>
5:21 pm - Sunday July 20, 9947

የተጣሉ መስለው የነበሩት ሻእቢያ፣ ህውሓትና፣ ኦነግም " እንደገና ፍቅር እንደገና" እያሉ ነው (ዘመድኩን በቀለ)

 ” የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፤ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።” ዕንባ 3፣7
~ የተጣሉ መስለው የነበሩት ሻአቢያ፣ ህውሓትና፣ ኦነግም የዐማራውን ከእንቅልፉ መንቃቱንና    አዚሙ መገፈፉን ባዩ ጊዜ ” እንደገና ፍቅር እንደገና ” የሚለውን ሙዚቃ ቴፕ ከፍተው በትግርኛም በኦሮምኛም እስታይል የዝላይ ጭፈራቸውንም የእሽክርክሪት መንቀጥቅጣቸውንም በይፋ መጀመራቸው በአደባባይ መታየት ጀምሯል። በድመ ፣ ጾረና ፣ ዛለአምበሳ ፣ ሽራሮ ፣ ቡሬ የገበሩት የዐማራና የኦሮሞ ልጆች ደም በትግራይ ምድር ተንጣሎ ፣ ተንሳፍፎ የፍርድ ያለህ እያለ እየጮኸ ነው። ሀገሬን ብለው ዘልለው በፈንጂላይ የቆሙ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች አስታዋሽ አጥተው። ድሮም የባድመው ጦርነት በስህተት ነው እየተባለ ነው። 80 ሺ ወጣት ጭዳ ከሆነ በኋላ ማለት ነው።
~ ኢትዮጵያን እንደዶሮ ብልት 12 ቦታ በመሸንሸን ዛሬ ለገባችበት አዘቅት የዳረጓት 3ቱ የሌሊት ወፎች መለስ፣ ኢሳያስና ሌንጮ ለታ ወነኞቹ ዲዛይነሮች ነበሩ መሃንዲሶች። አንዱ ሲጎድል ሁለቱ ግን አሉ። እናም ሁለቱ አሁን የማታ ማታ የጭንቁ ቀን ሲመጣ በቀን በብርሃን፣ በፀሐዩ ከያሉበት ተጠራርተው መሞዳሞድ ጀምረዋል። አንዱ ከአስመራ ፣ አንዱ ከቡሌ ሆራ ።
ወዳጄ ! ድሮም እኮ
~ ህውሓት ሲፋቅ ሻአቢያ ነው ።
~ ኦህዴድም ሲፋቅ ኦነግ ነው ።
~ ብአዴን ሲፋቅ #ኤሪትግ ነው ተብሎ ሲነገር አልሰማ ብለን እንደዋዛ አልፈነው ነው እንጂ ነገርየው ድብን ያለ እውነት እኮ ነው። አዳሜ ስትስቅበት የነበረው ጉዳይ አሁን በገሃድ ፈጥጦ ሊያስለቅስህ ከደጃፍህ ቆሟል። በነገራችን ላይ አቶ ሌንጮ ያፈሰሱት የዐማራው ደም ጠርቷቸው እንጂ ከእንግዲህ እድሜ አግኝተው ሥልጣንም ላይ ወጥተው እንደበፊቱ ዐማራውን ያርዱታል ብዬ አልጠብቅም። ባይሆን ልምድ አካፋልው ሊያሳርዱት ይችላሉ ብዬ እገምታለሁ።
