>
5:13 pm - Thursday April 18, 3286

በረከት ስምኦን ማለት....!?! (መኮንን ተስፋዬ)

የተሟላ እንዲሆን ስለ ጀግኖች መተረኩ

ትግሉን የጎዱትም ይነገር ታሪኩ!!!

በረከት ስምኦን ማለት….!?!
መኮንን ተስፋዬ
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ለመጀመርያ ግዜ የህዝብ አመጽ በተቀነባበረ መንገድ በድርጅት እየተመራ የተጓዘበት የኢህአፓ ታሪክ ነው ብንል ከእውነት የራቀ አይሆንም። የኸም የትግል ጉዞ የአፄውን የፊውዳል ስርአት ገርስሶ በህዝብ መንግስት ለመተካትና ደሞክራሲን ለማንገስ የነበረ ሲሆን ድሉ በምርጥ መኮንንኖች ብሎም በፋሺዝም  በአቋራጭ ተቀምቶ የህዝብ ተስፋ ደብዛ ጠፍቶ የወጣቱ ደም እንደጎርፍ የፈሰሰበት አሰቃቂ ዘመን  ነበር።
ኢህአፓ ከአመሰራረቱም በትግል ታሪኩም በኢትዮጵያዊነት የማይደራደር ድርጅት ስለሆነ ከውስጥ በፋሺስት ደርግ በሌላ በኩል ደግሞ በዘረኛ የትግራይ ድርጅት “ የትግራይ ነፃ አውጪ” ወያኔ ከፈተኛ ጥቃት ደርሶበታል።  በኤርትራ “ነፃ አውጪ” ሻአብያና በሱዳንም ይህ ነው የማይባል የማዳከም ዘመቻ ተካሂዶበታል።
ከራሱ ድርጅትም ውስጥ በወጡ ከሃዲና አንጃወች በከተማም ሆነ በገጠር ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። ከድርጅቱ በከሃዲነትና በአንጃነት የወጡ፤ በከተማ ከደርግ ጋር በማበር፤ በሜዳ በኢህአሠ  ውስጥ ከነበርሩት ደግሞ አንዳዶቹ ከወያኔ ጋር በማበር ለብዙ የቁርጥ ቀን ልጆችና ጀግና ኢትዮጵያውያን እልቂትና ደብዛ መጥፋት ሁነኛ ምክንያት ሆነዋል። ከወያኔ ጋር ያበሩት አንጃዎች ከወጣለት ዘረኛ ቡድን ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ህዝብ እየወጉ ለስልጣን እንዲበቃ ብሎም የወጣለት ዘረኛና አፓርታይድ ስርአትን መስርቶ እንዲገዛ ሁነኛ መሳርያ ሆነዋል። እስካሁንም ድረስ አብረው ስልጣን በመጋራት አልያም ከውጭ ሆነው የተቃዋሚውንና የህዝቡን ትግል በማዳከም የወያኔን እድሜ በማራዘም ይገኛሉ። አንዴ ባንዳ ሁሌም ባንዳ እንደሚባለው!!!
ወያኔ በራሱ አምሳል ጠፍጥፎ  የሰራው  ባእዴን የተባከው ድርጅትና መስራቾቹ  ሞራል የሌላቸው ቅንጣት ያህል እንኳን ህዝባዊ ጎን የሌላቸው የስልጣን ጥመኞች ስለነበሩ ከወጣለት ከሃዲና ዘረኛ ድርጅት ጋር በመቆም በኢትዮጳያ ላይ ዘምተዋል ስለዚህም በታሪክ መሃደር ወስጥ ወራሪውን የጣልያን ቅኝ ገዢ ከደገፉት ባንዳወች ጎን ለጎን ይዘገባሉ።
በአዴንን የፈጠረ ወያኔ ድራማው አያልቅበትምና አሁን ደግሞ በ 12ኛው ሰአት ለመሞት ጣራ ላይ ቢሆንም አልሞት ባይ ተጋዳይ በመሆን የህዝብን አመፅ ለማኮላሸት ትንንሽ ባአዴኖች በጎጠኝነት በየ ውጭ ሃገሩ ፈጥሮ አንድነት እንዳይኖር ህዝብ መከፋፈሉን ሃቀኛ ታጋዮችን ስም ማጥፋትና የትግሉን ትክክለኛ መስመር ለማሳትና የራሱን እንድሜ ለማራዘም ሙከራውን ተያይዞታል።
እነኝህንም ትንንሽ ጎጠኛ በአዴኖች የወያኔ ድራማ ይብቃ ወያኔን ወደ ከርሰ መቃብሩ ለመወርወር  ሁነኛ መሳርያ ኢትዮጵያዊነት ብቻ  ማለት የግድ ይሆናል!!!!!!
