>

የአማራ ህዝብ መፈናቀል እንዴት ጀመረ....?

 (የዜና ምንጮች -አዲስ አድማስ፣ ፍኖት_ለነፃነት ጋዜጣ ፣መኢአድ)
=>> በቤሻንጉል ጉምዝ ክልል በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ብሔር ተኮር ማፈናቀል: በጅጅጋ እና በአፋርም የቀጠለ ሲሆን በመላው አገሪቱ አማርኛ ተናጋሪ (አማራውን) እርስቱን በመንጠቅ ቤት ንብረት እንዳይኖረው ፣የንግድ እንቅስቃሴ ላይ እንዳይሳተፍ በተለየ ስልት ደሃ ሆኖ እና ከነባር ይዞታው እንዲበተን ተደርጓል እየተደረገም ነው።
=>> በዚህም ዋና ሴራውን የወጠኑት እና እየተገበሩት ያሉት የህውሃት(የወያኔ)ባለስልጣናት እና ካድሬዎች  አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ቦታዎች  ትዕዛዝ  የሰጡ ሲሆን በአዲስ አበባ ከፈረሱት እና እያፈረሱ አካሉ ቤቶች አብዛኞቹ ነባር የአማራ መኖሪያ እንደነበሩ በአዲስ አድማስ ጋዜጣና መኢአድ ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች አስረድተዋል ።
<< አማራን ከእርስቱ ማፈናቀል…. አዲስ አበባ>>
=>> በአዲስ አበባና በተለያዩ ከተሞች አማራ ብሔር(አማርኛ ተናጋሪውን)የባንክ ብር ጨምሮ መሬት እንዳያገኙ ከመደረጉም በላይ ከፍተኛ ግብር እየተጫነባቸው ከገቢያ ስርዓት ውጭ እንዲወጡ ተደርጓዋል።
<< አማራ ከቤሻንጉል…. ከመተከል፣ ያሶ ዞኖች እንዴት ተፈናቀለ?”
=>> ከቤንሻንጉል ጉምዝ ከ5000 በላይ ከተፈናቀሉት ውስጥ በያሶ ፣በመተከል (የጎጃም መሬት ) በገፍ ያለ የግድያና ዘረፋ የአካል ማጉደል የሃብት ንብረታቸው ተዘርፎ ያለምንም ደጋፊ አልባ ሁነው በሌሎች የጎሳዎች እንዲገሉ ህውሃት የሌሎችን ጎሳ ሰው በመግደል የእርስበርስ ግጭት በመፍጠር በአማራ ህዝብ እራሳቸውን እንዳይከላከሉ መሳሪያቸውን ትጥቅ በማስፈታት አማራውን በቅጥታ የዘር ማፅዳት እንዲካሄድበት አድርገዋል።
<< የሀረር አማራዎች ሰቆቃ…..ግድያ>>
 >> በሀረር ከነበረው ጭፍጨፋ ውስጥ በአንዲ
ወ/ሮ ኢትዮጵያ ይልማ (67 ዓመት አዛውንት ነበሩ በወቅቱ) የምትባል እማወራ ከነባለቤታቸው ቤት ንብረታቸው ተነጥቀው ልጇቸውን በእሳት እንዳቃሉባት እና ከሃረር እንድትባረር መደረጓን ለፍኖተ_ነፃነት_ጋዜጣ በወቅቱ ሰፍሯል።
<< ሀገር አልባ.ከእርስታቸው የተፈናቀሉ አማራዎች ጉዳይ>>
