እና ምን ይጠበስ ? የ…
አንዳርጋቸው ከ15 አመታት በፊት በፃፈው “ነፃነትን የማያውቁ ነፃ አውጭዎች ላይ……
” ዘሬ ከመንዝና ተጉለት አማራ የሚጎተተውን ያክል ከአዲአ ኦሮሞ ዘሬ ይመዘዛል። ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ብሄር ማለት ዘር ስለሆነ እኔ ብሄር የሚባል የለኝም ።ኢትዮጵያዊ ነኝ ” ብሎ ደምድሞ የማንነቱን ጉዳይ ከጨረሰው አስርተ አመታት ካለፉ በኋላ አንድ የፈረደባት እህቱ የፃፈችውን ደብዳቤ በስክሪን ሹት እያቀረቡ ” አንዳርጋቸው ኦሮሞ ነው ፣ ገለመሌ “በሚል እየተከራከሩ መለፋደድ ደምበኛ ቅጥቅጥ መሀይም መሆን ነው።
Afterall እዚያ ደብዳቤ ላይ ያለው የሁለት አያቶቹ ስም ብቻ ነው ። አንድ ሰው 4 አያቶች እንዳለው የማያውቁ የቀለም ሽፍቶች ያስቁኛልም ያሳቅቁኛልም። 🙂
…
አንዳርጋቸው ስለብሄር ያለውን አመለካከት ለማወቅ ከጥራዝነጠቅነት ወጥቶ መፅሀፉን ማንበብ ነው። የአንዲን መፅሀፍ ያነበበ ሰው ታላቁን ፈላስፋ ዲዮጋንን ያስታውሳል።
በአንድ ወቅት ታላቁ እስክንድር በሜቄዶኒያ ጎዳና በሰረገላ ታጅቦ ሲያልፍ ዲዮጋንን መሬት ሲቆፍር ይመለከተዋል። ታላቁ እስክንድር ወደ ዲዮጋን ጠጋ በማለት
…
” ድዮጋን ሆይ ምን ትቆፍራለህ ? ” ብሎ ይጠይቀዋል።
…
ዲዮጋንም ” ንጉስ እስክንድር ሆይ የአባቶችህን የነገስታትን አጥንት እየፈለኩኝ ነበር ነገር ግን ከባሮቻቸው አጥንት ለይቶ ማወቅ ተሳነኝ ። እስኪ አንተ መለየት ከቻልክ መርጠህ ውሰደው! ” በማለት የአፅም መአት ዘርግፎለት አሹፎበት ሄደ ።
በቃ አንዳርጋቸው በዘር ላይ ያለው አስተሳሰብ ይሄው ነው።
…
እኔ ቬሮኒካ መላኩ አማራ ነኝ ። በብሄር አምናለሁ ። አማራ በብሄሩር መደራጀቱን ማመን ብቻ ሳይሆን ለስኬታማነቱ 24 ሰአታት እፅፋለሁ። ነገር ግን ይሄ የእኔ እምነት አንዳርጋቸውን የመሰለ Global standard የሆነውን የፖለቲካ ሰው እንዳላደንቅ አያግደኝም ።
አንዳርጋቸው አማራ ሆነ ኦሮሞ ወይም ኮንሶ ሆነ አኙዋክ አይበርደኝም ኢትዮጵያዊነቱ ግን ያሞቀኛል።
…
ለማንኛውም የሆላንድ ፈረንጆች ለእስክንድር ነጋ ተሰብስበው ሲዘፍኑለት የነበረው እስክንድር ብሄሩ ሆላንዳዊ ስለሆነ ወይም ሆላንዶች አማራዎች ስለሆኑ አይደለም። ይልቁንስ የነፃነት ታጋዮችና አንግበው የሚያነሱት ጥያቄ ግሎባልና ሁሉንም የሰው ልጅ የሚመለከት ስለሆነ ነው።
ለማንኛውም አንዳርጋቸው ፅጌ የእኛ የአማሮቹም አይደለም የኦሮሞዎቹም አይደለም የኢትዮጵያ ብቻ ነው።