>

እፎይ… ጠቅላያችን "ከሚሚ ቅርሻት የማዕዛ ጣዕም ይበልጣል" አሉን  (ስዩም ተሾመ)

“የእናት ሆድ ሽንጉርጉር ነው” እንደሚባለው ኢትዮጲያም እንደ #እስክንድር_ነጋ የሚወዳት፣ እንደ #ሰብሃት_ነጋ የሚጠላት አላት፡፡ እንደ ጋሽ #ሰብሃት_ገብረእግዚያብሄር ያለ ኢትዮጲያዊ በወለደ መሃፀኗ እንደ #መለስ_ዜናዊ ያለ ጎጠኛ  ወልዳለች፡፡ “ጋዜጠኛ” ሲባል #ተመስገን_ደሳለኝን አይተን ዞር ስንል #ተመስገን_በየነ መጥቶ ድንቅር ይልብናል፤ #የማዕዛን ጣዕም ልናጣጥም ስንል #የሚሚ ቅርሻት ድንገት ደርሶ ይከረፋናል፡፡ “የኢትዮጲያ” ብሮድካስት ባለስልጣኑ ኣይተ ዘርዓይ አሰግዶም የመጣና ከንቧ ማዕዛ ይልቅ የዝንቧን ቆሻሻ ያወድሳል፡፡ ያኔ ጣዕሙ ወደ ጣር ይቀየራል፡፡ ከእውነት ጎን የቆሙ፣ ጥሩነትን ዓላማ ያደረጉ እነ እስክንድር፥ ጋሽ ሰብሃት፥ ተሜና ማዕዛ ያሉት እየተብጠለጠሉ ውሸትን የሚሰብኩ በመጥፎ ተግባራቸው የሚታወቁት እነ አቦይ ስብሃት፥ መለስ፥ ሚሚ ያሉት ይወደሱበታል፡፡ በዚህ ምክንያት ለብዙዎቻችን እውነት እና ውሸት፣ ጥሩ እና መጥፎ ይምታታብናል፡፡ መንግስት የሚለውና እኛ የምናውቀው ነገር እንደ ነጭ እና ጥቁር ይለያይብናል፡፡ ትላንት ግን የሆነ የተለየ ነገር ከዶ/ር አብይ አንደበት ሰማን!!!
ከሚሚ ቅርሻት የማዕዛ ጣዕም ይበልጣል አለን፡፡ እኛም መንግስት እውነትን “እውነት”፣ ጥሩን “ጥሩ” ማለት መጀመሩን ባየን ግዜ “እፎይ”አልን!!
Filed in: Amharic