>
5:13 pm - Saturday April 18, 7435

"የሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጉራጌና እና ቀቤና ዞንና ወረዳዎች የበላይ አመራሮች በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን እንዲለቁ" (ጠ/ሚ አብይ አህመድ)

“የሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጉራጌና እና ቀቤና ዞንና ወረዳዎች የበላይ አመራሮች በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን እንዲለቁ”

ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ 
ሪፖርተር፡ ጥላሁን ካሳ
በሀዋሳ፣በወላይታና ወልቂጤ  የተፈጠረውን ችግር ተከትሎ የበላይ  አመራሮች ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንዲለቁ ጠየቁ፡፡
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በወልቂጤ  ከህዝብ ጋር እያደረጉት ባለው የምክክር መድረክ ላይ እንዳሉት በደቡብ ክልል ለተከሰተው አሳዛኝ ነገር ሆን ብሎ በቸልተኝነት በመመልከት አልያም በማቀነባበር የክልሉ ባለስልጣናት ተጠያቂ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ግጭቱ የተነሳባቸው የሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጉራጌና እና ቀቤና ዞንና ወረዳዎች የበላይ አመራሮች በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን እንዲለቁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በወልቂጤ ከህዝቡ ጋር ባደረጉት ውይይት ይህን የሥልጣን መልቀቅ ጉዳይ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደሴ ዳልኬ ጋር በነበራቸው ቆይታም መነጋገራቸውን ገልፀዋል፡፡
በኦሮሚያም በነበሩ ግጭቶች  ተጠያቂ የነበሩ አመራሮችን የማንሳት ስራም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልልም ከአማራ ተወላጆች   መፈናቀል ጋር ተያይዞ ተጠያቂ የሚሆኑ አመራሮች  ከኃላፊነት እንደሚነሱና  ተጠያቂም እንደሚሆኑ ገልፀዋል፡፡
Filed in: Amharic