>
5:13 pm - Saturday April 19, 6786

የውስጥ ፍትጊያው ተባብሶ ቀጥሏል ፤ ህወሀቶቹ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል!!! (ለማ አባቦራ)

ትግሉ ተፋፍሟል ህወሀት ባለስልጣናት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል በዶክተር አብይ ወደ ስልጣን መምጣትም ሆነ ከዚያ ወዲህ እየተደረገ ያለው ጉዞ አልጋ ባልጋ አይደለም።
ህወሀቶች በድርጅታዊ አሰራር በዶክተር አብይና ለማ ቡድን ላይ ጨዋታ ሊጫወቱ ከመሞከር ጀምረው በተወሰኑ የመከላከያና የደህንነት ባለስልጣኖች አማካኝነት ውደ ግልበጣ እስከሚደርስ ውይይት አድርገው እንደነበረና እያንዳንዱ ሴራ ግን ደረጃ በደረጃ እየተፍረካከስ እንደመጣ ምንጮች ይገልጣሉ።
ዶክተር አብይ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሊሆኑ ሁለት ሳምንት ያክል ሲቀር የህወሀት ባለስልጣኖች እጅግ ደማቸው ፈልቶ የፈለገው ይምጣ ብለው እርምጃ ለመውሰድ አስበው እንደነበረና ይህንን ያወቁት የምእራብ መንግስታት ተወካዮች በቀጥታ የህወሀትን ቁልፍ ሰዎችና በተለይም የመከላከያና ደህንነት ባለስልጣኖችን በማነጋገር ከዚህ እርምጃ እንዲቆጠቡ ስላሳሰቧቸው የህወሀት ሰዎችም ባንድ ልብ እርምጃ መውሰድ እንዳልቻሉ እያደርም እየተፍረከረኩ እንደሄዱ ውስጥ አዋቂ የምእራብ ምንጮች ይጠቆማሉ።
እነዚህ ምንጮች እንደሚሉት ህወሀት እጅግ የተጠላበት ደረጃ ላይ ስለደረሰ ሀገሪቱን አረጋግቶ ለመግዛት በፍጹም እንደማይችል በራሳቸው መረጃ ሲያረጋግጡ ነው የታላላቆቹ መንግስታት ሰዎች ህወሀቶችን ሁኔታውን ከማባባስ እንዲቆጠቡ ያሳሰቧቸው።
የነ አባይ ጸሀየና አቦይ ስብሀት ጉዳይም ተመሳሳይ መንገድን በመከተል አርፈው በጡረታ እንዲቀጥሉ በምክር መሰል ማሰጠንቀቂያ ከሚፈሩት መንግስታት እንደተነገራቸው ምንጩ አሳውቋል።
እንደ መንጩ ከሆነ የህወሀት ሰዎች በዚህ ምክናያትም ነው ያዲስ አበባውን
ስልጣን እየለቀቁ ወደ መቀሌ መሰባሰብ የቀጠሉት። ለዚህም ነው እጅግ የማይወዱት የነ አንዳርጋቸውና ኮሎኔል ደመቀ መፈታትን እያዩ ምንም ማድረግ ያልቻሉት።
የህዝብ ግፊት ከሚያሳድረው ተጽእኖ በተጨማሪ “እነዚሁ መንግስታት እስካሁን በታየው የነ ዶክተር አብይ እርምጃ የተደሰቱ ሲሆን ፈጠን ብለው መሻሻል ያለበቸውን ህግጋት እንዲያሻሽሉ፣ ፖለቲካ ምሀዳሩን እንዲያሰፉ ወዘተ በግል በየአምባሳደሮቹ በጋራ ደግሞ በእርዳታ ሰጭዎች ስብስብ በኩል ግፊ ማድረጋቸው ቀጥሏል።
ምንጩ እንደሚለው ሁኔታው አሁንም ያልረጋ ነው ( ቮላታይል)። ህወሀቶች ለማንሰራራት መሞከራቸው የሚጠበቅ ነው።
የኔ አመለካከት ዶክተር አብይ ፈጠን ያለ እርምጃ መውስድ ከቀጠሉ፣ መዋቅሮቹ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማድረጉን ካጣደፉ፣ የህዝብንም መሰረታዊ ጥያቄ ፈጠን ብለው መመለስ ከቻሉ፣ ህወሀትና መዋቅሩ ብዙም ላያሰጋ ይችላል።
Filed in: Amharic