>

ከመጋረጃዉ በስተጀርባ (behind the curtain)  (አቤል ዮሴፍ)

 ጠቅላይ ሚንስተር አብይ የሚያደርገውን ሳላደንቅ አላልፍም የሚል አረፍተ ነገር በብዙዎች እየተስተጋባ ነዉ።
በርግጥ ላይ ላዩን ተመልክቶ ከመጋረጃዉ በተጀርባዉ (behind the curtain) መመልከት ላቃተዉ ነገሩ፤ ጥሩና ወደ መሰረታዊ ለዉጥም እያመራን ይመስላል።
ችግሩ የሚመጣዉ ከመጋረጃዉ በስተጀርባ ያለውን ገላልጠን ስንመለከትና በጥላቻና በግፍ የገዘፈውን የሉሲፈርን ታናሽ ወንድም ወያኔን ስንምለከት ነዉ።
ወያኔ፤ ምንም እንኳን ኢህአደግ የሚል ካባ ደርቦ ቢንቀሳቀስም፤ ሞተሩና የተንኮሉ አባት ወያኔ ነው፤ ሌሎች እንደመኪና ቀለም ሊቀያይራቸው የሚችሉ፤ ወይም ተጎታች ናቸው።
ይሁንና ወያኔ ከህዝብ መነጠሉና ሃገሪቱን እየዘረፈ ባዶ ማስቀረቱ፤ በደጋፊዎቹ በ አሜሪካኖችና በእንግሊዞች እንዲሁም በሌሎች ሃገሮች አልተደገፈም፤ ምንም ወያኔ ደንቆሮ ሽፍታ ቢሆንም፤ ምእራባዉያን ከልቅ ያጣ ዘረፋና በህዝብ ላይ የሚደርስ በደል፤ ህዝባዊ አመጽ እንደሚያስከትል ያዉቃሉ፤ ለዛም ነዉ፤ ደንቆሮዉና፤ በጭንቅላቱ ሳይሆን እንደ አዉሬ በሆዳቸው የሚያስቡትን የትግራይ ናዚዎች ሰብሰበው፤ ማስጠንቀቂያ መስተት ብቻ ሳይሆን፤ ነገሮችን መስተካከል እንዳለባቸው ማእቀብ አድርገዉባቸዋል።
ለዛም ነው የጨነቀዉ የትግሬ ናዚዎች፤ ሳይወድ በግዱ በምእራባዉያን የቀረበበትን ተጽእኖ ተቀብሎ፤ አብይን ጠቃላይ ሚኒስተር ያደርገ።
ምእራባዉያንም ይህን ያደርጉበት ምክንያት ያለዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ፤ ጠንክሮ የቤት ባሪያቸውን ወያኔን ፈንግሎ፤ ሌላ ሊያመታ ይችላል ከሚል፤ በክፉ ቀን የደረሰላቸውን የቤት ባሪያቸውን ከማዳን አንጻር ነዉ እንጅ፤ ለኢትዮጵያ ህዝብም አስበዉ አይደለም።
አሁንም ኢትዮጵያ ዉስጥ እየተደረገ ያለው፤ ወያኔን ከህዝባዊ አመጽ ከማዳንና፤ የትግራይ ሽፍቶች በገደሉት፤ በሰሩት ግፍና በዘረፉት ንብረት ተጠያቂ እንዳይሆኑ፤ ብሎም ከሃገሪቱ ስልጣንም ሳይወርዱ፤ ህዝብን አጭበርብሮና ለዉጥ እንደመጣ ተደርጎ እንዲቀጥል፤ በምእራባዉያን የተቀነባበረ ሴራ ነዉ።
ዋናዉ ቁም ነገሩ፤ ጠቅላይ ሚንስተር አብይ የሚያደርጋቸው ድርጊቶች ጥሩ ቢሆኑም፤ ነገሮች እንዲደርጉ ቀደም ተብሎ በ ምእራባዉያን የተወሰነና፤ የትግሬ ናዚዎችም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶትና ሌላ አማራጭ ስለሌለዉ የተቀበለዉ ነው።
ያ ማለት ግን የትግሬ ሽፍታ አሁንም ቢሆን ሃይሉ ያልተነካ እንደሆነ እንዲታወቅና፤ በተለይም በ አማራ ህዝብ ላይ ያለዉ የግፍ ተግባር በተጠናክረ ነገር ግን መልኩን በቀየረ ሁኔታ እያካሄደ እንደሆነ መረዳት ይሻል።
Filed in: Amharic