>

የአውሮፓ ህብረት የጥፋት  ዘመቻ  (ሀብታሙ አያሌው)

ምዕራባውያን የኢትዬጵያ ህዝብ ስነልቦና በሃይማኖተኝነት ችንካር የተሰቀለ በመሆኑ በቀላሉ እየተንጠራሩ ማውረድ ላለመቻላቸው ዋነኛ ምክንያት እንደሆነ በሚገባ ያውቃሉ።
ለዘመናት ከመፅሐፍ ቅዱስ ጀርባ አዝለው የዞሩት ስውር ዓላማ ለመምከኑ ምክንያት ከምሁር እስከ ገበሬ ከህፃን እስከ አዛውንት የኢትዬጵያን ህዝብ በመነፈሳዊነት  ስነ- ልቦና እና በሞራል ከፍታ ለመታተሙ ምክንያት በዋነኛነት የኦርቶዶክስ ተዋህዶን ቤተክርስቲያን እና የኢትዬጵያ እስልምናን ይከስላሉ።  ለኦርቶዶክስ ትጥፋ እና እስልምና ይዳከም መዝገበ ቃላታቸው  ፈርጀ ብዙ ምክንያት  ቢኖራቸውም  ወቅታዊ እና ቀን ከሌት እየደከሙ ካሉባቸው ቀዳሚ ጉዳዬች አንዱ ግብረ ሰዶምን በኢትዬጵያ ምድር ላይ ማወጅ ነው።
በእርግጥም በህወሓት የበላይነት በሚመራው የኢህአዴግ መንግስት ግብረ ሶዶማዊነት  ከዳዴ ከፍ ብሎ ቆሞ እየሄደ ነው፡፡ ሸገር አዲስ አበባ በይፋ የግብረ ሰዶም መለያ ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለበች ነው።   ፓትርያርክ አባ ማትያስና የሚመሩት ሲኖዶስ ለዚህ ግድ የላቸውም።  ምኩን የሆነው መጅሊስም ይሄ አያስጨንቀውም።  ህወሓት እስካለ ለፖለቲካ አጀንዳ ማስፈፀሚያ የዋለው ቤተክህነትም መጅሊሱም አሉ። ሞራልና እምነትን አስጥለው ህዝብና አገርን ለፓርቲ ጥቅም እያስገበሩ ይኖራሉ። ህወሓትም በስልጣን ለመቆየት  የኃይል ሚዛን መግዣ  በድፍረት ለግብረሰዶም መስፋፋት ተልኮ እንደ ዳረጎት አቅርቦናል። አርቲስት እና አክቲቪስት ታማኝ በየነ እንዳለው የቁልቁለት ጉዟችን ልክ አጣ !!
             ከታች ያለውን  ማስፈንጠሪያ ስትጫኑት ደግሞ የጉዞውን እርቀት ያሳያችኋል። ይህ መልዕክትና መረጃዬ በተለይ ለሃይማኖት አባቶች ይድረስ !!
በተያያዘ

ጅቦች  በቀደዱት  Sex tourismሞች  በኢትዮጵያ ውስጥ “ሬንቦ” የተባለ ማህበር አቋቋሙ!??!

