>

የአቶ በቀለ ገርባ ጥፋታቸው ምንድን ነው? (ኢ/ር ይልቃል ጌትነት)

የሰሞኑን ጨምሮ አቶ በቀለ ይህንን ተናገሩ እየተባለ ነቃፊዎቻቸው (ልብ በሉ ደጋፊዎቻቸው አላልኩም) የስድብ ናዳ ያወርዱባቸዋል። በእኔ እምነት ይህ ትክክል አይመስለኝም።እሳቸው ላመኑበትና ብዙ መስዋዕትነት ለከፈሉለት አላማ ሳይሸማቀቁ በድፍረት ተናግረዋል። በተናገሯቸው ነገሮችም ከደጋፊዎቻቸው አድናቆትና አክብሮት እንጅ የጎላ ትችት ሲቀርብባቸው አላየሁም። የነቃፊዎቻቸው መበሳጨት ምክንያቱ አልገባኝም። በእኔ እምነት በቀለ ገርባ የሚታገሉት ለደጋፊዎቻቸውና ለአላማቸው እንጅ ለነቃፊዎቻቸውና ለተችዎቻቸው አይደለም። በነቃፊዎቻቸው ጫጫታም እንደሚደሰቱ አልጠራጠርም። ምክንያቱም አቶ በቀለ የሚታገሉለትን አላማ እና የሚታገሉትን አመለካከት በግልፅ ለይተው ያውቃሉና። በመሆኑም በእኔ አስተያየት አቶ በቀለ ከቆሙለት አመለካከት አንፃር የተሳሳቱ አይመስለኝም። ስህተት ካለም በተናገሩት ንግግር እሳቸውን በሚነቅፉ ሰዎች በኩል ነው።ከፓርቲያቸውም ቢሆን የተናገሩት ነገር የፓርቲውን አቋም አያንፀባርቅም ሲባል ሰምቸ አላውቅም።
Filed in: Amharic