>
5:31 pm - Thursday November 13, 6836

"በእኛ መስዕዋትነት ሌሎች ተጠቃሚ ሆነዋል" ማለታቸው ከቅንነት ይልቅ ምቀኝነት የሚታይበት ነው!!! (ስዩም ተሾመ)

አቦ #በቀለ_ገረባ “እኛ በከፈልነው መስዕዋት ሌሎች ተጠቃሚ ሆነዋል” በማለት በኦሮምኛ የተናገሩትን #የአማርኛ ትርጉም ያድምጡ! እርግጥ ነው፣ ከዚህ ጨቋኝ ስርዓት ነፃ ለመውጣት የኦሮሞ ህዝብ ሆነ ራሳቸው አቦ በቀለ ከፍተኛ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ስለዚህ “በዚህ ምክንያት የታሰሩ ሰዎች መፈታት አለባቸው” የሚለው ትክክል ነው፡፡  ይሁን እንጂ፣ አንደኛ፦ ይህን ስርዓት ለማስወገድ ከጋምቤላ እስከ ጎንደር ህዝብ ከፍተኛ መስዕዋት ከፍለዋል፡፡ ሁለተኛ፦ በቀለ ገረባን ጨምሮ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ የሌሎች ብሔር ተወላጆች ከኦሮሞዎች ባልተናነሰ ዋጋ ከፍለዋል፡፡ ሶስተኛ፦ ኦቦ በቀለ ገረባ ያደረጉት ትግልና የከፈሉት መስዕዋት ከእነ #አንዳርጋቸው_ፅጌ፣ #ሌንጮ_ለታ፣ ዶ/ር #ብርሃኑ_ነጋ ከመሣሠሉ አንጋፋ ታጋዮች ጋር የሚነፃፀር አይደለም፡፡ ስለዚህ ኦቦ በቀለ ገረባ “እኛ በከፈልነው መስዕዋት ሌሎች ተጠቃሚ ሆነዋል” ማለታቸው ፍፁም ያልተጠበቀና የተሳሳተ፣ ከቅንነት ይልቅ ምቀኝነት የሚመስል ነው፡፡ በአጠቃላይ እንዲህ ያለ እሳቤና አመለካከት በፍፁም ከእሳቸው አይጠበቅም፡፡ አሁን እየተሰማኝ ያለው ስሜት “ምነው ይሄ ንግግር #ውሸት በሆነ!” የሚል ነው!!

Filed in: Amharic