>

ዶ/ር ዓቢይና አቶ ለማ (ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም)

አንዳንዶች ሰዎች የዶር. ዓቢይንና የአቶ ለማን የለውጥ መሪነትና የለውጥ አራማጅነት ወደዜሮ ደረጃ ያወርዱታል፤ ክብሩን ለራሳቸው ማድረግ አምሮአቸው አይመስለኝም፤ እኛ በዜሮ ደረጃ ላይ ቆመን አንድ ሰው ቀድሞን አምስተኛው ሰማይ ላይ ሲቆም ያቁነጠንጠናል፤ በዚህም የተነሣ ኢትዮጵያ መሪ የማይበቅልባት ምድረ በዳ ሆናለች፤ ሁሉም በመጠላለፍ የተካነ ሆኖ ‹‹በርታ! አለሁልህ!›› የሚል አይገኝም፤ ዛሬ ለማና ዓቢይ ያለውን ኃይል ተጋፍጠው የከፈቱት የለውጥ ጎዳና ወያኔን አስደንግጦ በእነዚህ የለውጥ አራማጆች ላይ አደጋ ባንዣበበት ጊዜ የዓቢይንና የለማን ጎራ በማጠናከር ፋንታ ማዳከሙ ማንን እንደሚጠቅምና ማንን እንደሚጎዳ ትንሽ ብናስብበትና ሀሳባችንን ብናቃና አገሪቱን ከጥፋት ለማዳን እንችል ይሆናል፤ አስተሳሰባችንን በማቃናት ሁለቱን የእግዚአብሔር ስጦታዎች እንደግፋቸው፡፡

Filed in: Amharic