~ #ሻአቢያ፦ በኤርትራ ምድር በአስመራ ጎዳናዎች ዐማራ ናቸው ያላቸውን ኢትዮጵያውያን በመኪና አስሮ በየመንገዱ እየጎተተ አሰቃይቶ ገድሎ ተሳለቀባቸው ። ከአሰብ ያባረራቸውን ኢትዮጵያውያን የውስጥ ሱሪያቸውንና የወርቅ ጥርሳቸውን ሳይቀር ገፍፎና ነቅሎ መለመላቸውን አዋርዶ ወደ ኢትዮጵያ ላከ። ገሚሱን እስርቤት፣ ገሚሱን ደግሞ ድንጋይ እያስፈለጠ በባርነት የኤርትራን ፒራሚድ ገነባበት። እናም የብዙ ዐማራዎች ደም እና እንባ በኤርትራ ምድር እየፈላና እየገነፈለ ዛሬ ኤርትራን ያለ ወንድ አስቀራት። የራሔልን ዕንባ የሰማ የተቀበለ ጌታም የዐማራውን ግፍ ቆጥሮና ደፍሮ ኤርትራን ወጣት አልባ የሽማግሌና የአሮጊቶች ሀገር አድርጎ አስቀራት ።
~ ዛሬ ኤርትራውያን ከኤርትራ ለመውጣት ነፍሳቸውን መስዋዕት አድርገው ያቀርባሉ። የሱዳን፣ የሊቢያና የግብጽ ወንበዴ ሆድቃቸውን ቀድዶ ኩላሊታቸውን በቁማቸው የሚዘረፋቸው ምስኪኖች ሆነዋል። ባህር የሚውጠውን ቤቱ ይቁጠረው። አያቶቹ የጎንደር ዐማራና አባቶቹ የትግራይ ትግሬ የሆነው ሻአቢያ በዐማራ ላይ ሻአቢያ የፈጸመው ግፍ በዚያች ምድር ገና እሳት ከሰማይ ያዘንብባታል። ጠብቁ ።
~ ህውሓት ፦ በሻአቢያ ተጠፍጥፎ በደደቢት በረሃ ከተሠራ በኋላ ቁጥር አንድ ጠላቴ በእሱ አጠራር #ነፍጠኛው የሚለውን #የዐማራውን ነገድ ካላጠፋሁ ሞቼ እገኛለሁ ብሎ ትግሉን ጀመረ። ባገኘበት ቦታ ሁሉ ዐማራ ነው የሚባለውን ሁሉ እየገደለ፣ ዘሩን እያጠፋ እያሰደደ ከዛሬ ደረሰ። በሞኝነት፣ በየዋኽነትም መንገድ እየመሩ፣ እንጀራ እያጎረሱ፣ ውኃ፣ ጠላ እያጠጡ፣ ስንቃቸውን ቋጥረው፣ ጓዛቸውን ተጨክመው፣ ከደርግ ጋር ታግለው ተዋግተው፣ ተከዜን አሻግረው ጎንደር ባህርዳር ወልድያ ደሴ እያሉ አዲስአበባ አስገብተው ከሚኒሊክ ቤተመንግሥት ያስገቡዋቸውን ምስኪን ዐማሮች ሳይቀር ይኸው ያለፉትን 27 ዓመታት ዘራቸውን አምክነው፣ አፍነው፣ አቆርቁዘው፣ አደህይተው፣ ከሞቱት ባላይ፣ ከቆሙት በታች አድርገው የበቀል ጥማቸውን ተወጡባቸው።
~ አጼ ምንልክ ጨቁነውናል በሚል የፈጠራ ወሬ ዐማራው በተለየ መልኩ ተጠቃሚ የሆነ ይመስል በምኒሊክ ቤተመንግሥት በኃይሥላሴ ዙፋን፣ በመንግሥቱ ኃይለማርያም ወንበር ተቀምጠው ዐማራውን ወቁት፣ ወገሩት፣ ሌሎች አናሳ ብሔሮች እንኳ መታወቂያ ሠርተው ለይተው እንዲ ቀጠቅጧቸው አበረታተው ሲችሉ፣ በጥይት ካልሆነም በጦርና በቀስት፣ በገጀራም፣ በጩቤና በቢለዋም፣ ደግሞም በክትክታ ዱላ ዐማራው በቤንሻንጉል ጫካዎች፣ በወልቃይት በራያ፣ በጉርሱም፣ በበደኖ፣ በበሻሻ፣ በአርባጉጉ፣ በጉራ ፈርዳ እንደማርያም ጠላት ቀጠቀጡት። አፈናቀሉት። ለዚህ ሁሉ ተጠያቂዋ ህውሓት ናት። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ጀንበሯ መጥለቁ አይቀርም።
