>

የዶ/ር አብይና የአቶ አንዳርጋቸው መገናኘት በስጋትና ጥርጣሬ የታጀበውን ፖለቲካ ለማርገብ የታለመ ነው!!! (ኢ/ር ይልቃል ጌትነት)

እንደ አዲሱ ግልብጥ በዶ/ር አብይ በኩል የኢህአዴግ ደጋፊ መንጋ አተያይ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቀላል ቢሆን ኑሮ እኔም የኢህአዴግ ደጋፊ እሆን ነበር!!!
የጠ/ሚ ዶ/ር አብይንና የአቶ አንዳርጋቸውን መገናኘ በተመለከተ ደስታ ይሁን ተስፋ ባላውቅም ወሬው በጣም ደምቁዋል። የኢህአዴግን የድርጅት ባህሪ ለሚገነዘብ ሰው ኢህአዴግ በ17ቱ ቀናት ስብሰባ የወሰናቸውን ውሳኔዎች ከመፈፀም የተለየ ዶ/ር አብይ ጠ/ሚ በመሆናቸው ችግሩን የሚመጥን የተወሰደ ወሳኝ የፖለቲካ እርምጃ አላየሁም። የካቢኔ ሹመት በተመለከተ ከዶ/ር አብይ የአቶ ኃይለማሪያም ሳይሻል አይቀርም። የሰሞኑን የመቀሌውን ግንቦት 20ን በተመለከተ የተደረገውን የፓናል ውይይት ለተመለከተ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ሌላኛውን ገፅታ በደንብ ያሳያል። ብዙ ወደ ዝርዝር ሳልገባ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ብዙ ውጥንቅጥ ያለበትና ትልቅና ረጅም ስራ የሚጠይቅ ነው። የዶ/ር አብይና የአቶ አንዳርጋቸው መገናኘትም በስጋትና ጥርጣሬ የታጀበውን ፖለቲካ ለማርገብ በተለይምለኢህአዴግ  በዶ/ር አብይ በኩል  ትልቅ የህዝብ ግንኙነት ስራ ከመሆን አልፎ ለተጨባጭ የፖለቲካ ችግሮች ሃቀኛ መፍትሔ በመስጠት በኩል የኢህአዴግን አጠቃላይ የድርጅት ባህሪና የውሳኔ አሰጣጥ አያይዘን ስናየው ገና ብዙ ስራ የሚጠይቀንና ትግላችንንም በአትኩሮት ከመስራት አልፎ ተስፋ እንድናደርግ የሚያደርገን ምንም አይነት ተጨባጭ ነገር የለም።መከራን እየተቀበሉ ተስፋን እየተመገቡ ስቃይን መግፋት የሃገራችን የጋራ ስነ ልቦና ከሆነ አርባ አመት አለፈው።
Filed in: Amharic