>

"...ከገደሉኝም ትግሌን አደራ በተለይ የኔ ትውልድ አደራ! አገራችን የወያኔ ዘረኞች ብቻ መፈንጫ መሆን የለባትም!" (ሳሙኤል አወቀ)

ታደለ ጥበቡ
“ከማርቆስ እንደመጣ ደወለልኝ።ባህርዳር ሜላት ካፌ ተገናኘንና አወራን።ያኔ ከብሔራዊ ደኅንነት አዲስ አበባ ሳሙኤል አወቀ  እንዲገደል ትእዛዝ የተቀበለው የባህርዳር ቅርንጫፍ የደህንነት ሰዎች ደረጀ አላምረው የተባለ የማርቆስ ልጅና የባህርዳር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች የመረጃ ሀላፊ እና የዩንቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ባይሌ የግል ሾፌር ቴዎድሮስ አለኹኝ ተከታትለውት በተሳፈረበት መኪና አብረው ነው የመጡት።ሳሙኤል አወቀ እጅግ ሲበዛ ደፋር ነው።ድፍረቱ አስገድሎታል”ይላሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉት የሰመጉ ባህርዳር ቅርንጫፍ አባል የሆነ ሰው።
የሰመጉ አባል የሆነው ሰው  ይቀጥላል”ያኔ ሳሙኤል አወቀ ክፉኛ ተደብድቦ ነበር።ወደኛ ሪፖርት ለማድረግ በተደጋጋሚ ይመጣ ነበር።ሁልጊዜም ለደህንነቱ ሲባል አልጋ የሚዝለት እኔ ነበርሁ።አልጋው ዘወር ያለ ቦታ ነው። ያኔ ከማርቆስ እንደመጣ አልጋ እንደያዝሁለትና ለደህንነቱ ከኔ ጋር እንዲሰነብት ነገርኩት።ሳሙኤል ግን ‘ከገደሉኝም ይግደሉኝ እስከመቸ ፈርቸና ሸሽቸ’አለኝና ተው እያልኩት ወደ ማርቆስ ተመለሰ።ሲመለስ አብረውት መጥተው የነበሩት ደህንነቶች የተሳፈረበትን መኪና ከኋላ በመከታተል እነ ቴዎድሮስ አለኸኝና ደረጀ አላምረው ኮድ 3 እና ታርጋዋ ቁጥሯ አማ- 13572 ፒክ አፕ ጥቁር መኪና ይዘው ወደ ደብረ ማርቆስ አበረውት ሄዱ።
ሳሙኤል እስከ ምሽቱ አንድ ሰአት በሰላም መግባቱንና ደህና  መሆኑን ደውሎልኝ ነበር።ከሁለት ሰአት በኋላ ግን ስልኩ ይጠራል አይነሳም።ይጠራል አይነሳም።በቃ ገድለውታል ብዬ ተስፋ ቆረጠሁ።ውነትም ገድለውታል።ደፋሩና ተራማጁ ሳሙኤል ተገድሏል።ማርቆስ አደባባይ ላይ ጭንቅላቱን በጥይት አፍርሰው ገድለውታል።
@ሳሙኤል አወቀ ከሞሞቱ በፊት እንዲህ ብሎ ነበር በfacebook አድራሻው;-
‹‹ውድየደብረማርቆስ ከተማ ኗሪዎች! ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣችሁ ከ25 0000 በላይመራጮች(ኮረጆውን) እርሱት እና በተጨማሪም በ31 ዩኒቨርስቲ የምትገኙ ከ14,000 በላይ ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣችሁ ሌሎች ደጋፊዎች እና የኢሕአዴግ አባላትም።
የማያፍረው ብአዴን / ኢሕአዴግ ድምፅ መቀማቱ ሳያንስ በ21/08/2007 ዓም አፍነውደብድበው ከሞት መትረፌ ቆጭቷቸው እሰር ቤት ለመወርወር ያለመከሰስ መብቴን
እንኳን ተዳፍረው የሀሰት ክሰ እየፈጠሩ ነው! በስልኬ እደተደወለም ያለፍላጎቴደሕንነት እያስገደደኝ ይገኛል፡፡ ተገደልሁም፣ ታሠርሁም፣ ታፈንኩም ነፃነት አይቀርምእና ለማሰረጃነት የደሕንነቶችን ስም፤ ፎቶግራፍ ፤ እና አድራሻ እንዲሁም በሐሠትምሰክርነት እና ከሳሽነት የተደራጁ አካላት እና ዋና ተወካዮች የደብረማርቆስ ከተማ04 ቀበሌ አመራሮች እና ፖሊስ ለታሪክ አሰመዘግባለሁ፡፡ ማንኛውም የምከፍለው ዋጋለሀገሬ እና ለነፃነት ነው፡፡ ከታሠርሁም ሕሊናዬ አይታሰርም ከገደሉኝም ትግሌን አደራበተለይ የኔ ትውልድ አደራ! አገራችን የወያኔ ዘረኞች ብቻ መፈንጫ መሆን የለባትም! ትግላችን የነፃነት ጉዟችን ጎርባጣ መድረሻችን ነፃነት ታሪካችን ዘላለማዊ ነው!››
Filed in: Amharic