
መለስ እያንዳንዷ የተናገራት አረፍተነገር በደመቀ ጭብጨባና እልልታ የታጀበች ስለነበረች፣ በዚሁ የተደነቀው እንግሊዛዊ ጋዜጠኛ “የኢትዮጵያው መሪ ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የበለጠ ሞቅና ደመቅ ያለ የህዝብ ሙገሳ እያገኘ ነው” ሲል ገልጾ ነበር።
መለስ በኤርትራውያን ልቦና ልዩ ሥፍራ የነበረው ታላቋን ኢትዮጵያ አድህይቶ፣ በዘር ከፋፍሎና ጥላቻን አስፋፍቶ ለመግዛት የቻለ “ልባም” ልጃቸው ነበር።
ምንም እንኳ በወያኔ አመራር የጋራ አመራር የነበረ መስሎ ቢወራም፣ ሃቁ ግን ከማሌሊት ምሥረታ በኋላ መለስ ብቸኛው አድራጊ ፈጣሪ እሱ ነበር።
ቱባ ቱባ የሚያካክሉ የህወሓት ፖሊት ቢሮ አባላት እኩል ከመለስ ጋር የስልጣን ድርሻ የነበራቸው ቢመስሉም፣ ግን አይደለም። ድርሻቸው እሱ የሰጣቸውን አጀንዳ በፍጹም ታማኝነት መተግበር ነበር። አብነትም መጥቀስ ይቻላል።
ለምሳሌ ደርግ በመጨረሻው የስልጣን ዘመኑ ከወያኔ ጋር ለመደራደር ወደ ሮም የሄደበት ወቅት ነበር። በጠ/ሚኒስተር ተስፋዬ ዲንቃ የተመራው የኢትዮጵያ ልኡክ 26 አባላት እንደነበሩት ይታወሳል። በወያኔ በኩል ግን የኢትዮጵያ ዕጣ ፋንታ ለመወሰን ድርጅቱን ወክሎ የተገኘው የወያኔው ሰራዊት ጌት መለስ ዜናዊ ብቻ ነበር። በእርግጥ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የተባለው የመለስ ካድሬ በሥፍራው የነበረ ሲሆን፣ የሥራ ድርሻው ግን የመለስን ብሪፍ ኬስ (የእጅ ቦርሳ) ከመሸከም እና ጌታውን ከማጀብ የተለየ አልነበረም።
ከሚገርመው ነገር በቅርቡ የወያኔ እና የኦጋዴን ነፃ አውጪ ድርጅት በኬናያ ሲገናኙ፣ ከኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር በኩል እንደ ህወሓት መለስ ብቻ ሳይሆን የተገኘው፣ የኦጋዴን ሊቀመንበር፣ ዋና ጸሃፊ፣ የጦሩ ኃይል መሪ እና የኦጋዴን የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ተገኝተው ነበር። በንፅፅሩ ህወሃት/ኢህአዴግ ምን ያህል የአንድ ፀረ-ኢትዮጵያ ግለሰብ ድርጅት እንደነበር ማወቅ አያዳግትም።
ጠቅለል ባለ መልኩ፣ መለስ እና ግብረአበሮቹ ለአመታት ያክል ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነውን አጀንዳውን ይቃወሙ የነበሩትን በሳል ሰዎች በወንፊት አጣርቶ ካጠፋ በኋላ፣ የኋላ ኋላ “በሬዎቼ” የሚላቸውን የፖሊት ቢሮ “ዞምቢዎች”ን አሰልፎ ስልጣን ከያዘ በኋላ ኢትዮጵያን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ ለ20 አመት ገዝቶ አልፏል።
የወያኔ መሪዎችና ሰራዊቱም እንደ ኤይድስ ቫይረስ የገዛ ሀገራቸውን ሰራዊት እያዳከሙ፣ እየገደሉና እየደመሰሱ ትግራይ ተወልደው ያደጉ አክራሪ የኤርትራ ብሄርተኞችን ተሸክመው ሚኒሊክ ቤተመንግስት ሊገቡ ችለዋል። እስከ ዛሬም ድረስ በአሳሳችዋ “ህወሓት” ስም ኢትዮጵያን አዳክመውና ኢትዮጵያዊነትን አዋርደው እየገዙ ይገኛሉ፡፡
