>

የትግራይ ህዝብ "ህወሃት" የተባለው ጠላቱን ተፋልሞ የመደምሰስ ጊዜው አሁን ነው! (አብርሀ በላይ)

በትግራይ ስም ህወሃትን ተቆጣጥረው የኖሩት ሰዎች “የኤርትራ ደም” ያላቸው ብለን በቀላሉ የምናልፈው አይደለም። ብዙ ማስረጃዎች እንደሚመሰክሩት፣ በትግራይ ይሁን በተቀረው ኢትዮጵያ ተወልደው ያደጉ ትውልደ ኤርትራ እንዳው ኤርትራ ተወልደው ካደጉት ኤርትራውያን የበለጠ ጽንፈኛ የኤርትራ ብሄርተኞች (ultra Eritrean nationalists) ሁነው ኑረዋል፣ ለቆሙለት አላማም የኢትዮጵያን ህልውና እስከ ማናጋት ደርሰዋል።
ለምሳሌ ኢሳያስ አፈወርቂ በሱ ዙርያ የነበሩት የረዥም ጊዜ ጓዶቹን (G-15) የጦርነት ፖሊሲውን ስለተቹት ብቻ አስሮ በበሽታና በቶርቸር እንዲያልቁ አርጓቸዋል ። ሌሎቹም በጭካኔው ተማረው በብዛት አገር ጥለው ሄደዋል። አብዛኞቹ የጦር መኮንኖችም እየሸሹ ኢትዮጵያ ገብተው ይኖራሉ። ኢሳያስ ያለ ጓደኛ ብቻውን ስለቀረ ኤርትራውያን የኤንጂኔር አስገዶም “ንበይነይ ኮይነ አነ” (እኔ ብቻዬ ቀረሁ) የሚለውን ቆየት ያለ ዘፈን ዘፍነውለታል።
ታድያ ማን ነው የኢሳያስ ታማኝ ካልን ኢትዮጵያ ተወልደው ያደጉ ኤርትራውያን ናቸው። ከብዙ አብነቶች በጥቂቱ፤
1) አምባሳደር ግርማ አስመሮም – ደብረብርሃን ተወልዶ አድጎ፣ እንዳውም በአንድ ወቅት ለኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ተወጫች እንደነበር ይነገራል። ትግርኛ እናኳን በቅጡ መናገር የማይችለው ግርማ አስመሮም፣ የኢሳያስ እጅግ ታማኝ “ተወርዋሪ ዱላ” ነበር። አንዴ በአሜሪካ የኤርትራ አምባሳደር፣ ወይም በተባበሩት መንግስታት የኤርትራ አምባሳደር ሲሾመው፣ ኤርትራ የአፍሪካውያን ጉዳይ ስትፈልግ ደግሞ፣ ይኸው ግርማ ከአሜሪካ ተነስ ይለውና በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት አምባሳደር ሆኖ ሲሰራ እስከ እለተ ሙቱ ድረስ ይሰራ ነበር። እሱም ባቅሙ ኢትዮጵያን አዳክሞ ለመበተን ሳይታክት ታግሏል።
2) ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ – በጣልያን አገዛዝ ኤርትራውያን ከ4ኛ ክፍል በላይ መማር አይፈቀድላቸውም ነበር። አስመሮምም 4ኛ ክፍል እንደጨረሱ በ 1945 ወደ አ.አ. መጥተው የተፈሪ መኮንን የመጀመሪያ ተማሪ ሆኑ። አብሮዋቸው ከተማሩት ደግሞ ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ይገኙበታል። ኢትዮጵያ ለአስመሮም ፈረሱም፣ ሜዳውም ያውልህ ስትላቸው፣ በአንትሮፖሎጂ በኦሮሞ ህዝብ የገዳ ሥርአትን አጠኑ። ሻብያ ሲወረን፣ አስመሮም አሳድጋና አስተምራ ለክብር ያደረሰቻቸው ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ቀበቷቸውን ጠበቅ አርገው ተንቀሳቀሱ። ታች ወርደው የሻብያ ፕሮፓጋንዲስት ሆነው በርካታ ፀረ-ኢትዮጵያ ጽሁፎችን ሲፈበርኩ ኑረዋል። ሁሉም ዶግ አመድ ሆኑ እንጂ! መጨረሻም የተባበሩት መንግስታት ኤርትራን በሰብአዊ መብቶች ጥሰት ሲከሳት፣ የኢሳያስ ብትር የሸሹ ኤርትራውያን ስደተኞች የሰጡትን የምስክርነት ቃል አስመሮም ውሸት ነው በማለት ክሱን ለማክሸፍና ኢሳያስን ለማስደሰት ላይ ታች ብለው በርካታ ኤርትራውያንን አስቀይመው ቀርተዋል። ዛሬም ቢሆን በአክራሪ የኦሮሞ ቡድኖች መሃል በመገኘት በማር የተለወሰ ፀረ-ኢትዮጵያ አንድነት የሆነ ነግግር ያደርጋሉ።
