ሽማግሌው ስብሃት፣
” ህውሓት የመገንጠል ጥያቄ በፕሮግራሙ አሰፈረ። ይሄን የመገንጠል ጥያቄ ለማስረዳት ሲንቀሳቀስ ከፍተኛ ተቃውሞ ደረሰበት” በማለት ይገልጣል።
ህውሓት መገንጠልን በሚሰብከው ፕሮግራሙ ላይ አጋጥሞት የነበረውን ተቃውሞ ሲያብራራ ደግሞ የሚከተለውን ይላል፣
#1•1• “የመጀመሪያው የተቃወመውና ያልተቀበለው የትግራይ ሕዝብ ነው። የትግራይ ህዝብ ” እኛ የኢትዮጲያ ንጉስ ነው የምናውቀው ፣ መገንጠል አንቀበልም አለን”።
#1•2• “ቀጥለው ያልተቀበሉን ኢዲዩ፣ ኢህአፓ፣ መኢሶን ናቸው። ከእነዚህ ጋር በመገንጠል ጥያቄ ላይ የነበረን ትግል እልህ አስጨራሽ ነበር።”
#1•3• “ቀጥሎ የተቃወመን ሻዕቢያ ነበር። ሻዕቢያ የኢትዮጲያ አንድነት መጠበቅ አለበት፣ መገንጠል የሚለው ትክክል አይደለም ብሎ ተከራከረን።”
#1•4• ” ግብጾችም አልተቀበሉንም። ዲፕሎማቲካሊ የኢትዮጲያን አንድነት መገነጣጠል የሚለው ያሰድበናል አሉ።”
#1•5• ” ምእራባውያንም አልተቀበሉንም። አልፈው ሄደው ሻዕቢያን ኢትዮጲያን ከሚገነጣጥል ጋር ትብብር አታድርግ ብለው አስጠነቀቁት።”
#1•6• ” የመገንጠል ጥያቄ የተቀበለን የኢትዮጲያ ህዝብ ነው። በተለይም እኛ የምንማርካቸው ሙርከኞች ( አነ አባዱላ፣ ኩማ ይመስሉኛል) ዘንድ የመገንጠል ጥያቄ ከፍተኛ ተቀባይነት ነበረው።”
” አሮጊቷ ኢትዮጲያ!” በስብሃት ነጋ አይን፣
# 1• ” አንበጣ በሊታ ይሉን ነበር”
#2• ” ባርያ እንባል ነበር!”
#3• ” ሽርጥ ለባሽ እንባል ነበር!”
#4• “የኢትዮጲያ ብሔር ብሔረሰቦች አይጥና ድመት ነበሩ! እርስ በራስ ሲጨራረሱ ነበር!”
#5• ” በአለም ላይ never again ማለት ያለበት ካለ የኢትዮጲያ ህዝብ ነው።”
#5• ” ኢትዮጲያን በትክክል የተረዳትና ያወቃት ህውሓት ብቻ ነው።”
እንደ መውጫ፣
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ እግዜር ይይልህ! እንደዚህ ጨርቃቸውን አስጥለህ ታሳብዳቸዋለህ? ። በዚህ አካሄድ በቀጣይ ቀናት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጲያን ኢኮኖሚ በቁጥር አንድ ስለ ተቆጣጠረው ” ኤፈርት” የቁጥጥር ማስፈፀሚያ እቅድ ( ፍኖተ ካርታ ጨምሮ) መዘርዘር ሲጀምሩ ህውሓቶች ሸርተቴ በሸርተቴ ይሆናሉ። ማነህ በረኸት!ህላዌ! አዲሱ! ዳይፐር መያዝና ማቀበሉን ( ለአንዳንዶቹም መቀየሩን) እንዳትረሱ!