>

በበደኖና በአርባጉጉ በአማራው ላይ የዘር ጭፍጨፋ የፈፀመው ማን ነው? (ኡመር ያሲን)

ከ1984 እስከ 1987 ዓ.ም በበደኖና በአርባጉጉ በአማራው ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ተፈፅሟል:: እንጥፍጣፊ ሰብአዊነት በጎደላቸው ጨካኝና አረመኔ በሆኑ ባለስልጣናት ንፁሀን አማሮች ከነህይወታቸው ገደል ተከተዋል:: ዘግናኝ ጭፍጨፋ የተፈፀመባቸውን የንፁሀን አስከሬ ጥልቀት ካለው ገደል በገመድ እየተጎተተ ሲወጣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) ተመልክተናል::
ለብዙ ግዚያትም ሰው መሆናችንን እንድንጠላ አድርጎናል::ይሄ ሁሉ ዘግናኝ ጭፍጨፋ የተፈፀመው በኢህአዴግ ባለስልጣንና በኦኖጎቹ የያኔው የማስታወቂያ ሚ/ር በነበሩት ዶ/ር ዲማ ነገዎና ሌንጮ ለታ ጭምር ነው::
ኦነግ በጠረባ ተመትቶ 50 ሽህ ጦሩን በትኖ ከሀገር ሲፈረጥጥ የአማራውን ጭፍጨፋ በሚመለከት ኢህአዴጎች ጭፍጨፋውን ያካሄደው ኦነግ ነው ምክኒያቱ ደግሞ በሚኒሊክ ግዜ ደረሰብን ላለው በደል የበቀል ጅራፍ ነው ሲል:ኦነግ ደግሞ ጭፍጨፋውን ያካሄደው ኢህአዴግ በተለይም ህወሀቶች በህዝቦች መካከል ደም ለማቃባት ስለፈለጉ ያደረጉት ነው በማለት ለተለያየ ሚድያ ሲገልፁ ኖረዋል::
ሜዳውም ፈረሱም ይሄው እንዳለው ያገሬ ሰው አሁን እርስ በራሳቸው ሲካሰሱ የነበሩት ሰዎች(ኢህአዴግና ኦነግ)ሸገር ላይ ይገኛሉ:: አሁንስ በበደኖና በአርባጉጉ የዘር ጭፍጨፋ የፈፀመው ማን ነው?
Filed in: Amharic