3) ተስፋዬ ገ/አብ – ወዳጄ ተስፋዬን የማያውቀው ሰው የለም። ቢሾፍቱ ተወልዶ ያደገው ተስፋዬ ገ/አብ መለስ ዜናዊና በረከት ስምኦን የሰጡትን ኦሮሞንና አማራውን የማጋጨት ነጥቦችን በሰላ ብዕሩ ቀምሞ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ጊዜ ጠብቆ የሚፈነዳ “የቡርቃ ዝምታ” የተሰኘ ቦም የሰራ ሰው ነው። ቀጥሎም በርካታ መጻህፍት ሲደርስ፣ ተልእኳቸውም ኢትዮጵያን ማፈራረስ፣ ህዝቧም እርስ በርሱ ማናቆር ነው። ተስፋዬ ለሻብያ ደህንነት እንደሚሰራ፣ በጁ የተገኙ ዶክሜንቶች ደግሞ በኢትዮጵያውያን መሃል በንዚን እያርከፈከፈ የእርስ በርስ ግጭትን ለመጫር ያለሙ ነበር።
4) መለስ ዜናዊ – አድዋ ተወልዶ ያደገው መለስ፣ የዊንጌት ተማሪ እያለ ራሱን የኤርትራ ተወላጅ እንጂ የትግራይ ሰው አርጎ ታይቶም፣ ተሰምቶም አይታወቅም። የባንዳ ልጅ እየተባለ እየተናቀ ያደገው መለስ፣ ሻብያን ከመቀላቀል ይበልጥ አትራፊ ሆኖ ያገኘው እሱን መሰል ጠላቶች በአመራር ላይ ያሉበትን “ህወሃት” ነው።
ከሚጠቀሱ ሥራዎቹ በደደቢት የፖለቲካ ት/ቤት ከፍቶ ምንም የማያውቀውን የትግራይ ወጣት፣ በፀረ-ኢትዮጵያ ፕሮፓጋንዳ አስክሮ፣ የኤርትራ ነፃ አውጪ አርጎ በገፍ እያስመረቀ በሳሄል በረሃ የሻብያ ጠባቂ እና የደርግ ጥይት አብራጅ ማድረግ ነበር። ለዚህም እንዲረዳው “የኤርትራ ትግል ከየት ወዴት?” እና ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድሃኔን ሙልጭ አድርጎ የሚሰድበውን “የኤርትራ ትግል ቁልቁል አፉ አይደፋም” የሚል የስድብ መድበል ጽፎ አሰራጭቷል። እንደ የትምህርት መማሪያም ለአመታት ታጋዩ በመጽሃፉ ተጠምቆበታል።
መለስ ትግራዮችን አሞኝቶ፣ ይህ ቃል ይደገም፣ ትግራዮችን አደንዝዞ፣ ቀጥቅጦና አጃጅሎ፣ የገዛ አገራቸው ጠላት ሆነው ለኤርትራ ነፃነት እስከዛሬ ድረስ እንዲዋጉላት ያደረገ አክራሪ የኤርትራ መሪ ነበር። መለስ ቁሜለታለሁ ያለውን የትግራይ ወያኔ ትግል “አንዲት ጦማር” ሳያቀርብ ለኤርትራ ነፃነት ግን አስፈልጊውን – ኢትዮጵያን እየገደለም ቢሆን – ሁሉ አድርጓል።
በጦርነቱ ጊዜም አራት ኪሎ ሆኖ፣ “ያይናቸው ቀለም ካላማረን [ኤርትራውያንን] እናባርራለን” እያለ እየቀለደ፣ ጊዜ ገዝቶ ግን የኢትዮጵያ አንፀባራቂ ወታደራዊ ድልን ያከሸፈ፣ ኢትዮጵያን በዘር ከፋፍሎ ለዘር እልቂት ደግሞ ደጋግሞ የጋበዘ፣ አርቲፊሻል የኑሮ ውድነት ፈጥሮ ኢትዮጵያዊው በማያባራ ድህነት እንዲጠቁ ያደረገ፣ የትግራይ፣ የአማራው፣ የኦሮሞ፣ በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ደመኛ ጠላት ነው።
የትግራይ ህዝብ የመለስ ድርጅት የሆነው ህወሃትን በትግሉ ማፍረስ አለበት። የመለስ ጠላትነት ለምናውቅ፣ መለስ እንዴት የኢትዮጵያ ጦር ኃይሎች ድልን አክሽፎ፣ ኢሳያስ አፈወርቂን ከወደቀበት አፈር አንስቶ፣ ኢትዮጵያን ለመቅጣትና አገራችን ዝንተ-አለም ወደብ-አልባ ሆና የኤርትራና የጅቡቲ ጥገኛ ሆና እንድትቀር፣ ሆን ብሎ ሙተው የተቀበሩትን የአፄ ምንሊክ ጊዜ ውሎችን ቆፍሮ አውጥቶ ኢትዮጵያን አይቀጡ ቅጣት የቀጣ ደመኛ የአገራችን ጠላት ነው። እሱ ብቻ ሳይሆን የሱ ተከታዮች ኢትዮጵያዊው ወገናችን ታግሎ እንዲጥላቸው ያስፈልጋል።
