ኢትዮጵያን 27 አመታት ሙሉ ሲያሰቃያት የኖረው በሽታ እንደ ጉንፋን ቀላል አይደለም። አገሪቱ በህውሃት አማጩ የፖለቲካ ካንሰር ፍዳዋን አይታለች።
ዶ/ር አቢይ አህመድ የተባለ የፖለቲካ ዶክተር አገሪቱን ለማዳን የተቻለውን እየሞከረ ነው።፡ ኢትዮጵያን የያዛት የፖለቲካ በሽታ በህመም ማስታገሻ የሚድን አይደለም። በሽታውን ከስሩ ነቅሎ ለመጣል የተቀናጀ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ፍቱን መድሃኒት ያስፈልጋል።
አሁን አገሪቱን ከለከፋት በሽታ እየታከመች ብትሆንም የህውሃት የአረጄ ጥርስ እየተሸራረፈና እየተነቀለ ፈፅሞ ማኘክ የማይችልበት ሁኔታ ላይ ገና አልደረሰም። በዚህም ምክንያት እዚያም እዚህም ደደቢት በርሃ ላይ ቆብ ደፍቶ የተካነበትን የዘር ግጭት መቀስቀሱ አይቀርም።
የታረደች ዶሮ መሞቷ ላይቀር ስትንደፋደፍ በአካባቢው ያለውን ሰው በደም መበከሏ ደመነፍሳዊ ባህሪይ ነው ። ህውሃትም የመጨረሻውን ትንፋሿን ሰብስባ መውተርተሯ አይቀርም። 27 አመታት የተዘረጋው የጥፋት ኔትወርክ እስኪበጣጠስ በወልይታና በሲዳማ ፣ በጉራጌና በቀቤና ዛሬ እንደሰማነው አይነት ግጭት ሌላም ቦታ ሊከሰት ይችላልና ይሄን አደገኛ ሴራ ለማምከን ሁላችንም እንበርታ። ዶ/ር አቢይንም ፣ህዝቡንም አገሪቱን የምንረዳበት ትንሹ ነገር እርስ በርስ መተባበርና ለግጭት በር አለመክፈት ነው።
ዛሬ #በወልቂጤ ከተማ ዙሪያ የተፈጠረው ግጭትና ሁከት
ስዩም ተሾመ
