>
7:25 pm - Monday May 16, 2022

የዞን ዘጠኝ ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ ላይ ተጨማሪ 28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠ!

የዞንዘጠኝ ጦማርያኑ እና ጋዜጠኞቹ ላይ ተጨማሪ 28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠ!
ዛሬ አራዳ “ፍርድ ቤት” አንደኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት
ናትናኤል አበራ
አጥናፍ ብርሃኔ
ዘላለም ክብረት
እንዲሁም
ጋዜጠኞቹ
ኤዶም ካሳየ
ተስፋዓለም ወልደየስ
አስማማው ሀይለጊዮርጊስ ላይ ተጨማሪ 28 “የምርመራ ቀናት” ሲፈቀድ ፣ ፍርድ ቤቱ የፍትህ ስርአቱ መፋጠን እንዳለበት እና ከዚህ በሁዋላ የፓሊስን ምክንያቶች እንደማይቀበል አስጠንቅቋልም ተብሏል። ሁሉም ታሳሪዎች በጥሩ መንፈስ ላይ እንደሆኑ በቦታው የነበሩ ወዳጆቻችን አስተውለዋል።
ማስታወሻ
የጦማርያኖቹ እና የጋዜጠኞች እስር ፓለቲካዊ መሆኑን እና ምንም ወንጀል አለመስራታቸውን እያስታወስን ዛሬ ፍርድ ቤት ለተገኙ ከ300 በላይ ለሚሆኑ የዞን ዘጠኝ ወዳጆች ከፍ ያለ ምስጋና እናቀርባለን።

Zone nine blogers 2

ዞን ዘጠኝ ጦማርያን

Filed in: Amharic