
የሲሚንቶ ገበያው ሲደራ የውጭ ኩባንያውም ገባበት። ዳንጎቴ በምሳሌነት ይጠቀሳል። የዳንጎቴን ሰራተኛ ሞሶቦ ሙገር ላይ እንዳደረገው በተወሰነ ብር አባብሎ መንጠቅ አይችልም። በማስፈራራት፣ በሴራ እንደ ሙገር ለማንበርከክ አይጥሩም። የውጭ ኢንቨስትመንት የሚሉትን መና ያስቀራል። በዳንጎቴና በሞሶቦ መካከል ያለው ጥራት የትየለሌ ነው። ሞሶቦ ገበያውን ለዳንጎቶ እየለቀቀ መጣ! በዚህ ከቀጠለ መክሰሩ ነው! አፈር አፍሶ የሚሸጠው ሞሶቦ ከከስ ደግሞ ኢፈርት ከሰረ ማለት ነው። ፖለቲካውን በገንዘብ ኃይል የተቆጣጠረው ትህነግ ከሰረ ማለት ነው!
ትናንት ምን ተፈጠረ? ኃላፊውና ሌሎች ግለሰቦች ተገደሉ።
ምን አልባትም ኢትዮጵያ ለመዋለ ንዋይ ምቹ አይደለችም፣ የአደጋ ዞን ነች ብለው ጥለው እንዲሄዱ ይሆናል። ይህ የተደረገው ደግሞ ኦሮሚያ ላይ፣ ያውም በአብይ ዘመን። ለትህነግ/ህወሓት ብዙ ትርፍ ያለው ሴራ ይመስለኛል።