>

ያቆሰልነው አውሬ ጭካኔው ጨምሮ የቀን ጅብ ሆኖ መጥቷል እንጠንቀቅ!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

* ታስታውሱ እንደሆነ ባለፈው አመት ጌታቸው ረዳ በሚዲያ ቀርቦ ስለትግራይ የበላይነት ስለሚባለው ወቀሳ ሲያስረዳ ” የትግሬ የበላይነት የሚባለው ነገር አያ ጅቦ መጣልህ እያሉ ህፃን ልጅን እንደሚያስፈራሩት አይነት ተረት ነው።” አለ ።
ይሄን  አባባል ጌታቸው ረዳ ከመናገሩ ወድያውኑ ” እንደት የትግራይን  ህዝብ  በአያ ጅቦ ሌላውን የኢትዮጵያ ህዝብ በህፃን ልጅ ያመሳስላል ” ብለው ዘመቻ ከፍተውበት ነበር ።  🙂
* በጌታቸው ረዳ ጠቋሚነት መሰረት እኛም እስኪረሳ ድረስ  ለብዙ ጊዜ እነዚያን ሰዎች  ” አያ ጅቦ ” እያልን መጥራታችንን አስታውሳለሁኝ።
* የኦሮሚያ ክልል  ፕሬዚደንት የሆኑት ለማ መገርሳም ባለፈው “አደገኛውን ጅብ እንዳቆሰሉት ግን እንዳልሞተና ይሄው የቆሰለ ጅብ ዋሻው ውስጥ ገብቶ ቁስሉን እየላሰ እንደሆነ ተናግረዋል።
* ዛሬ ደሞ ጠቅላይ ሚኒስትር  አቢይ አህመድ  ጅቦቹ ጭካኔያቸውን ጨምረው ከሌሊት ጅብነት ወደ ቀን ጅብነት  እንደተሸጋገሩና ከእነዚህ የቀን ጅቦች ህዝቡ መጠንቀቅ እንዳለበት ጠቃሚ ምክር አቀብለውናል።
ጓዶች አሁን የቀን ጅብ ማን እንደሆነ ግልፅ ነው ። የት እንደሚገኝም እናውቃለን ከእኛ የሚጠበቀው እርስ በራሳችን ከሚያበላሉን ከቀን ጅቦች ራሳችንን መጠበቅ ብቻ ነው።
የጅቦቹ ጉዳይ በጠቅላይ ምኒስትሩ አንደበት
– ….ትንሿ ኢትዮጵያ በምናላት የደቡብ ክልል ግጭቶችን በመቀስቀስ እኛን አባልተው ሊበሉን ለሚፈልጉ የቀን ጅቦች አሳልፎ የሚሰጥ ድርጊት መሆኑን ህብረተሰቡ ማወቅ አለበት …
– እንኳን የክልል የመገንጠል ጥያቄም ቢሆን የሚፈታው በውይይት እንጂ በእልቂት አይደለም…
– በቀጣዩ ሳምንት ሀዋሳ መጥቼ አወያያችኋለሁ…
ቪዲዮውን ለመመልከት ቀጥሎ ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
Filed in: Amharic