>

አበበ ካሴ በጠና ታሟል!! (በኤርሚያስ ፀጋዬ)

ከቀናት በፊት ወንድሜ ዳንኤል ተስፋዬ የአበበ ካሴን በጠና መታመም ባለበት እስር ቤት ሄዶ በመጎብኘት አሳውቆን ነበር ዛሬ አበበን ለመጎብኘት ቃሊቲ ዞን 2 ተገኝቼ ነበር አበበ እጅግ በጣም ጠንካራ ታጋይ ነው ይንን ሁላ የመከራ ጥግ የደረሰበት አይመስልም ዛሬም ለኢትዮጵያ ህዝብ ሲል መሞት ምኑም አይደለም ይህንን ስል ግን አበበ ምን ይህል ስቃይ ላይ እንዳለ ለመግለፅ ቃላት ያጥራል ።
~አበበ ሁለቱ ኩላሊቶቹ ከድብደባ ብዛት መስራት እያቆሙ ነው!በዚ ሰዐት ለኛ ምንም የሆኑት መቀመጥም ሆነ መተኛት ለአበበ ስቃይ ናቸው የእግሩ ደምስሮች እየተቆጣጠሩ ወደላይኛው የሰውነቱ አካል እየወጣ ነው በክላሽ አፈሙዝ የተመታው ጭንቅላቱ በአፍንጫው በኩል ፈሳሽ እያወጣ ነው ይህ ሁላ ግፍ ሀገሬን ህዝቤን በማለቱ ነው።
አበበ ካሴ ይፈታ!!!  
Filed in: Amharic