=>> ከ200 በላይ በባህርዳር ከተማ የለ መጠለያ በየጎዳና ዳር ወድቀው የቀሩ አማራዎች በከፍተኛ ስቃይ እንደነበሩ ያትታል ከ3500 በላይ በፍኖተ ሰላም ሰፍረው ያለምንም መጠጠለያና ድጋፍ ለልመናና ለእንግልት መዳረጋቸውን በወቅቱ አዲስ አድማስ በዜና እትሙ ጉዳዩን ለአንባብያን  አድርሷል።
       * ከነዚህም ውስጥ በትቂቱ ዝርዝር እናቅርብ ፦
1, አቶ ገዛው አንድአርጌ ከነ ባለቤቱ እና ከ3ቱ ልጆች ጋር ሲፈናቀል
      *  ወ/ሮ ሰላም ፣የ9ኝ አመቱ ልጃቸው ደሳለኝ ግዛው፣ብርቅነሽ ግዛው (7አመት)፣እናትነሽ ግዛው (3አመት)
2,አቶ ብርሃኑ ብሬ ከነ ባለቤቱ ስም
      *  ወ/ሮ ፀሀይነሽ ስትባል ማስተዋል ብርሃኑ (9አመት)፣አቢ ብርሃኑ (4 ዓመት)፣የሁለት አመት ህፃን ጭምር ይዛለች ።
3, አቶ  በየነ አረጋ ከነባለቤቱ እና ሁለት ልጆቹ ጋር
4, አቶ ስሜ ንብረት ከነ ባለቤቱ ስም ወ/ሮ መሰረት እና ከ2ቱ ልጆች ጋር።
5, አስፋው ሺበሽ ፣ወ/ሮ ትሸት 4 ልጆች ጋር።
6,ዮሃንስ አቅናው ፣ወ/ሮ ትሁን 1ልጃቸው ጋር።
7, ቻላቸው እሸቱ፣ ወ/ሮ አቤነሽ ፈንታ 5 ልጆች ጋር
8, አደራው አለው ፣ ወ/ሮ ፀሐይነሽ እና 3 ልጆች ገር።
9,ቸሬ ብሬ ፣ከነ ባለቤቱና ከ2 ልጆች ጋር።
10,ወልዴ ታዩ፣ ከነፍሰጡር ባለቤቱ ጋር።
11,ፈንታሁን አለሙ ከነ ባለቤቱ እና 4 ልጆች ጋር።
12, ምንገር ጌታቸው ከነፍሰጡር ባለቤቱ ጋር።
ከላይ ላብነት የተጠቀሱት እንጅ የቀሪዎች ዝርዝር ማግኜት አልቻልኩም
<<አማራ…… ለምን?>>
=>> ወያኔ ከመጀመሪያው ጀምሮ የአማርኛ ተናጋሪውን (አማራውን) ህዝብ በብሔራዊ ደረጃ በጨቋኝነት በመፈረጁ በአርባ ጉጉ ፣በበደኖ ፣በአርሲ፣በባሌ ፣በጋምቤላ፣በሀረር፣ኢሊባቡርና፣ጅማ፣ወለጋ፣ እንዲጨፈጨፍ ሲያረግ ምን ያክል አማራውን ለማጥፋት እንደፈለገ አመላካች ነበር።
=>> ስለሆነም ከአንድ አመት በፊት በቤንች ማጅ ዞን በጉራፋርዳ ወረዳ ከፍተኛ ጭካኔ በአማራው አርሶ አደር፣ሴቶች፣ነፍሰጡር ህፃናትና ሽማሌዎች ላይ የነበረው ጭፍጨፋና የማፈናቀል አማራው በግዞት ጎዳና ላይ የትም እንዲወድቅ የኔ ቢጤ ከመሆን አልፎ ለአውሬና ለስቃይ ኖሮ
የተጋለጠው አማራው በቤሻንጉል ፣በጅጅጋ ፣በአፋር፣እና በኦሮምያ ክልል የዘር ማፍፋትና ዘረፋ እየደተፈፀመባቸው በርካታ ምስሎቹና እውነታወች ለታሪክነት በማስረጃ ተመዝግበዋል።
(ታዲህ እንዲህ ያለ ግፍና በደል እየደረሰ እንዴት ዝም ይባላል? እስከመቼ ሃገር አልባ እንሁን? ወገኔ መክት !ለራስህ ለማንነትህ በህብረት ቁም!!)
Filed in: Amharic