>
5:33 pm - Thursday December 5, 4154

ጀግናው ታጋይ አበበ ካሴ ይናገራል፥ (ጥሩነህ ይርጋ)

ጀግናው ታጋይ አበበ ካሴ ይናገራል፥
በማዕከላዊ የደረሰበትን ግፍና ኢ- ሰብአዊ ድርጊት ከአንደበቱ እንስማ!??! (ኦድዮ)
ጥሩነህ ይርጋ
አንዳንድ ሰዎች ልጁ የሚናገረውን ሰምታችሁ ለምን አዎጣው ልትሉ ትችላላችሁ፥
እሄ ሰው አበበ ላለፉት ዓመታት ቢታሰርም በብዙ መከራ እያሳለፉት፥ አንድም ቀን ተሸንፎላቸው አያውቅም፥ ጭስና ጀግና መውጫ አያጣም እንቢ እንዳለ ነው በአሸናፊነት የወጣ፥
– የአንድ ብሔር ሰዎች ከማእከላዊ እስከ ማረሚያ ቤት ተደራጅተው ነው የሚያጠቁኝ የነበረው።
– ትልቁ እና ሁሌም በቁጭት እና በእልህ የሚያነሱት ጉዳይ “እየረገጥነው እየገደልነው ያለውን የአማራ ህዝብ እናንተ ናችሁ ያነቃችሁት ለዚህም ዋጋ ትከፍላላችሁ….” በተደጋጋሚ የሚሉት ነው
ጥፍሬን ነቃቅለዋል ብልቴ ላይ አሰቃቂ ጉዳት አድርሰዋል…..
– ከነሱ ባልተናነሰ ይህን ሁሉ በደል አማራው ላይ እያደረሱ ያሉትን ለሆዳቸው ያደሩ ሰዎችን እናውቃቸዋለን …..
– የፍርድ ቤቱን ዳኛ “በእናንተ ዳኝነት ፍትህ ይገኛል ብየ ስለማላምን አልቀርብም” እንዳለ የዘርዓይን ዓይን ሳያይ የወጣ ጀግና መሆኑንም ሰምቻለሁ።
ለመሆኑ የተበደለ ሰው እንዲህ ሆንኩ ብሎ ለመናገር ካልደፈረ እንዴት ነው የሚታገለው?

ጀግናው ቆፍጣናው ወንድሜ አበበ ካሴ እንኳን እግዚአብሔር አስፈታህ!!!

አምሳሉ ገ ኪዳን
አበበ ካሴ ማለት የሰው ልጅ ምን ያህል አካላዊና ሥነልቡናዊን ጥቃትንና ሰቆቃን መቋቋም እንደሚችል ማሳያ ማለት ነው፡፡ እስከማውቀው ድረስ በጭራቁ ወያኔ አረመኔያዊ ጥቃት ከተፈጸመባቸውና በሕይዎት ከተረፉት ወገኖች የአበበን ያህል አረመኔያዊ ሰቆቃ (ቶርቸር) የተፈጸመበት ሰው የለም፡፡ ወያኔ በአበበ ላይ ያልፈጸመው የሰቆቃ (የቶርቸር) ዓይነት የለም፡፡
ቅሊንጦ ታስሬ እያለሁ ከአበበ ጋር አንድ ክፍል ውስጥ ነበርን፡፡ ከዓመታት በፊት ከእስር እንደተፈታሁ ይሄንን የአበበን ታሪክ “የቅሊንጦ አንበሶች!” በሚል ርእስ መጻፌ እና የአበበን ማንነት ማስተዋወቄ ይታወሳል፡፡
አበበ በተፈጸመበት አረመኔያዊ ሰቆቃ ምክንያት ለበርካታ ቋሚ አካላዊ ጉዳቶች ተዳርጓል፡፡ ግማሽ አካሉ በድን ሆኖበታል፡፡ ዘር መተካት አይችልም፡፡ አይችልም ብቻ ሳይሆን አባለዘሩ ለከፍተኛ ኢንፌክሽን (ምርቀዛ) ተዳርጎ አሁንም ድረስ በከፍተኛ ሕመም እየተሰቃየ ያለ ሰው ነው፡፡
ኢትዮጵያውያን ሆይ! እባካቹህ በቻላችሁት መጠን ሁሉ አበበን እርዱት???
Filed in: Amharic