እነኝህን በየውጭ ሃገሮች ተቅምጠው ህዝብ አንድ እንዳይሆን  ቀን ከማታ የሚሰሩ፤ እውነተኛ ታጋዮችን ስም የሚያጠፉ፤ ወጣቱን ውዥንብር ውስጥ የሚከቱ ማጋለጣችንን እንቀጥላለን። ወያኔን ስንዋጋ እስከ አሰሱ ገሰሱ ነውና!!!!!
የበረከት ስምኦን ታሪክ ይቀጥላል!! 
ኤርትራ በእንግሊዝ ወታደራዊ ግዛት ስር በወደቀችበት ጊዜና በፌደሬሽኑ ዘመን፤ ፤ ብዙ የኤርትራ ትወልጆች ወደ ጎንደር የመጡበት ግዜ ነበር ። ከነኝህም መካከል የበረከት ስምኦን አብትና እናት አቶ ገብረ ሕይውትና ወ/ሮ ብሬ( ዕደይ ብሬ) ይገኙበታል። አሁን በሕይወት አይኖሩም። ሁለትም የተቀበሩት በኖሩበት ከተማ በጎንደር ነበር። በጎንደር ከተማ ልዩ ስሙ አምባ ጂኔ በሚብለው ሰፈር ቤት ሰርተው፤ ሀብት ንብረት አፍርተው ልጆች ወልደው ከህብረተሰብ ጋር በሠላምና ፍቅር፤ በመተባበርም አብረው ይኖሩ ነበር። ከልጆቻቸው መካከል አንዱ ፤ አሁን የወያኔ አገልግይ የሆነው፤የቅድሞ ስሙን የለወጥው፤ የዛሬው በርከት ስምኦን ነው። በረከት ስምኦን በጎንደር ከተማ ልዩ ስሙ አባ ብየዕግዚ ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር ተወለደ። ተወልዶ ያደገበን የጎንደር ከተማንና አንከብክቦ ያስደገውንም ሕዝብ በመክዳት፤ የወያኔ ቅጥረኛነቱን ተልዕኮ  ለማከናወን ከወያኔ ጎን በመሰለፍ  ወንጀል ፈፃሚ ሆኗል ። በተለየ መልኩ ጎንደርን ብሎም ባጠቃላይ ኢትዮጵያ ሀገራችንን  እየጎዳ ተቀምጧል ።
አምበርብር በሚል የሜዳ ስም የሚታወቀው በረከት ስምኦን በ1972 ዓ.ም. ኢሕአሰን በመክዳት ወደ ወያኔ ከሄዱት ቁልፍ ከሃዲዎች መካከል አንዱ ነው። ከመክዳቱ በፊት በረከት በኢሕአሠ ውስጥ የአንድ ጋንታ ኮሚሳር ሆኖ ሲሰራ የነበረ ሲሆን በወቅቱ በደርግ አንጻራዊ ጥንካሬ በመደናገጥ ከጥቂት ጓደኞቹ ጋር በመሆኑ በሰራዊቱ ውስጥ አንጃ ፈጥረው ችግር ሲፈጥሩ የነበረ መሆኑ ይታወቃል። በወቅቱ ሲያካሂዷቸው ከነበሩ ጸረ ድርጅቶች ተግባሮች መካከል የተለያዩ ምክንያቶች በመደረደር የሰራዊቱን እንቅስቃሴ ማደናቀፍ፤ ጦርነት አልዋጋም በማለት አቋም መውሰድ፤ የመጠጥና የዝሙት ባህል ማስፋፋት፤ ሰራዊቱና ፓርቲው አልቆለታል ብሎ ቅስቀሳ ማካሄድ፤ አባላት በድርጅታቸው ላይ እምነት አጥተው የመታገል ፍላጎታቸው እንዲላላ ማደረግና የመሳሰሉት ይገኙበታል።
