>

ከአንዳርጋቸው እና ከአቦይ ስብሃት ማን ነው ኢትዮጲያዊ?  (ስዩም ተሾመ)

“ኢትዮጲያዊን ከሀገሩ ልታወጣው ትችላለህ፣ #ኢትዮጲያዊነትን ግን ከውስጥ ማውጣት አትችልም!” የሚለውን የዶ/ር አብይ ንግግር #ለዳንኤል_ብርሃኔ ማን በነገረው?! ራስ አሉላ በደምና በጎራዴ ያስከበረውን የኤርትራ ምድር #አሰብን መርቀው ለነፍስ አባታቸው ኢሳያስ አፍወርቂ “እንሆ በረከት” ያሉት #የባንዳ_ልጆች “ኢትዮጲያዊ” ተብለው በሚኖሩት ሀገር ለኢትዮጲያ አንድነትና ነፃነት ሕይወቱን አሳልፎ የሰጠው አንዳርጋቸው ፅጌ “ቪዛው ያልታደሰ እንግሊዛዊ ዜጋ ነው” ቅብርጥስ ይለኛል?! አንዳርጋቸው እኮ እንግሊዛዊ ዜጋ የሆነው ከእነ አቦይ ስብሃት ነጋ ጋር እኩል “ኢትዮጲያዊ” መባል ውርደት ስለሆነበት ነው፡፡ ስለዚህ የእነ አቦይ ስብሃት ውድቀት የአንዲን ኢትዮጲያዊነት ያረጋግጣል፡፡ የጎንደር ወጣቶች 2008 ላይ እንደተነበዩት ማፍያው ህወሓት ይወድቃል እንጂ ኢትዮጲያ አትፈርስም!!! ከጥንት ዘመን ጀምሮ ኢትዮጲያ በባንዳ ልጆቿ ቆስላ-ትታመማለች፣ በጀግኖች ልጆቿ ታቅፋ-ተደግፋ፣ ታክማ ትድናለች!! የእነ አቦይ ስብሃት ኢትዮጲያን የማፍረስ ህልም በእነ ለማና አብይ ፉርሽ ሲሆን የአቦይ ስብሃትና ጋሻ-ጃግሬዎቹ ባንዳነት፣ አንዳርጋቸው እና ተከታዮቹ ኢትዮጲያዊነት በደማቅ ታሪክ ተፅፏል፥ ለዝንተ-አለም ተረጋግጧል!! “ንገሩኝ ባይ መንገድ ላይ ምን ያደርጋል” አሉ!!ማን ነው ኢትዮጲያዊ? ሀገር አዳኝ ጀግና ወይስ ሀገር ሽያጭ ባንዳ? “ንገሩኝ ባይ” ሁላ!!!
Filed in: Amharic