~ ኦነግ ፦ የዮሐንስ ለታው ኦነግ የጃጀ፣ የደነዘዘ፣ ባለ ምርኩዝ ጎታታ #ሰው ባላ ድርጅት ነው። ድርጅቱ በህውሓትና በሻአቢያ እንቁልልጮ ተብሎ ሥልጣን እንዳማረው ምራቁን እያዝረበረበ እንደቋመጠ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ መድረክ የተገፋ ከንቱ ድርጅት ነው። ድርጅቱ የሰው ስጋ በመብላት የሚታወቅ ሳዲስት ድርጅት ነው። በሰሜን ተራሮች ላይ ከደርግ ጋር የነበረው ውጊያ ከብዶ የህውሓት ታጋዮች የሚበሉት ቢያጡ ዕጣ ተጣጥለው እርስ በእርሳቸው ይበላሉ እንደነበር ራስ ደጀን ቅዱስ ያሬድን በጎበኘን ጊዜ የሰማነው ታሪክ ነው። ሎቱ ስብሃት።
~ ኦነግም የኦሮሞ ታጋዮችን ያውም የኦሆዴድን ታጋዮች በምርኮ በያዘ ጊዜ የሴት ኦሮሞዎችን ጡት እየቆረጠ፣ የወንድ ኦሮሞዎችንም ጭን እየጎመደ ይመገብ እንደነበር ” በአንድ ወቅት የኢትዮጵያ ፕሬዘዳንት የነበሩትና አሁንም ለምስክርነት በህይወት ያሉት ዶር ነጋሶ ጊዳዳ ” #ዳንዲ_ነጋሶ [ ወይም የነጋሶ መንገድ ] በሚለው መጽሐፋቸው በገጽ 150 ላይ እንዲህ ሲሉ ነበር ከትበው ያስቀመጡት። ” … እነ ሌንጮና ኦነግ የሚሠሩት ሥራ እኮ መስመሩን የሳተ ነበር። የኦህዴድ ሴት ታጋዮች በኦነግ ጡታቸው ይቆረጥ ነበር። ወንዶች ደግሞ የጭናቸው ሥጋ እየተቆረጠ ብሉት ይባሉ ነበር። በበደኖ በርካታ ሰዎች ከእነህይወታቸው በገደል እየተወረወሩ ተገድለዋል። ይሄ የተፈፀመው በኦነግ ወታደሮች መሆኑን የኦነግ አመራር አባቢያ አባ ጀበል ፓርላማ ቀርቦ አምኖ ነበር። ይሄ የተመዘገበ ታሪክ ነው…። በማለት ነበር ምስክርነታቸውን በመጽሐፍ ከትበው ለታሪክ ያስቀመጡት።
~ አሁን ዐማራው የተደረገበት የሱዳን ድግምት፣ አዚሙ፣ መተቱ ፈረሰ፣ ረከሰ፣ እናም ነቃ። ብድግ አለ። እስከዛሬ ኢትዮጵያም ሲል ተገድሎ ። ዐማራ ነኝም ሲል ተገድሎ ዋጋውን በመገደል፣ በመታሰር፣ በመገረፍ፣ በመሰደድ ተቀበለ። አሁን ግን ወጣቱ የዐማራ ትውልድ እምቢኝ፣ በቃኝ፣ ዐማራውን የማታከብር ኢትዮጵያ የራሷ ጉዳይ አለ። ብሎም ተነሳ። መጀመሪያ መቀመጫዬን አለች ዝንጀሮ።
~ አንቀጽ 39 ን የፈጠሩት ኦነግ፣ ሻአቢያ እና ህውሓት ናቸው። ዐማራው ለምን፣ እንዴት፣ አረ ተዉ ሲል በአንድነቱ ብቻውን የሚጠቀም ተደርጎ ታየ። በዚህም ምክንያት ዋጋ ከፈለ። ዘሩ ጠፋ። ተጨፈጨፈ። ህገመንግሥቱ ሲጸድቅ ዐማራው ውክልና አልነበረውም። ወኪሎቹ ኤርትራዊው በረከት ስምኦንና ትግራዋዮቹ እነ አይተ አዲሱ ነበሩ። ጉራጌው ስኳሬ ፓስተር ታምራት ላይኔም ዐማራ አሳርዶ ያስበላ ጨካኝ ነው። ኦሮሞ ምን ትጠብቃለህ ቂምህን ተወጣ እንጂ በማለት ዐማራውን በአሰቦት ያሳረደ ነው።  ሲዳማው ተፈራ ዋልዋም ዐማራውን ያስጨፈጨፈ ነው። እንደ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ወደ ሰላሳ ሺህ ዐማራ ስታፈናቅል ደግሞ ህውሓት ሚንስትር አድርጋ ነው የምትሾምህ።