በረከትና ጓደኞቹ ለተወሰነ ጊዜ ታስረው በኋላ በአመክሮና በይቅርታ ቢሊቀቁም የጀመሩትን የአንጃ ስራ ቀጥለው በሰራዊቱ ውስጥ መፈንቅል ለማካሄድ በቅተዋል። በመጨረሻም አብዛኛው የሰራዊት አባላት ወደ ሌላው የሰራዊት ክፍል እና ወደ ሌላ ቦታ ቢሄድም በረከትና ጓደኞቹ ከወያኔ አመራር ጋር ተላልከው ያሰባባስቡትን ጀሌዎች ይዘው፤ መሸከም ያልቻሉትን መሳሪያና ጥይት  ወንዝ ውስጥ ጨምረው ወደ ትግራይ ሄደዋል። በበለሳ ከነበረከት ጋር ግምባር ቀደም ሚና ከነበራቸው መካከል የተዋጣላት ነጭ አረቄው ቀምቃሚ ተፈራ ዋልዋ፤ አስማረ (ኮበሌ)፤ ይትባረክ (ህላዊ ዩሱፍ) ይገኙባቸዋል።
ትግራይ እንደደረሱ በርካታ አብረዋቸው የነብሩ ሰዎች ትተዋቸው ወደ ሱዳን ሲጓዙ ከሌላ አካባቢ ኢሕአሰን በመክዳት የተቀላቀሏቸውን እነ ጌታቸው ጀቤሳ (ያሬድ ጥበቡን ) በማካተት የወያኔ አሽከርና አገልጋይ የሆነውን ባዕዴንን በእነመለስ ትአዛዝና አስተባባሪነት ፈጠሩ።
በረከት ስምኦንና የመሳሰሉት በኢትዮጵያ ሉአላዊነት የተደራደሩ፤ ተንከባክቦ ባሳደጋቸው ህዝብ ላይ ከወያኔ ጎን ቆመው ጦር የሰበቁ፤ ያስገደሉ፤ያስጨፈጨፉ፤ በአንድ ዘር ላይ የታለመ እልቂትና ጉዳት ያደረሱ፤ ሃገራቸውን ለባእዳን አሳልፈው ለመስጠት መሳርያ የሆኑ ከታሪክ ተጠያቂነት እንዳያመልጡና የህዝብ ፍርድ እንዲያገኙ ተግተን መሰራት የእያንዳዱ ኢትዮጵያዊ ግደታ ነው።
ልዩ ልዩ የህዝብን ትግል የጎዱ፤ አሁንም እየጎዱ ያሉ፤ በንፁሃን ደም የታጠቡ፤ በህዝብ ጠላትነት ጎራ የተሰለፉ ግለሰቦች አጭር ታሪክ በዚህ አምድ ስር ይቀጥላል!!!
ማሳሰብያ፡  በፎቶው ላይ የሚታዩት ከሕወሓት ጋር በመተባበር  ኢትዮጵያ ላይ ጦር ከሰበቁ መካከል አቶ ታምራት ላይኔ እና በረከት ስምዖን በብአዴን 3ኛ ጉባኤ ላይ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በረከት ሲምኦን ባሁኑ ግዜ ነው።
ፍርድ የህዝብ ነው!!
አንድነት ሃይል ነው እናቸንፋለን!!!
Filed in: Amharic