>

የህወሃት እና የብአዴን መስመሮች (ሚኪ አምሀራ)

ኢትዮጵያ ወይ ሙሉ ለሙሉ ወይ በከፊል መቀሌን ያላካተተ ብድር ወስዳ አታዉቅም፡፡ በጠቅላላ ብድር እየተባለ የሚመጣዉ ገንዝብ የት እንደሚፈስ እኒህን መረጃወች እንያቸዉ፡፡
1. ቻይና ለ መቀሌ የዉሃ ፕሮጀክት 250 ሚሊን ዶላር ብድር ሰጠች፡፡ 2010
2. የአፍሪካ ዴቬሎፕመንት ባንክ 104 ሚሊየን ዶላር ለኤሌክትሪክ ማስፋፊያ ከመቀሌ-ዳሎል-ሰመራ አፍዴራ፡፡ 2008
3. የህንድ፤ቱርክ እና ቻይና መንግስት 1.5 ቢሊየን ዶላር ለባቡር መንገድ ከመቀሌ-ታጁህ(ጅቡቲ)፡፡ 2007
4. የአፍሪካ ዴቬሎፕመንት ባንክ 70 ሚሊየን ዶላር ብድር ለኤሌክትሪክ ዝርጋታ ከመቀሌ-አዲግራት-መቀሌ- አድዋ መስመር እና ባህርዳር መቀሌ መስመር፡፡ 1992
5. የፈረንሳይና የአለም ባንክ ብድር 250 ሚሊየን ዶላር ለአሸጎዳ ነፋስ ሃይል ማመንጫ መቀሌ አካባቢ፡፡ 2007
6. ከአለም ባንክ ብደር 500 ሚሊየን ዶላር በላይ መቀሌ ኢንዱስተሪያል ፓርክ፤አዋሳ ናዝሬትና ኮምቦልቻ
7. የተከዜ የሃይል ማመንጫ እና የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ከተከዜ እስከ መቀሌ 350 ሚሊየን ዶላር (የኢትዮጵያ መንግስት)፡፡ 2000
ይሄን ያቀረብኩት አንዲያዉ ለምሳሌዉ ነዉ፡፡ ሌሎች ብዙ አሉ፡፡ ህዝቡ ቢጠቀም ችግር የለም፡፡ ዞሮ ዞሮ ሁሉም ህዝብ እንዲጠቀም ነዉ የሚፈለገዉ፡፡ ዉሃ የሌለዉ ዉሃ ቢያገኝ፤ መብራት የሌለዉ መብራት ቢያገኝ ችግር የለዉም፡፡ ዋናዉ ቁም ነገሩ ግን ህወሃት የዉሃ መስመር፤ የባቡር መስመር፤ የኤሌክትሪክ መስመር፤ የአዉሮፕላን መስመር፤ በቃ ያልገነባዉ መስመር የለም፡፡ ብአዴን ደግሞ የመስመር መፋለስ እያለ በአመት 30 ጊዜ ይሰበሰባል፡፡ ብአዴን መስመር እያለ የሚሰበሰበዉ ጉድ ቢሰመር ደቡብ አፍሪካ ይደርሳል፡፡በብድር እና በእርዳታ የሚመጣዉ በቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ የት ደረሰ ብሎ ጠይቆ አያዉቅም፡፡ ንግድ ባንክ እና ልማት ባንክ የአማራ ክልል በጀትን የሚያስንቅ ብድር ለአንድ የህወሃት ባለሃብት ሲያበድሩ ጠይቆ አያዉቅም፡፡ እነ ተክለብርሃን አምባየ 4 ቢሊየን ብር ከንግድ ባንክ ሲበደሩ ይሄ ነገር ብሎ አያዉቅም፡፡ ኧረ ለክልሉ የተበጀተ 5 ቢሊየን እኛ አንጠቀምበትም ብሎ ለሌላ ክልል ሲሰጥ እራሱ አይተናል፡፡ በረከት ነዉ እንዲያዉም ለምን ሲባል እኛ ፕሮጀከት አልቀረጽነም ያለዉ፡፡
የአማራ ገበሬ መከራዉን አይቶ እያረሰ ያልተጠቀመበትን የዉጭ ብድር መክፈል እንዲሁም ኤፈርትን መደጎም እዚህ ላይ ማብቃት አለበት፡፡
ግልባጭ ANDM CC office ANRS Communication Affairs Office OPDO official
Filed in: Amharic