀኑ አብስረውናል። ዶክተር ዲማ  በንግግራቸው ብዙ ጉዳዮችን ያነሳሉ።  ኦዴግ ከወያኔ ጋር ለመደራደር  የወሰነው ዶክተር ዶክተር በያን በንግግራቸው ያነሷቸው ጉዳዮች ሁሉ ስለተሟሉ ይሆን?
Filed in: Amharic