አሁን ታዲያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዐማራው በማንነቱ ለመደራጀት ቆርጦ መነሳት ዐማራውን ቁጥር አንድ ጠላት ባደረጉት ጎራዎች መንደር የሌለ መደናበር ተፈጥሯል።
ሸአቢያ ግንቦት ሰባትንና መሰል በኤርትራ ምድር እንዋጋለን ብለው ያለ ውጊያ የተቀመጡትን በሙሉ በሉ ወደ ሀገራችሁ ግቡና በሰለማዊ መንገድ ታገሉ ብላቸዋለች እየተባለ ነው።
ህውሓትም ከሻአቢያ ጋር የሚያስታርቀኝ የሽማግሌ ያለህ እያለች ነው። በአዲስ አበባ አንዴ በስብሰባ አንዴ በውይይት እየደከመች ነው ። ጀነራሎችም የሃይማኖት አባቶች ተብዬ ካድሬዎችንም ይዛ የሙጥኝ እያለች ነው።
ኦነግ ሆዬም ኦዴግ ነኝ ብሎ ከች ብሎላታል። በሚጠየፈው በምኒልክ ቤተመንግሥትም ገብቶ ከዙፋኑ ሥር መስተንግዶ ተደርጎለታል። ባፈሰሰው የዐማሮች ደም፣ አንክቶ በበላቸው የኦሮሞ ሴቶች ልጆች ጡትና ሥጋ አወራርዶ በበላቸው ነፍሳት ሳይጠየቅ በቦሌ ወጥቶ 27 ዓመት በአውሮፓ ሲጦር ከከረመ በኋላ አሁን መልሶ በዚያው በወጣበት በቦሌ ተመልሶ መጥቶ የንጉሥ አቀባበል ተደርጎለት አዲስ አበባ ፊንፊኔ ገብቷል።
~ ገና ምን አይታችሁ በዐማራው መደራጀትና ዘሩን ከጥፋት ለማዳን ብሎ በሚያደርገው መሰባሰብ መጀመር እንኳን ኦነግ ኦዴግ ሳጥናኤል ከነ ሠራዊቱ ፣ ዲያብሎስም ራሱ ከነጭፍሮቹ ከሲኦል እየተንቀዠቀዡ ሳይመጡ አይቀርም። ዐማራው እምቢኝ አልገደልም ፣ እምቢ አልታረድም ፣ እንቢ አልገረፍም ፣ እንቢ የማንም መጫወቻ፣ የቀስትና የጦር መለማመጃም አልሆንም ብሎ ቅድሚያ ለነገዱ፣ ቅድሚያ ለማንነቱ ከሰጠ፣ አጅሬ ዲያብሎስ የለመደው የደም ግብር ሊቀርበት ነዋ። እናም ገና ይሰባሰባሉ።
~ ለማንኛውም በዐማራው ደም እጃቸው የተነከሩ ሁሉ ለማንኛውም እንኳን ሁሉም ወደ ሀገር ቤት መግባት ጀመሩ። ይግቡ!  ይግቡ !  ግቡም በሏቸው፤ ከምር ይግቡ። ከዚያ መጨረሻቸውን ፈጣሪ ያውቃል።
~ አንተ ግን ዐማራው ሆይ ! የ #መክት_ዐማራን ዓላማ እንዳትዘነጋው። እንዳትተወው። እነደሌሎቹም አንተም ቅድሚያ ለማንነትህ ስጥ። ኢትዮጵያ የትም አትሔድብህም። መጀመሪያ ነገድኽን ታደገው።
~ እንኳን ኦነግ ኦዴግ ዲያብሎስም ከሲዖል ቢመጣ ከመሰባሰብህ ለአፍታ እንኳ እንዳትዘናጋ። ለዐማራው በማንነቱ ከመደራጀትና ዘሩ እንዳይጠፋ ከመከላከል ውጪ ሌላ ምንም ዓይነት መድኅን የለው። አራት ነጥብ።
ሻሎም !  ሰላም ! 
ከራየን ወንዝ ማዶ ።
Filed in: Amharic