>

"ዐቢይ ወደ አቦይ?" (ካሳ ይልማ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአንድ እጁ እያጠበ በሌላው ጭቃ መቀባቱ ተያይዞታል!?!
ካሳ ይልማ
አዜብ መስፍን:-
 *አዎ የሟቹ ሚስት
*አዎ ከቤተመንግሥት አልወጣም ብለው፣ በእግዚኦታ ተጎትተው የወጡት
*አዎ በቅርቡ ትምእት ከሚባለው የህወሓት ሀገር መዝባሪ ድርጅት ኃላፊነታቸው የተነሱት
*አዎ በቅርቡ ከህወሓት ፖሊት ቢሮ በካልቾ የተመቱት
*አዎ ያለምንም ትምህርት ከስልጣን ወደ ስልጣን እንደግል ሱቃቸው የሚቀያይሩት
*አዎ አዜብ በህወሓት ጄነራሎች እነ ክንፈ ዳኘው ከ3ቢሊየን ዶላር በላይ የተዘረፈው ሜቴክ – የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ቦርድ አባል ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐቢይ አህመድ ተሾመዋል።አስመላሽ ወልደሥላሴ አባይ ነፍሶም ቦታ ተገኝቶለታል። ህወሓት የጀመረውን ህወሓት ይጨርሰው ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በታላቁ ቤተመንግሥት ለትግራይ ክልል ሰዎች ግብዣ ባደረገበት ዕለት “በጡረታ ከተገለሉ የቀድሞ ባለስልጣናት መሀከል ከአቶ ታደሰ ሀይሌ በስተቀር ብዙዎቹ አኩርፈዋል።አይዟችሁ አትታሰሩም ብለናቸዋል።ስራም እየፈለግንላቸው ነው።” ማለታቸው ከጠንካራ የመሪ አቋም ይልቅ የህወሓት ገመድ እየጎተታቸው መሆኑን ያሳብቃል።
የካቢኔ ምርጫቸውን ለተመለከተ የእነአዜብ ሹመት ሲጨመር “ዐቢይ ወደ አቦይ?” ብለው መጠየቃቸው ግድ ነው።
Filed in: Amharic