>

ባድመ ባድመ ይሉናል ከ17 በላይ ግዛቶች ናቸው ተላልፈው የተሰጡት!!! (አርአያ ተስፋ ማርያም)

” የመከላከያ ሰራዊት በደምና አጥንቱ ያስከበረውን መሬት መለስ ወይም ስዩም ሊሰጡ አይችሉም። እኛ በመሬታችን ላይ አለን። ውሳኔ ያሉትም 4 ኪሎ መለስ ቢሮ አለ። ከቤታችሁ ውጡ ሲሉን እጃችንን አጣምረን አንመለከትም። ሻወር ስትወስድ ሳሙና አዳልጦህ ልትሞት ትሽላለህ። ለአገርህ በክብር መሞትን የመስለ ነገር የለም!..  ሉአላዊ ግዛቷን በጀግኖች ልጆቿ መስዋእትነት አስከበራ..”መሬቶቼን ውሰዱ” ስትል አሳልፋ የሰጠች አገር ኢትዮጵያ ናት!” በ1996 ዓ.ም የኢሮብና ባድመ ነዋሪዎች የተናገሩት። ሁሉም ሊያውቀው የሚገባው ባድመን ጨምሮ ከ20 በላይ ግዛቶች ናቸው ተላልፈው ይሰጡ የሚባለው። ኢሮብ፣ ሸላሎ፣ ሸሸቢት፣ ባድመ፣ ቦሎሞኮዳ…ወዘተ 17 ናቸው። (ቦሎሞኮዳ ጀግናው ምሩፅ ይፍጠር የተወለደባት ወረዳ ናት።)

በቅሎ  ፤ ቁኒናቀቁነቶ እና ዛላንበሣን ጨምሮ ኢሮብን በከፊል ። በምዕራብ በማስመሪያ የተሠመረ ይመሥል እስከሽራሮ ከተማ  ሁለት ኪሎሜትር እስኪቀረው ድረስ ነው  በዚህ ውስጥ በድመ  ፤ ገዛ ገረስላሴ  ፤ ገዛ አምሀራይ  ፤ ገመሀሎ  ፤  ሠምበል  ፤ ጓልገመሀሎ እና ገዛ ብሌን በጣም የሚታወቁ አካባቢወች በውሣኔው መሠረት ለኤርትራ የተወሠኑ አካባቢዎች ናቸው!  የሚያሣዝነው ወያኔ እያለ በኢትዮጵያ ላይ የውጭ ወረራ ቢያጋጥመን ማነው ከእንግዲህ በዚህ አካባቢ ሔዶ መሥዋትነት የመመከፍለው ብዬ ሣሥብ የህወሀት ወንጀል ጣሪያ ነክቶ እንኳን ዛሬም ደጋፊ መኖሩን ሣይ አዝናለሁ!  ደማችሁ ደመከልብ ሆኖ ነቀራችሁ ወንድሞቼ ነፍሳችሁን ይማርልኝ! 

Filed in: Amharic