በርግጥ በኢትዮጵያ ያልተጠበቀ፣ ደስ የሚል ክስተት ተፈጥሯል። ባንዳው ህወሃት በቀጠቀጣት ትግራይ “ኢትዮጵያዊነት” እየተዳከመ በመጣበት ወቅት፣ የተቃዋሚው የዓረና ደጋፊዎች ነን የሚሉ ካድሬዎችም ከባንዳው ህወሃት የማይሻሉ ሆነው እየተከሰቱ ባሉበት ወቅት፣ ኢትዮጵያዊነት ለምልሞና ጠንክሮ በደቡብ ኢትዮጵያ በነለማ መገርሳዎችና አብይ አህመዶች ብቅ ማለቱ ነው። በርግጥ የጠ/ሚ አብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣት በራሱ ትልቅ ለውጥ – ማለት ከጠላት አገዛዝ ወደ ኢትዮጵያዊ አገዛዝ የተሸጋገርና፣ የህዝብ ክትትልና ወሳኝ ድጋፍ የሚሻ ሲሆን – የሞተ መስሎ እንደገና እየተነሳ እየገደለ ረጅም መንገድ የተጓዘው የህወሓት ድርጅት ሙሉ በሙሉ እስካልተወገደ ድረስ የኢትዮጵያ ህልውና አደጋ ላይ እንደሆነ ግልጽ መሆን አለበት)።
አንዳንድ ሰዎች የመለስን አገዛዝ ከአፄ ኃይለስላሴና ከኮ/ሌ መንግስቱ ቀጥሎ የመጣ ዲክታቶሪያዊ መንግስት አርገው ያስቀምጡታል። ይህ ግን ፍጹም ስህተት ነው። ለኢትዮጵያ እድገት ብዙ የደከሙት አፄ ኃ/ስላሴ ይቅርና ኮ/ሌ መንግስቱም ከመለስ ጋር እኩል በአንድ ቅርጫት ውስጥ መክተት የታሪክ ስህተት ነው። ኮ/ሌ መንግስቱ በርግጥ ጨካኝ እና ችኩል ዲክታተር ሆነው ኖረዋል። ነገር ግን ለኢትዮጵያ ሀገራቸው የነበራቸው ፍቅር በዚያው ልክ የትየለሌ ነበር።
መለስ ዜናዊ እና የህወሓት ግብረአበሮቹ መጀመሪያ በትግራይ ህዝብ ላይ መጠነ-ስፊ ወንጀል የፈጸሙ፣ የማእከላዊ መንግስት ስልጣን ከጨበጡ ጀምረው ደግሞ በኢትዮጵያ ሀገራችን እና በኢትዮጵያዊው ወገናችን ላይ ለትውልድ የሚዘልቅ ወንጀል የፈጸሙ ናቸው።
የህወሃት ዘመን በጠላትነት መፈረጅ ለኢትዮጵያ ህልውና ይጠቅም እንደሆን ነው እንጂ የሚጎዳ ነገር አይኖረውም። ለምሳሌ በመለስ ጊዜ የተደረጉ ውሎች የኢትዮጵያ ሉ ዓላዊ መብቶችን የሚጻረሩ ስለሆኑ ፋይዳ-ቢስ (null and void) መደረግ አለባቸው። እንደነ አልጀርስ ስምምነቶች ማለት ነው። እነዛ ፋይዳ ቢስ ከሆኑ ደግሞ አብዛኛውን የቀይባህር የአፋር ዳርቻ ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ የሚደረገው ቀጣይ ዘመቻ ተስፋ ያለመልማል። በርግጥ ይህ እልህ አስጨራሽ ትግል እንደ መለስ ለኢትዮጵያ የተቆረቆሩ መስለው የሚዋጉን የባንዳ ኃይሎችን ገና ከጅምሩ በልዩ ልዩ መንገድ ሊያዳክሙን፣ ተስፋ ሊያስቆርጡን ከመፍጨርጨር ወደ ኋላ አይሉም። ጠላት ሀገራችንን የሚጢጢዋ የጅቡቲ ጥገኛ አድርጎ አስቀርቷቷል።
የቀይ-ባህር ጉዳይ ስናነሳ ልክ ሙቶ እንደተቀበረ የጥንታዊ የጋሪዮች ታሪክ አድርገው ሊነግሩን የሚከጅሉ የትግራይ ዞምቢዎችን አትስሟቸው። እነሱ አንደ መቶ አመት ወደ ኋላ ተጉዘው ሙተው የተቀበሩ በአፄ ሚንልክና ጣልያን ጋር የተደረጉ ሙተው የተቀበሩ ውሎች ህይወት ዘርተው ኢትዮጵያን ካጠቁ፣ እኛ የትናንቱ የባድሜ ጦርነት የወለደው የአልጀርስ ስምምነት” ፋይዳ-ቢስ ማድረግ እንዴት ያቅተናል?
ግን ደግሞ የመለስ ዞምቢዎች ተስፋ አይቆርጡም። ሞታቸው የኢትዮጵያ ክብር፣ ዳግም የኢትዮጵያ አንድነትና ትንሳኤ ነውና!!! ግን እነሱ እንደተመኝዋት ሀገራችንማ በትናንሽ ጠላቶች ተከባ፣ ተዋርዳ መኖር የለባትም። እነዚህ የመለስ ከብቶች ብቅ በሚሉበት መድረክ ሁሉ እየደፈጠጡ መሄድ አለብን። ዞምቢዎች በፍጹም አይቀየሩም። አንዴ ሙተዋልና።
በድጋሚ የመለስ/ህወሃት ዘመን የጠላት (መርስነሪ ሩል በኢትዮጵያ) ተደርጎ መፈረጅ አለበት እንጂ፣ እንደ አንደ የኢትዮጵያዊ አካል አገዛዝ ዘመን ተደርጎ መወሰድ የለበትም።
ከዚሁ ሳንወጣ
የትግራይ ልጆች በበታችነት ስሜት እንዲስቃይ አድርገው ካሳበዱት በኋላ ጭንቅላታቸው ላይ አውጥተው ሾሙት፤ ግን ለምን? ክላን ውጤቱን ስለሚያውቁት !!! ይለናል Adane Wussobo የተባለ ጸሀፊ:-
