>

ፌደሬሽኑ ከእስር የተፈቱትን ጀግኖች ይጋብዛል፤ አብይስ ገና መፈታታቸው አይደለምን!????! (በፍቃዱ ሞረዳ)

 ፌደሬሽኑ ከእስር የተፈቱትን ጀግኖች ይጋብዛል፤
አብይስ ገና መፈታታቸው አይደለምን!????!
በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ዶክተር አቢይ ‹‹ ቢገኙ;›› በማለት አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን ለፌዴሬሽኑ ‹‹ፃፉ›› በተባለዉ ደብዳቤ ሰበብ ጫጫታ ደርቷል፡፡
    እኔ ግን የግራም ሆነ የቀኙ ፍላጎት 0x1000 ነዉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ የካሳ መንግሥት ምን ዐይነት የተለየ የፖለቲካ ትርፍ ሊያገኝበት ነዉ ጥያቄዉን ማቅረቡ ?
  ‹‹አይገኝ››  ባዮቹስ የትኛዉን ትርፋቸዉን ( የፖለቲካ) አስልተዉ ነዉ ?
ፌዴሬሽኑ ከዚህ በፊት ከእስር የተፈቱትን ታጋዮች ጋብዞ የለ? ዘንድሮም እስክንድር ነጋን በክብር እንግድነት ጋብዟል፡፡ በቅርቡ ከሕወሓት እስር ቤት የተፈቱትን አቢይ አህመድንስ ቢጋብዝ ምን ይለዋል?
 እንደእኔ ግን ጠሚዉም አይምጡ፡፡ ግርግር፣ ክልከላ፣ሽለላ፣ መፈክር… ሳይኖር አዳሜ ዳላስ ሄዶ ስትሬሱን ያስታም፡፡ ዓለሙን ይቅጭ፡፡  ሙዱን አታበላሹት፡፡
ፌዴሬሽኑ ግን ቢዝነስ ቀረበት፡፡
Filed in: Amharic