 ታደለ ጥበቡ
አዲስ አበባ  ከአፍሪካ  ህብረት ጀርባ አውሮፓ ዪኒየን ቢሮ ላይ  የግብረሰዶም መለያ ባንዲራ በይፋ ተሰቅሏል። 
ደርግ እና ህውሃት “ፈሪሃ እግዚአብሔርን”አፈራርሰው ፈሪሃ ሌኒን እና ፈሪሃ ማርክስን  ሲተክሉብን ጅቦች  በቀደዱት  Sex tourismሞች  በኢትዮጵያ ውስጥ “ሬንቦ” የተባለ ማህበር አቋቁመው በይፋ ስራ ጀምረዋል።
ለምሳሌ የጣሊያን ዜግነት ያላቸው  ራንቺፍ ፎክቲዎሊ የተባሉ ግለሰብ፣ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ዙርያ በሚገኝ ወላጅ አልባ ለሆኑና ለአካባቢው ልጆች የትምህርትና ዕርዳታ በሚሰጥ ድርጅት ውስጥ፣በታዳጊ ወንድ ሕፃናት ላይ የግብረሰዶም ወንጀል ፈጽመዋል።
የግብረሰዶማውያን ዋና ተጠቂዎች
-ከ14 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት፣ የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ የከፍተኛ ተቋማት ተማሪዎች እንዲሁም በማረሚያ ቤቶች ውስጥ የሚገኙ የህግ ታራሚዎች
-እንዲሁም በወላጆቻቸው የተረሱ ህፃናት፣ ከአንድ ወላጅ ጋር ብቻ የሚኖሩ፣ የጐዳና ተዳዳሪዎች፣ ስደተኞች፣ የአዕምሮ ውሱንነት ችግር ያለባቸው ሰዎች፣ የአካል ጉዳተኞችና በህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ በብዛት ይጠቃሉ።
ግብረሰዶማውያን በኢዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች የራሳቸው መገናኛ ሆቴሎች፣ መቀጣጠሪያ ካፌዎች፣ የተመሳሳይ ፆታ ወሲብ መፈፀሚያዎች፣ መዝናኛና ማሣጅ ቤቶች ያላቸው ሲሆን በአብዛኛው በቦሌ አካባቢ የሚገኙ ሲሆን በተለይ ደግሞ ፍሬንድሺፕ ህንፃ፣ ቦሌ ድልድዩ አጠገብና፣ ቦሌ ሸዋ ዳቦ፣ ፒያሳ፣ አራት ኪሎ፣ ቦሌ፣ ሳሪስ፣ መካኒሳ፣ ጎተራ፣ ሲ.ኤም.ሲ.፣ ሃያ ሁለት፣ ካዛንቺስ፣ ገረጂ
፣ቦሌ ከሚሊኒየም አዳራሽ ጀርባ ያሉ ደብዛዛ የምሽት ቤቶች፣ ኤድና ሞል ሲኒማ፣ አትላስ፣ ፍሬንድሺፕ፣ ፍላሚንጎ፣አምባሳደር የሚገኘው ፍል ውሃ መታጠቢያ፣ወሎ ሰፈር፣ሃያ ሁለት አካባቢ ያሉ ፔንሲዮኖች፣ ቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጀርባ፣ጎተራ ኮንደሚኒየም እና ሲ.ኤም.ሲ. አፓርታማ ያሉ ሰፈሮች ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ቦታዎች ናቸው፡ “ዜጋ” የሚለው ቃል የመግባቢያ ኮድ ሥማቸው ነው!
ለአንድ ቀን ለወንድ  አዳር  እስከ 15,000 ብር ድረስ እንደሚከፍሉ  በቅርቡ የተደረጉ ጥናቶች ያሳያሉ።
ግብረሰዶማውያን  ከተለመዱት የወንዶች አለባበስና ስታይል ለየት ያሉና በቀላሉ አይን የሚስቡ ነገሮችን ማድረግ የሚያዘወትሩ ሲሆኑ አብዛኛዎቹ በግራ ጆሮአቸው ላይ ሎቲ ያደርጋሉ፡፡ ጠበብ ያሉ (ታይት) ሱሪዎችን፣ ሰውነትን በተለይም ደረትና ክንድን የሚያጋልጡ ልብሶችን መልበስና ሱሪያቸውን ዝቅ በማድረግ ፓንታቸውን እያሣዩ መሄድንም ያዘወትራሉ፡፡  ብዙውን ጊዜም ነጣ ያሉ (ድፍን ነጭ) ካልሲዎችን በክፍት ጫማ ማድረግን ያዘወትራሉ፡፡ ሁልጊዜም ንፁህና መልካም ጠረን እንዲኖራቸው ይተጋሉ፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ  በኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ ስለ ግብረ ሰዶማዊነት ይናገራል፡፡ የሰዶምና የገሞራ ሰዎች ግብረ ሰዶማውያን ነበሩ፡፡ ሰዶምና ገሞራ በዮርዳኖስ ሸለቆ የተቆረቆሩ ከተሞች ነበሩ፡፡ በእነዚህ ሁለት ከተሞች ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ግብረ ሰዶማውያን ማለትም ወንድ ከወንድ፣ ሴት ከሴት ጋር ዝሙት የሚያደርጒ ይህ ኃጢአትም በእነርሱ ይበዛ ስለነበር ስያሜው የቦታውን ስም በመያዝ ግብረ ሰዶም ተባለ፡፡ በዘመናት ሁሉ ይህን ኃጢአት የሚሠሩ መጠሪያ ሆኖ አገለገለ፡፡ ዛሬም በግብር የሚመስሉአቸው ሰዎች ግብረ ሰዶማዊ ወይም ሰዶማውያን እየተባሉ ይጠሩበታል፡፡ የሰዶምና የገሞራ ሰዎች ወንድ ከወንድ፣ ሴት ከሴት ጋር የሚፈጽሙት ዝሙት አጸያፊ ስለነበር እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ወሰነ፡፡ (ዘፍ. 18÷20፣ ዘፍ.19÷5-9)፡፡ ሁለት መላእክትን ወደ ሰዶም ላከ፡፡ ሁለቱ መላእ ክት የእግዚአብሔር ሰው እና ከሰዶማዊነት ግብር ንጹሕ የነበረውን ሎጥን ከከተማው እንዲወጡ ካደረጉ በኋላ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን በእሳትና በዲን አጠፋ፡፡ (ዘፍ.19÷10-26) ሰዶምና ገሞራ አሁን በጨው ባሕር እንደተሸፈኑ የሥነ ምድር ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ሰዶምና ገሞራ የክፋት ሁሉ የፍርድም ምሳሌ በመሆን ተጠቅሰዋል፡፡ (ኢሳ. 1÷9-10፣ ኢሳ. 3÷9፣ ኤር. 23÷14፣ ሰ.ኤ.4÷6፡፣ ሕዝ. 16፡46፣ ማቴ.10÷15፣ ራእ. 11÷8)
መጽሐፍ ቅዱስ ግብረ ሰዶማዊነት ነውር እና አጸያፊ እንደሆነ ይመሰክራል፡፡
– (ዘሌ. 30÷13)
 (ዘፍ. 13÷13)
 (ይሁዳ. ቁ. 7)
 (ሮሜ. 1÷24-27)
 (ቆሮ. 6÷9-10)
  ዘሌ 20: 13
ግብረሶዶማዊነት ይሄን ያህል የተወገዘ መሆኑ እየታወቀ የኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 6/29 እና  አንቀጽ 6/32  ግብረሰዶም ወንጀል መሆኑን ቢደነግግም  ለምዕራቡ ዓለም ለጋሽ አገራት ውትወታና ጫና እጅ የሰጠው ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር በራሱ ግፊት “የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት” የግብረሰዶማዊያን ጉዳይ በይቅርታ ከማይታዩ ወንጀል ነክ ጉዳዮች ወጥቶ በይቅርታ ከሚታዩ የወንጀል ጉዳዮች አንዱ ሆኖ እንዲታይ አስወስኗል፡፡ዛሬም የአውሮፓ ዪኒየን በኩራት ቢሮው ላይ ሰቅሎት ውሏል።
Filed in: Amharic