>

ጥገናዊ ለውጥ ውሎ አድሮ ወደ ትርምስ እና እልቂት ይወስደናል እና ይህንን መፍቀድ አንችልም!!! (ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ)

ከዶክተር አብይ ጠቅላይ ሚንስትር ሆኖ መሾም በኋላ የሀገራችን ፖለቲካ በሁለት ምክንያቶች በጣም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚሻው ነው።
አንደኛ ፡ ዶክተር አብይ በቃላት ደረጃ ለማድረግ እፈልጋለሁ የሚሏቸው ነገሮች አብዛኛዎቹ እኛም የምንፈልጋቸው እና እስከ ዛሬ የታገልንላቸው አላማዎቻችን ስለሆኑ የሚሉት የምራቸውን ከሆነ እንዲሳካላቸው ከልብ መመኘት ብቻ ሳይሆን በተቻለን መጠን ልናግዛቸው እንፈልጋለን። እኛ እነኚህን ውጤቶች ነው እንጂ የምንሻው የግድ እኛ ካላመጣናቸው አንልም። እንደ ድርጅት እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲመጣ የማገዝ እንጂ ስልጣን የመያዝ ፍላጎት ኖሮን አያውቅም። በርግጥም ይህን የሚጠራጠሩና መጠራጠርን ብቻ በራሱ ትልቅ የፖለቲካ እውቀት አድርገው የሚያዩ ሀይሎች እንዳሉ እናውቃለን። እነሱ ተጠራጠሩም አልተጠራጠሩም ግን በድርጅታችን ውስጥ ስር የሰደደውና በፍጹም የማያወላውለው ዕምነታችን ይኸው ነው።
በሌላ በኩል  ፡  ግን አሁን ያለውን የፖለቲካ ኃይል አሰላለፍ ከስሜት በወጣ መንገድ ካየነው  ከመጀመሪያው ቢሆንስ (እውነተኛ የዴሞክራሲያዊ ሽግግር) ይልቅ የሁለተኛው ቢሆንስ (ጥገናዊ ለውጥ)እውን የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው። ዶክተር አብይ ወደ ጥገናዊ ለውጥ እያመሩ ላለመሆኑ ማረጋገጫ ማግኘት እንሻለን። ጥገናዊ ለውጥ ውሎ አድሮ ወደ ትርምስ እና እልቂት ይወስደናል እና ይህንን መፍቀድ አንችልም።
እነኚህ ሁለት ሁኔታዎች ተቃራኒዎች በመሆናቸው በከፍተኛ ጥንቃቄ መራመድ ይኖርብናል።  
 የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ሙሉ ንግ ግ ር  ቀጣዩን ሊንክ  በመጫን ያድምጡ/ይመልከቱ።
Filed in: Amharic