>

"ራሳችን ታግለን ባመጣነው ድል፣ ድሎቻችንን ሊቀማን የሚችል ኃይል እየገጠመን ነው"  - አምባሳደር ስዩም መስፍን (በወሰን ሰገድ ገ/ኪዳን)

ከምሽቱ 4:30 ሲል ዐይኔን ቴሌቪዥኔ ላይ ቸክዬ እንድቀር ግድ የሚል ፕሮግራም ገጠመኝ፡፡ ቴሌቪዥን ጣቢያው #Walta ነው፡፡ እነ አምባሳደር ስዩም መስፍን ለግንቦት 20 በትግራይ ክልል ያቀረቡትን “ጥናት” እና ውይይት ነው እያስተላለፈ ያለው፡፡ ስዩም መስፍን ጥናታቸውን ሲያቀርቡ ነው የጀመረው፡፡ 1:20 ደቂቃ የፈጀው ፕሮግራም ከተጠናቀቀ በኋላ ለ30 ደቂቃ ት…ክዝ ብዬ ቀረሁ፡፡
.
ምን አስተከዘኝ?
.
ጥናት አቅራቢው ያቀረቡትን ፅሁፍና ተሰብሳቢዎቹ የሠነዘሯቸው አስተያየየቶች ናቸው ያስተከዘኝ፡፡ በተለይ አቶ ስዩም በንግግራቸው መሃል የሠነዘሯቸው አንዳንድ ዓረፍተ ነገሮች የሚያስተክዙ ሆነው ነው ያገኘኋቸው፡፡ ምን ነካቸው? ሠውየው አሁንም እዛው ናቸው፡፡ እዛው አብዮታዊ ዴሞክራሲ ችንካር ላይ ተሠቅለው “ወይም ሞት” ያሉ ነው የሚመስለው፡፡
እናም በየመሀሉ በሚቀረቅሯቸው ቃላቶች (ዓረፍተ ነገሮች) እያስተከዙኝ ነው ፕሮግራሙ ያለቀው፡፡ ለምሳሌ ያህል አንድ ሶስት አባባላቸውን ልጥቀስ፡፡
“አንዳንዶች አብዮታዊ ዴሞክራሲ አርጅቷል ይላሉ” አሉ ጋሽ ስዩም፡፡ (እሱን ይዘን እስከቀራንዮ እንጓዛለን ነው አባባላቸው)
☞ እኔ ምን ማርጀት ብቻ አፍጃጅቷል እንጂ አልኩ፡፡ አፍጃጀ ማለት፣ አንድ ሰው ከማርጀት አልፎ እንደ ህፃን ልጅ “ጭቃ ማቡካት” የሚያሰሰኘው ዕድሜ ላይ ደረሰ ማለት ነው፡፡ 😀
.
“የመንግሥታችንን ህዝባዊ ልማታዊ ስርዓት መጠበቅ አለብን” አሉ፡፡ (እንዴት ነው ሚጠብቁት?) “የዚህ ስርዓት ተጠቃሚ በሆኑ ምሁራን መጠቀምና ተጠቃሚነታቸውን እንዲገልፁ ማድረግ ይኖርብናል” አሉ፡፡
.
እኔ ☞ ስለዚህ “የስርዓቱ ተጠቃሚዎች ብቻ የሚመሰክሩለት ከሆነ፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ሕዝባዊ አይደለም ማለት ነው፡ አልኩ፡፡
.
በነገራችን ላይ አንዳንዶቹ አባባሎቻቸው ግራ የሚያጋቡ ናቸው፡፡ ለምሳሌ፦
“ሚዲያ የስነ አዕምሮ ጦርነት በሕዝባችን ላይ የከፈተበት ወቅት ነው”
“ደርግ ተመልሶ እንዲያንሰራራ የሚሰራ ያለ ይመስላል”
“ራሳችን ታግለን ባመጣነው ድል፣ ድሎቻችንን ሊቀማን የሚችል ኃይል እየገጠመን ነው” ወዘተረፈ የሚሉ፡፡ ስላች የገቡ እንዲህ ዓይነት አባባሎች”ጥልቅ” ትንተና ስለሚፈልጉ በደምሳሳው “ዘ ይገርም” ብዬ ነው ያለፍኳቸው፡፡
.
በመጨረሻ ግን ለ “ብአዴን” ነው ያዘንኩት፡፡
ብአዴን “ጥርስ ውስጥ የገባ” ድርጅት መስሎ ነው የታየኝ፡፡ አንድም በአጋር ድርጅቶቹ፣ አንድም በተቃዋሚዎች ጥርስ ውስጥ፡፡
በእርግጥም ብአዴን ቀብሩ ቅርብ ነው። እነ ስዩም ከማስፈራራት ወደ ጥናታዊ ዝብዛብ መንሸራተት መቻላቸው በራሱ ለውጥ ነው።
ማእበሉ እስኪወስዳቸው ድመትነታቸውን ሳያምኑ አንበሳ ነን ብለው ይንጎማለሉ። ባቡሩ ያረጁ ያፈጁትን እያንጠባጠበ ነው እየተጓዘ ያለው።
 ግራ እንደገባቸው አብዮታዊ ምናምናቸውን ታቅፈው ይሞታሉ።
ያረጀ ውሻን ትሪክ ማስተማር አይቻልም። ስለዚህ አንፍረድባቸው። መለስን ማደንቀው ትልቅ ለመሆን በትንንሽ ተከቦ እሱ ሲሞት መሞት የጀመሩ ይህው እስከዛሬ ወደ መቃብራቸው እያዘገሙ ነው። ሌላ የመለስ ውለታ በግዜ መሞቱ ነው። ፈጣሪ እሱን ቀጨልን እኛ እራእይና ቅዠቱን መቅበር አያቅተንም።
Filed in: Amharic