>

"ህወሀት አምላክ አይደለችም" (ኦቦ ለማ መገርሳ)

አያና አበራ
ህወሐት ኢህአዴግ 27 አመት ሙሉ ጥላቻን ስሰብክ የኖረ መንግስት ነው።በዚህን ጊዜም በኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ቀላል የማይባሉ ልዩነቶችን ፈጥሯል።ለዘመናት ተከባብሮና ተፋቅሮ አብሮ ሲኖሩ የነበሩትን ማህበረሰቦች ለያይቷል።ሁሉም የኛ ከሚል አገር የኔ ወደሚል መንደር አውርዶታል።አንደኛው ሌላኛውን በጥርጣሬ እንድመለከት አድርጓል።አገርን እየገፉ ገደል ጫፍ አድርሰዋል።ኢትዮጵያን አስጨናቂ ምጥ ይዟት ሁሉም በፍረሓት ሰመመን እየተናጠ ባለበት #ለማ ተገኘ።የፖለቲካው መሐንዲስና ጥበበኛው #ለማ_መገርሣ ሥልጣን በያዘ በአጭር ጊዜ ውስጥ ህወሐት የገነባችውን የጥላቻ ግምብ ንዶ ህዝብ ለህዝብ እንዲተያዩ አድርጓል። በተለይም በኦሮሞና በአማራ ህዝብ መካከል ያለውን ልዩነት በማጥበቡ መላውን ህዝብ ሲያስደስት ፀረ ህዝቦችን ግን አንገት አስደፍቷል።ህዝብን ከህዝ ለማጋጨት ያሰፈሰፉ እንደ ENN አይነቶቹ ፀረ ህዝብ ለጊዜውም ቢሆን ጣታቸውን እንዲሰበስቡ አድርጓል።
ለማ መገርሳ ወደ ስልጣን ባይመጣ ኖሮ  እስከ ዛሬ የስንት ሰው ህይዎት ያልፍ ነበር? ስንት ሰው አካል ጉዳታኛ ይሆን ነበር? ከመፈታት ፈንታ ስንቱ ይታሰር ነበር? ለማ ስንቱን አድኗል? ከተራራ የገዘፈች አይነኬዋን ህወሐት በቆራጥነት ተጋፍጦ ለራሳቸው እስኪገረሙ ድረስ  አይበሬነቱን አሳይቷቿል።   “ህወሐት አምላክ አይደለችም” እንዳለው ባዶ ኮዳ  መሆኗን አሳይቶናል። እድሜ #ለለማ ህወሐት ዛሬ በልኳ ለመኖር ተገዳለች።
Filed in: Amharic