
የዚህ ሁሉ ጸረ ህዝብ እና ጸረ-ሃገር ተንኮል ደሞ በግራም በቀኝም ብሎ በሚቀጥለው ምርጫ ዙፋን ላይ በመለስ ዜናዊ ተመልምሎ ላለፉት እረጅም አመታት እየተገፋ ስልጣን ሲከመርለት እና ስሙ ሲጋነን እና ሲንቆጳጰስ የኖረውን ቴወድሮስ አድሃኖምን ወደ ጠ/ርነቱ ቦታ ለማምጣት ነው። ከወዲሁ ቴወድሮስ አድሃኖምን ወደ ስልጣን የማምጣቱ ዘፈን ግጥም እና ዜማ ምን እንደሆና መገመት ይቻላል። የተማሩ የተመራመሩ፣የኢትዩጵያ የጠና ጥበቃ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመሆን ከፍተኛ የስራ ልምድ ያካበቱ፣ ከሃገር አልፈው የአለምን ህዝብ በከፍተኛ አመራር እያገለገሉ ትልቅ ስምን ከተረፉት ከዶ/ር ቴወድሮስ አድሃኖም የተሻለ ኢትዩጵያን ለመምራት ብቃት ያለው መሪ የለም. . .ገለመለ ገለመለ”እየተባለ ከበሮ ሊደለቅ ተዶልቷል።
ችግሩ ግን ቄሮ እና ፋኖ መራሹ የኢትዩጵያ ተራማጅ ህዝብ ማን ምን እንደሆነ ያውቃል። ካሁን ወዲያ በኢትዩጵያ ምድር ላይ በኢትዩጵያ ህዝብ ጀርባ ላይ በደም ከተጨማለቀው ከህወሃት ነፍሰበላወች መሃከል ማንም ማንም ማንም ተመልሶ አይፈናጠጥም። ጠ/ሚሩን በማደናቀፍ፣ የኦህዴድ እና ብዓዴን መሪወችን በመደለል እና በማስፈራራት የትኛውንም ህወሃቴ በኢትዩጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ለመጫን ከተመሞከረ ተራራን አንቀጠቀጥኩ የሚለው ጎራ ተራራን የሚያቀልጥ የህዝብ ቁጣ ምን እንደሚመስል ያየዋል። ዘመነ ቴወድስ አድሃኖምን በኢትዩጵ በህልማቸው ካልሆነ በእውን እንደማያዮት ይረጋገጥላቸው።