>

"...ጌታቸው እና ሳሞራን ገለል ማድረግ ለህዝቡ አእምሮ ውስጥ የሚቀመጥ ትልቅ ሀውልት ነው!!!" (ኤርሚያስ ለገሰ)

(አርትኦት አለማየሁ ማ/ወርቅ)
… በተለይ የደህንነት ሀላፊው እና ኤታማዦር ሹሙ መነሳትን በራሱ እንደ ትልቅ ታሪክ ነው የምንቆጥረው። በግለሰብ ደረጃም፣ በአገር ደረጃም ፣ በውስጣዊ ድርጅት አኳያም ታሪካዊ ተደርጎ ሊወሰድ ይገባል ብዬ ነው የማስበው።
በግለሰብ ደረጃ ስልጣንን እንደ ርስት የመቁጠር ዝንባሌዎች  እንደማይሰሩ የታየበት ነው።
እስከ ዛሬ ድረስ የደህንንት ፅ/ቤት ስንል ከጥበቃው ጀምሮ የትግራይ ተወላጅ ህወሀትን ነው የምናስበው። ግለሰቦቹ እንደ ርስት ነው ስልጣንን ይዘውት የነበረው። በመሆኑም የእነዚህ ሰዎች መነሳት ስልጣንን በርስትነት ይዞ የመዝለቁ ሁኔታ ያበቃለት መሆኑን አመላካች ነው።
የማንሳቱና የማሰናበቱ ሂደት ግለሰቦቹ የፈጸሙትን ወንጀል በእጅ አዙር መንገር አድርጌ ነው የምወስደው። በሌላ አነጋገር እንደ ሀውልት ነው የማየው። እንደ አንድ ጭንቅላት ውስጥ እንደሚቀመጥ ሀውልት።
– ጌታቸው እና ሳሞራ የዘረኝነት ምልክቶች ናቸው
– ጌታቸው እና ሳሞራ የኢ-ፍትሀዊነት ምልክቶች ናቸው
– ጌታቸው እና ሳሞራ የዘር ማጥፋት ምልክቶች ናቸው
– ጌታቸው እና ሳሞራ የተደራጀ ሌብነት እና ዝርፊያ ምልክቶች ናቸው
– ጌታቸው እና ሳሞራ የበታችነት ስሜት የወለደው የአምባ ገነንነት ምልክቶች ናቸው
– ጌታቸው እና ሳሞራ ስልጣንን እንደ ርስት የመያዝ ምልክቶች ናቸው ሌላም ሌላም…
እነዚህ ሰዎች ፓርቲ እና መንግስት – ፓርቲ እና ህዝብ ሳይነጣጠሉ እንዲታዩ ለማድረግ አደገኛ ፖለቲካ ሲጫወቱ የነበሩ ሰዎች ናቸው።
ሳሞራ እንደምናስታውሰው “… የትግራይ ህዝብ ማለት ህወሀት ነው፣ ሕወህት ማለት የትግራይ ህዝብ ነው…” ያለ ለእልቂት የሚጋብዙ ፍጹም አደገኛና መርዘኛ ቃላትን ይጠቀም የነበረ የአደገኛ ነገሮች ምልክት ነው።
 ጌታቸው እና ሳሞራ የጸረ አማራ ምልክቶች ናቸው…
ሳሞራ አንድ ወቅት ባንክ ስብሰባ ላይ ተገኝቶ “…የቀበርነው አማራ እና ኦርቶዶክስ ሲያንሰራራ ቆመን ማየት አንችልም …” በማለት በአደባባይ የተናገረ ሰው ነው።
– ጌታቸው እና ሳሞራ የመሀይምነት ምልክቶች ናቸው… አንድ ወቅት ጌታቸው ከያማማቶ ጋር ሲወያዩ በሚስጥራዊ ኬብል በተላከ መልእክት “….እናንተ እንዲህ የማታደርጉልን ከሆነ የአሜሪካንን ተቃዋሚዎች ስልጠናን ጨምሮ በብዙ ነገሮች ረድተን እናዘምትባችኋለን…” ያለ አሳፋሪ ሰው ነው።
ስለዚህ የዘረኝነት፣ የዘር ማጥፋት፣ የተደራጀ ሌብነት እና ዝርፊያ፣ የበታችነት ስሜት፣  የመሀይምነት፣ ስልጣንን እንደ ርስት የመውሰድ ምልክቶችን ገለል ማድረግ ለእኔ ልክ እንደ አእምሮ ውስጥ የሚቀመጥ ሀውልት አድርጌ ነው የማስበው።
Filed in: Amharic