>

እኛም ቀኑን እንዲህ አስበነው ውለናል!!! (መሀመድ አሊ ሞሀመድ)

ዛሬ ግንቦት 20 ቀን ነው፡፡ ፀረ-አንድነት ኃይሎች ኢትዮጵያን የተቆጣጠሩበት፣ ሉኣላዊነታችንንና ብሔራዊ ጥቅማችን ጥያቄ ውስጥ የገባበት፣ የሀገራችን ህልውና ፈተና ላይ የወደቀበት፣ ኤርትራ ከእናት ሀገሯ እንደምትገነጠልና ኢትዮጵያም በታሪኳ  የባህር በር ባለቤትነቷን እንደምታጣ የተረጋገጠበት፣ በቀሪው ህዝብ መሓላ አደገኛ የዘረኝነት መርዝ የተረጨበት፣ ሀገር ወዳዶች ሁሉ አንገታቸውን የደፉበት፣ የሀገር ፍቅር ስሜት የሌላቸው ወገኖች ከየትም ተሰባስበው የሀገራችንን አንጡራ ሀብት ለመቀራመት ፊሽካ የተነፋበት፣ ለአገዛዙ ቅርብ የሆኑ ወገኖችና እነሱን  የተጠጋ ሁሉ በአቋራጭ መክበርና መበልፀግ የሚችሉበት ጥርጊያ መንገድ የተከፈተበት፣  ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ባይታወር የሆኑበት፣ ለስግብግቦችና ሆዳሞች የአዲስ ዘመን ብስራት የተነገረበት፣ በሀገርና በወገን ላይ ፈረጀ-ብዙ ግፍና በደል ለመፈፀም ከፋፋይ ኃይል እንደዋዛ መንበረ ሥልጣን የተቆናጠጠበት ቀን – ግንቦት 20፣
“የዘመናት የህዝብ ብሶት የወለደው ጀግናው የኢህአዴግ ሠራዊት ደርግ ሲጠቀምበት የነበረውን የአዲስ አበባ ሬዲዮ ለሰፊው ህዝብ ጥቅም ሲል ተቆጣጥሮታል” – ግንቦት 20፣ 1983 ዓ.ም
እናማ; እኛም በከፍተኛ ብሔራዊ ቁጭት እንዘክረዋለን – መቼም አንረሳውም፡፡
Filed in: Amharic