>

ከ200 በላይህፃናትና ሴቶች  ጭካኔ የተሞላበት ግድያ ተፈጸመባቸው 500 ሺህ በላይ ተፈናቀሉ!??! (ታደለ አሰፋ)

በኦሮሞ ክልል የታጠቁ ሀይሎች የተሳተፉበት ግድያ እና ማፈናቀል ነው ሲሉ የጌዴኦ ብሔረሰብ  አባላት ተናግረዋል ። ተፈናቃዮቹ ታዲያስ የማንነት ጥያቄ በማንሳታችን ብቻ ለዚህ አደጋ ተጋለጥን ሲሉም ተደምጠዋል ።
የሚደንቀው የለማ መገርሣ ኦህዴድ ከአብዲ ኤሌ ያልተናነ ማፈናቀል ና ግድያ ሲፈፀም የጋዜጠኞች ዝምታ ነው።
በጉጂና ጌዴኦ አጎራባች ቦታዎች አስደንጋጭና ጭካኔ በተሞላበት አሰቃቂ ሁኔታ  ከ200 በላይህፃናትና ሴቶችን ላይ ግድያ ተፈጸሟል፤  ከ500 ሺበላይ ሰዎችም ለመፈናቀላቸው ምክንያት እንደሆነ ቪኦኤ  በሰኔ 4 ቀን የአማርኛ  ዘገባው አስደምጧል ።
የኦሮሞን መፈናቀል ከሱማሌና ኦሮሞ አጎራባች የዐመቱ መጀመሪያ ላይ በዜና አውታሮች ሠፊ የሚድያ ሽፋን ተሰጥቶታል። ታዲያ የዛሬ ሳምንት በስለት በአሠቃቂ ሁኔታ ለተገደሉት ህፃናትና እናቶች ከ ግማሽ ሚሊዮን ያላነሱ ዜጎች (የአማራው ብሔረሰብ) ተፈናቅለው በረሀብና ዝናብ ጫካ ላይ የተጣሉትን ህዝቦችስ ማን ነው እየደረሰባቸው ያለውን የጭካኔ ግድያ መፈናቀል የሚዘግበው? ወይስ ይህን ፋሽስታዊ ተግባር እንዳይጋለጥ ሽፋን እየሰጠ ያለ ስውር እጅ አለ??
ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ የሚመሩት ኦህዴድ በባድሜ እንደተጠየቀው በማፈናቀሉም  ሂደት ሊጠየቅ ይገባዋል።
የዘፈን ዳር ዳሩ… እንደሚባለው ኢህአዴግ በዐቢይ መሪነት በመቀነስ  እየተደመረ የክልሎች ጦር አበጋዞች በየክልሎቹ ዘር ፅዳት እየተባባሰ እንደሚሄድ ነው የሚያሳየው። ኢህአዴግም በመፍረስ ላይ ነው።
ትግራይ ህዝብ በሰልፍ የዐቢይን ኢህአዴግ በድንበር ማካለል መቃወምም መዘዙ ከፍተኛ ነው።
በሌላ በኩል በኦሮሚያ ና ሌሎች ክልሎች ማፈናቀል ግድያ መባባስ ኢትዮጵያችን የደቡብ ሱዳን ዐይነት የጎሳ ጦርነት ውስጥ  እየገባች  ለመሆኑ ፍንጭ ነው።
ምናልባት ዐቢይ የኢህአዴግ ኮፍያቸውን አውልቆ ብሔር  የለሹን ሠራዊት በኮሎኔልነት በመምራት ኢትዮጵያን ከጎሳ ዕልቂት  ለማዳን ያገኙትን የህዝብ ድጋፍ  ይጠቀሙት ይሆን
 ??? የምናየው ይሆናል!!
በሌላ ዜና :- 

አማራዎችን ከኦሮሚያ ክልል ያፈናቀሉ ባለስልጣናት መባረራቸውን ኦ.ሚ.ኔ ዘግቧል

በኦሮሚያ ክልል የአማራ ተወላጆች እንዲፈናቀሉ ለማድረግ ሲሞክር አንድ የተደራጀ ቡድን በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወይም ፕረዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ በኦህዴድ አመታዊ ኮንፈረንስ ላይ አስደናቂ ውሳኔ ማሳለፉን OBN ዘገበ።
በኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችን አፈናቅላችኋል፣ ወይም ለማፈናቀል ሞክራችኋል፣ ጥላቻን ዘርታችኋል፣ ወይም ህዝብ ለህዝብ እንዲጣላ ምክንያት ሆናችኋል የተባሉ የዞን፣ የወረዳ፣ የቀበሌ ና የልዩ ልዩ ቀበሌዎች አመራሮችን አሰናብተዋል፣ የአንዳንዶቹም በህግ እንዲታይ አድርገዋል ብሏል የክልሉ ቴሌቪዥን።
<<..የአማራ ህዝቦች ወንድሞቻችን ናቸው፣ ያለ እነሱ እነሱም ያለኛ..ወይም አንዳችን ያለ አንዳችን መኖር አንችልም..በቅርቡ የመጣውን ለውጥ እንኳን ተመልከቱ፣ የሁሉቱ ክልል ህዝቦች ትግል ነው..አሁን የምታዩት ለውጥ ያመጣው… የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች በአማራ ክልል ያለምንም ችግር እየኖሩ ነው፣ ስለሆነም ወንድሞቻችን በኦሮሚያ ክልል ያለምንም ስጋት ሰርተው እራሳቸውን መለወጥ፣ ሀብት ማከማቸት ይችላሉ፣ አንዳንዶች በኦሮሚያ ና በአማራ ክልል ተወላጆች ላይ አለመተማመንን ለመፍጠር እየተሯሯጡ እንደሆነ በዚህ ሳምንት የታየ ድርጊት መሆኑን አረጋግጫለሁ፣ ስለዚህ የሁለቱ ክልል ህዝቦች ይንን ሴራ መመከት ያስፈልጋል.. >>..ሲሉ ፕረዚዳንት ለማ መገርሳ ተናግረዋል።
በኦሮሚያ ክልል የአማራ ተወላጆች እንዲፈናቀሉ ለማድረግ ሲሞክር የነበረ አንድ የተደራጀ ቡድን በቁጥጥር ስር እንዳዋሉም ተናግረዋል ሲል ነው የዘገበው።
Filed in: Amharic