>
5:13 pm - Tuesday April 19, 2585

አንዳርጋቸው በቢቢሲ ሃርድ ቶክ (መስቀሉ አየለ)

 
“ትግሉ ላይ ጨለምተኛ ለሆናችሁና አጋጣሚውን በመጠቀም አንዳርጋቸው ጽጌ የተኮስነው ቀለሃ የለም አለ ብላችሁ ወደ ተዊተር ለሮጣችሁ ሁሉ ትንሽ ግምት ውስጥ ብታስገቡ ለትንተናችሁ እንዲረዳ ጥቂት ነገር ላካፍላችሁ።
 
፩ አንዳርጋቸው ጽጌ አለም ከሁለት አስርተ አመታት በላይ በእንግሊዝ ውስጥ ሲኖር የእንግሊዝ ፓስፖርት እንዳልወሰደ፤ ነገር ግን የነ ዶር ብርሃኑ ነጋን እና የቅንጅት አመራሮች በመሉ እስር ቤት መግባት ተከትሎ  ከኖርዌይ እስከ ደቡብ አፍሪካ፣ ከካሊፎርኒያ እስከ ሲድኒ አውስ ትራሊያ  ድረስ ዞሮ ትግሉን ለማነቃነቅና ክፍተቱን ለመጓዝ በገጠመው የቪዛ ችግር የተነሳ ከበርካታ ኢትዮጵያውያን በተደረገበት ተጽእኖ የእንግሊዝ ፓስፖርት ለመውስድ እንደተገደደ፤
 
፪ ግንቦት ሰባት ሲመሰረት ግን ግንባሩን ወደ መሳሪያ ትግል እንዲያመራ ወሳኙን ሚና የተጫወተ ብቻ ሳይሆን ወጣኒያኑን በአይዲዮሎጅ በመቅረጽ ዋናው ሰው እርሱ መሆኑን፤ ነገር ግን የመን ላይ ታፍኖ ከመወሰዱ በፊት ወደ እንግሊዝ በወጣና በገባ ቁጥር የእንግሊዝ መንግስት አውሮፕላን ጣቢያ ውስጥ የተለየ የሴኪዩሪቲ ጥያቄ ማብዛት ጀምሮ የነበረ መሆኑን እና አንድ የእግሊዝ ፓስፖርት ለወሰደ ሰው የእንግሊዝ መንግስት አሸባሪ ብሎ ጦርነት ያላወጀበትን የአንድ መንግስት  መሳሪያ አንስቶ ለመገልበጥ መሞከር በህጋቸው ወንጀል መሆኑን ወዘተ ለሚያውቅ ሰው አንዳርጋቸው በቢቢሲ ሃርድ ቶክ ላይ ሲቀርብ ምን ማለት እንደነበረበት አይጠፋውም።ወደ ፊትም ፓስፖርቱን መልሶ ኑሮውን በኤርትራ በረሃ ካላደረገ በቀር  በዚህ ሚዲያ ፊት ከዚሁኑ የተለየ ነገር መናገር እንደፖለቲከኛ እንደማያስኬደው ልብ ይሏል። የዜና ተቋሙ አንዱና እንደማጥመጃ የሚያገለግል የምእራቡ ኢስታብሊሽመንት መሆኑን ይታወቃል።” 

አቶ አንዳርጋቸው ከቢቢሲ ሃርድ ቶክ ጋር ያደረጉትን ለማድመጥ (ለመመልከት) ማጣቀሻውን ይጫኑ 

Andargachew Tsige Interview on BBC Hardtalk

Filed in: Amharic