
አንዳርጋቸው በአርበኞች ግንቦት 7 ከታሰሩት መካከል ቁንጮው ነው። በፖለቲካ እስር ከታሰሩት መካከል ቁንጮው ነው። አንዳርጋቸው ፅጌ ታዋቂ ነው። ታዋቂ በመሆኑ ብዙ ተጩሆለታል። ይህ ጩኸትም አሳሪዎችን አክስሯቸዋል።
በአርበኞች ግንቦት 7 የታሰረው ዋነኛው ሰው ሰፈታ፣ በፖለቲካ እስር ቁንጮው አንዳርጋቸው ፅጌ ሲፈታ ግን ሕዝብ በስም ስላላላወቃቸው ብቻ፣ ስላልጮኸላቸው ብቻ ብዙ አንዳርጋቸው ፅጌዎች በእስር ላይ ናቸው።
ለምሳሌ!
በፎቶው ላይ ከአንዳርጋቸው ጎን ሆኖ፣ አንገቱም ወጣ አድርጎ በትኩረት እያየ የሚገኘው አወቀ መኮንን ይባላል። እነ አንዳርጋቸው “በቃ” የሚል ልብስ ለብሰው ሲሰለጥኑት ከተነሱት ፎቶ ላይም ከአንዳርጋቸው ቀጥሎ ይታያል።
እስር ቤት ካገኘኋቸው ታጋዮች መካከል እንደ አወቀ አንዳርጋቸውን የሚያውቀው የለም። ውሏቸው አንድ ላይ ነበር። አሁን አወቀ በእስር ላይ ነው። በርካታ የአወቀ ጓደኞች፣ ኤርትራ ውስጥ ከአንዳርጋቸው ጋር አብረው ይውሉ ያድሩ የነበሩ ወጣቶች በእስር ላይ ናቸው።
አንዳርጋቸው አሸንፎ ተፈትቷል። ሲከስሩ ለቀውታል። ያልተጮኸላቸው ግን አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ። በአርበኞች ግንቦት 7፣ በፖለቲካ ክስ ቁንጮው፣ ማንም እንዳያየው ተፈርቶ ታስሮ የቆየው አንዳርጋቸው ሲፈታ፣ ስማቸው የማይጠቀሰው፣ የማይጮህላቸው አንዳርጋቸው ፅጌዎች ሁሉ በአስቸኳይ ሊፈቱ ይገባል! እነ አወቀ መኮንን!