>
5:30 pm - Wednesday November 1, 0180

እውነቱ ይህ ነው!  (ውብሸት ሙላት)

‹‹አቶ ለማ መገርሳ ዐምሐራዎችን ያፈናቀሉ የኦህዴድ አመራሮችን አባረሩ›› ብላችሁ ውሸት ስትቀባጥሩ የነበራችሁ ሰዎች ሁሉ … ልታፍሩ ይገባኋል! የፃፈችሁት/የተናገራችሁት ሁሉ ውሸት ነው፡፡ እኛም ‹‹ማስረጃ አቅርቡልን?›› ስንላችሁ … ፀጥ አላችሁ፡፡ ማስረጃ የላችሁማ! ከየት ታመጡታላችሁ?!
.እንግዲያውስ እውነቱን እወቁት … የኦህዴድ የፖለቲካና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ከፍያለው አያና ትናንት ምሽት ‹‹አቶ ለማ መገርሳ ሰዎችን ያፈናቀሉ አመራሮችን ከኃላፊነታቸው እንዳሰናበቱ ተደርጎ በማኅበራዊ ሚዲያ የተወራው ወሬ ውሸት ነው፤ የተፈናቀለ ሰው የለም፤በግለሰቦች መካከል በተፈጠረ ፀብ ምክንያት አካባቢዎቹን ለቀው የወጡ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው›› በማለት ለVOA Amharic ተናግረዋል፡፡
አቶ ከፍያለውም የአቶ አዲሱ አረጋን፣ የአቶ ነብዩ ደብሳ (የቄለም ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ)፣ አቶ ደምሴ ዋጨቦ (የቄለም ወለጋ ዞን የአስተዳደርና ጸጥታ ጉዳዮች ኃላፊ)፣ የአቶ ታመነ ኃይሉ (የሰዲ ጨንቃ ወረዳ አስተዳዳሪ) እና የዶ/ር ነገሪ ሌንጮን ክህደት ደገሙት፡፡
የVOA Amharic ባልደረባ የሆነው ጋዜጠኛ እስክንድር ፍሬው አቶ ከፍያለው አያናን አነጋግሮ የሰራው ዘገባ ማስፈንጠሪያ (Link) ከዚህ ጽሑፍ ጋር ተያይዟል፡፡
Filed in: Amharic