5) ስብሃት ነጋ፣ ቴድሮስ ሓጎስ፣ ብርሃነ ገ/ክርስቶስ ወዘተ ኢትዮጵያ በቀል ኤርትራውያን ከራሳቸው አልፈው እንደነ ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሃዬ፣ ወዘተ የመሳሰሉ ታማኝ የኢትዮጵያ ጠላት ሎሌዎችን ለማፍረት ችለዋል።
በአጠቃላይ፣ ያለንበት ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው። በተለይ ደግሞ እንደ ኢሮብ የመሰሉ ሉዓላዊ የኢትዮጵያ መሬቶች ግማሹ ለኤርትራ እንዲሰጥ የኢህአዴግ ም/ቤት ወስኗል። ይህ ውሳኔ በመለስ የተላለፈ፣ ኢትዮጵያን ያዋረደ ውሳኔ ነው። የትግራይ ህዝብ በህይወቱ እያለ ይኸው የጠላት ውሳኔን መቃወም ብቻ ሳይሆን ከመሃሉ የሚገኙትን ባንዳዎቹን ከወገኑ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን ተሰልፎ ታግሎ ማሸነፍ አለበት። “ውድብና” (ድርጅታችን ከአደጋ እንጠበቅ! ጠላቶቻችን ተነስተውብናል!” የትግራይ ህዝብ ተነስ፣ ታግለህ ያገኘኸው ድልህን ሊነጥቁህ ተነስተዋል!” ቅብጥርሶ የሚሉ የማታለያ መል እክቶች አሽቀንጥረህ ጥለህ የምታውቃቸው ጠላቶችን ጎሮሮ ለጎሮሮ በየትኛውም ሜዳ ተናነቃቸው። ያንተ ጠላት ወገንህና እና አለኝታህ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ሳይሆን ባንተ ስም የሚነግዱት እነ ስብሃት ነጋ፣ ስዩም መስፍን፣ አባይ ጸሃየ የመሳሰሉ ሲገድሉህ የኖሩት ጠላቶችህ ናቸው። ትግራይ ማንም የህወሃት ደጋፊ ያንተውና የናት አገርህ የኢትዮጵያ ጠላት አርገህ ቁጠረው። ገድለውሃል፣ ግን አልሞት አልካቸው። እስኪጨርሱህ አትጠብቅ!
የተላለፈው ውሳኔ የዓጋመና የኢሮብ ህዝብ ብቻ መቃውም የለበትም። ድፍን የትግራይ ህዝብ ከባንዳው የወያኔ ድርጅት ሶላቶች ጋር ጉሮሮ ለጎሮሮ ተናንቆ ማሸነፍ አለበት። ይህ ሳይሆን ከቀረ፣ ከ ማእከላዊው መንግስት እየተባረረ ያለው የባንዳ ቡድን የትግራይን ህዝብ በምርኮኝነት ይዞ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ያጣውን ስልጣን በ ኃይል ለማስመለስ ደም ከማፈሰስና አገር ከማፈራረስ ወደ ኋላ አይልም።
ለዚህም “ህወሃት ስልጣን ካጣ ኢትዮጵያ ትበታተናለች” ያለው ባንዳው ስብሃት ነጋ ማስታወስ በቂ ነው። ከእንግዲህ በኋላ የትግራይ ህዝብ ማንቀላፋቱ፣ መሞኘቱ፣ የኛ ናቸው እያልክ ሲገድልህ የኖረውን ፈራ-ተባ እያሉ ማየት ፈጽሞ መቅረት አለበት። የትግራይ ህዝብ ስትነሳ ደግሞ የተቀረው ኢትዮጵያዊው ወገንህ ከጎንህ ቆሞ በአንተ ስም ሲገድልህ የኖረውን ጠላት እስከ ወዲያኛው እንደሚፋለመው ሳይታለም የተፈታ ነው።
ወገኔ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ – አንተም ብትሆን ከ40 አመት በላይ በጠላት የተቀጠቀጠውን የትግራይ ህዝብ በወያኔ ፕሮፓጋንዳ ተታለህ የሩቅ ተመልካች እንዳትሆንበት! በተቻለህ መጠን ከጠላት ጋር በሚያደርገው ፊልሚያ ከጎኑ እንደምትቆም በቻልከው መንገድ ግለጽለት። የኋላ ኋላ ድሉ የጋራ ይሆናል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
ሞት ስልጣን ላይ ላሉ የኢትዮጵያ ጠላቶች!!!
Filed in: Amharic