>

አፋጣኝ ምላሽ የሚሹ ወቅታዊ ጥያቄዎች!!! (ሚኪ አምሃራ)

” ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ እስረኞችን በማስፈታት በኩል እየሄዱበት ያለዉ አካሄድ ጥሩ የሚባልና የሚበረታታ ድርጊት ነዉ፡፡ በሚቀጥሉት ጊዚያቶች የኢኮኖሚ፤ የህገመንግስትና እና ሌሎች ተቋማዊ ሪፎሞች ጨምሮ ወይም የፖሊሲ አቅጣጫወችን ይዘዉ እንደሚመጡ ተሰፍ እናደርጋለን፡፡
ከዚህ ዉጪ እኔ ፕረሰናሊ ጠቅላይ ሚኒስትሩን በሶስት አስቸኳይ ጉዳዮች ላይ በግሉ intervene እንዲያደርግ እፈልጋለዉ
1. ከኦሮሚያ ተፈናቅለዉ ራያ እና ሌሎች አካባቢዎች ያለምንም እርዳታ የተበተኑ አማሮች፡፡ እንዲሁም ከቤኒሻንጉል ተፈናቅለዉ ባሀርዳር ላይ ቤተክርስቲያን ተጠልለዉ የሚገኙትን አማሮች ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግሉ ኢንትረቬን እንዲያደርግ እና መፍትሄ እንዲሰጥ፡፡ ከቤኒሻንጉል የተፈናቀሉትን እንዲሁም የመንግስት አካል ደብዳቤ ጽፎ እንዲወጡ ማዘዙን ጋምቤላ ላይ ባደረጉት ንግግር አንስተዋል፡፡ እርስወ በግልዎ ይሄን ያስፈጸመ የመንግስት አካል ተጣርቶ እርምጃ ተወስዶበት ይነገረኝ ብለዉ በሚዲያ ማስተላለፍ አለብወት፡፡ አለበለዚያ በሚቀጥሉት ጊዚያቶች የመፈናቀል ጉዳይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል ፍንጭ ያየንበት እና እየሆነ ያለ ነዉ፡፡ ይህ ደግሞ አገርን እና ህዝብን አደጋ ላይ ይጥላል፡፡ስለዚህም በግልዎ ጊዜ ሰተዉት ከኦሮሚም ከቤኒሻንጉልም የተፈናቀሉ ዜጎች ባስቸኳይ ሁሉ ነገር ተሟልቶላቸዉ እንዲመለሱ እና በአፈናቃዮች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ ማስተላለፈ አለበወት፡፡
2. ለእስረኞች mass amnesty እንዲሰጡ፡፡ አሁን ባብዛኛዉ የምናዉቃቸዉ እና ታዋቂ የሆኑት ሰወች እየተፈቱ ነዉ፡፡ ነገር ግን ብዙ የማናዉቃቸዉ በዉሃ ቀጠነ የታሰሩ ብዙ ሺህ እስረኞች አሉ፡፡ እንግዲህ በሽወች የሚቆጠር አማራ የታሰረዉ በግንቦት7 ስም ነዉ፡፡ እነ ጌቴ አስራደን የመሳሰሉ የጤና ባለሙያዎ፤አስተማሪዎች እና ተመራማሪዎች የለምንም ጥፋት ነዉ የታሰሩት፡፡ የዚህ ድርጅት አላፊዎች እንደሚታወቀዉ ክሳቸዉ ተነስቷል አንዳርጋቸዉም ተፈቷል፡፡ ስለዚህም በሚቀጥለዉ ሳምንት ቀሪ እስረኞች ይፈታሉ መባሉን ብንሰማም አሁንም ብዙ አስረኞ ያለ አስተዋሽ እዛዉ ላይ ሊቀሩ ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ባጠቃላይ እንደ ሀገር መሪ ወይ እርስወ ወይም ፕሬዝደንቱ mass amnesty በመፍቀድ ሳይንጠባጠቡ የሚወጡበት መንግድ እንዲመቻች፡፡
3. ብዙ የአማራ ልጆች በድብቅ እስር ቤቶች ነዉ የሚገኙት፡፡ ለምሳሌ መቀሌ ባዶ ስድስት፤ ኦጋዴን፤ አፋር፤ ቤኒሻንጉል እና እንዲሁም የህወሃት ስዉር እስር ቤቶች በአማራ ክልል ዉስጥ ለምሳሌ ጎንደር ማዞሪያ ሰፈር ዉስጥ ያለ የጅምላ እስር ቤት እና አዘዞ ካምፕ ዉስጥ እስከ አንድ ሽህ እስረኛ የሚያስተናግደዉ የመሬት ዉስጥ እስር ቤት፡፡ ባህርዳር መኮድ የሚባለዉ ገጠር መንገድ አካባቢ የሚገኘዉ እስከ 1500 የሚይዘዉ የመሬት ዉስጥ እስር ቤት፤ እና ወልደያ ጎንደር በር የሚባል አካበባ ከአንድ ፎቅ ስር ዉስጥ እስከ 250 ሰዉ የሚይዝ እስር ቤቶች አሉ፡፡ እኒህ እንዲፈተሹ ትእዛዝ ቢያስተላልፉ፡፡ በተለይ መቀሌ የዛሬ 24 አመት ጀምረዉ የታሰሩ ብዙ የአማራ ሰወች አሉ፡፡ አሁን 60 እና 70 አመት የሆናቸዉ እዛዉ እስር ቤት፡፡ ስለዚህም የትግራይ ክልል መንግስት እነዚህን እና ከወልቃይት ራያ ጥያቄወች ጋር ተያይዞ ያሰራቸዉን ሰወች እንዲለቃቸዉ መመሪያ ቢያስተላልፉ፡፡ከዚህም በተረፈ በብጥብጥና ሁከት ብሎ ብአዴን በክልሉ እስር ቤቶች ያሰራቸዉ 21 ሺህ እስረኞን እነንዲፈታ ጫና እንዲያደርጉ፡፡    እነዚህ እጅግ ጊዜ የማይሰጣቸዉ ጉዳዮች ስለሆኑ እጅ ጥያቂወቻችን ብዙ ናቸዉ ከወልቃየት ጉዳይ እስከ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዉክልና ድረስ አለን፡፡
Filed in: Amharic