>

አብይ እንደዋዛ (ዶ/ር ዘላለም እሸቴ)

ፈጣሪ የሰጣት ለኢትዮጵያ ምድር

ስጦታ አድርጎ ታሪክ የሚቀይር

ለያዘን አባዜ ጥላቻን የሚያሽር

መድሃኒት ተገኘ ስብዕናው ፍቅር

 

እንደ ንጋት ብርሃን ጨለማውን ገፎ፥

ስጋትን አምክኖ ሁሉን በአንድ አቅፎ፤

ራዕዩን ሰንቆ አዋላጅነቱን፥

ደረሰ ያገር ልጅ ሊሆንልን ፍቱን።

 

ሙጥኝ የሚል መዥገር ነው ብሎ መገመት፥

እንዴት ይታሰባል ለስልጣን የሚሞት፥

አባት መሆን ሲችል ለኢትዮጵያ እናት።

 

የዛሬ ሁለት ዓመት ቁርጥ ነው ነገሩ፥

እውነተኛ ምርጫ ሊታይ በሀገሩ።

 

ፈጣሪ የሰጣት ለኢትዮጵያ ምድር፥

ዶ/ር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ምስጢር፤

ኢትዮጵያን አሻግሮ ሕዝብ ንጉስ ሲሆን፥

እኛም በተራችን ስጦታ አድርገን፤

እርሱን እንድንሰጥ ለምስራቅ አፍሪካ፥

የአብይ ስራ ይሁን ጥቁር የሚያፈካ።

ይሄ ሁሉ ጉዞ ፊት እየጠበቀን፥

የቀን ጅቦች መንገድ ቆመው ሲሰልሉን፤

ጣጣ ስናበዛ፥

እንዲሁ እንደዋዛ፤

እያቅማማን ስናመነታ፥

እንዳናስመታ እንዳንመታ።

 

ኢሜል፡ ethioStudy@gmail.com

Filed in: Amharic