>

ሲዳማዎች ይሄ መጥፎ ኢሜጅ አሻራው በቀላሉ የሚለቅ እንዳይመስላችሁ!!! (ቬሮኒካ መላኩ)

ሲዳማዎች ይሄ መጥፎ ኢሜጅ አሻራው በቀላሉ የሚለቅ እንዳይመስላችሁ!!!

ቬሮኒካ መላኩ
ከቀዝቃዛው ጦርነት መባቻ  በኋላ ፣ከበርሊን ግንብ መደርመስ እና ከሶቬት ጎራ መፈራረስ በኋላ በምስራቅ አውሮፓ  መዋቅራቸው የፈራረሰው  የኬጅቢ እና የምስራቅ ጀርመን የስለላ አባላት የፈፀሙት ወንጀል እጅግ አሰቃቂ እንደነበር ብዙ ተፅፎለታል።
አንድን የቆሰለ የደህንነት ተቋም እስከመጨረሻው ነጥብ ድረስ ተከታትለህ ሊኩይዴት ካላደረከው የሚፈጥረው ጉዳት ቀላል አይደለም።
 ከወደ አዋሳ የተለቀቀው ቪዲዮ እንቅልፍም አያስተኛም እህልም አያስበላም።  እንድሁ አንጎል ውስጥ እየተንከላወሰ እረፍት ይነሳል ።
አንድ የገባኝ ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ  መካነ አራዊት ( Zoo) ውስጥ መታጎር ያለበት ብዙ ሰዎች መኖራቸውን ነው።
ሽፈራው ሽጉጤ የሚባል ያልሰለጠነ አገር በቀለ የሆነ ” ሂምለር ” ገና በጧቱ ጉራፈርዳ ላይ ያን ወንጀል ሲፈፅም ማስወገድ ሲገባችሁ ይሄው አሁን አዋሳ ላይ የተፈፀመውን ሆረር  በቪዲዮ አለም እየተመለከተው ነው።
ሲዳማዎች ይሄ መጥፎ ኢሜጅ አሻራው በቀላሉ የሚለቅ እንዳይመስላችሁ።
ከቤኒሻንጉል ክልልና ከጉሙዝ መማር ነበረባችሁ። በህፃን አበጥር ወርቁ ላይ የተፈፀመው ድርጊት ዜናው  በአለም እንደ ሰደድ እሳት ከመሰራጨቱ የተነሳ
ዛሬ ” ቤኒሻንጉል”  ስትሉት ማንኛውም ፈረንጅ የአባይን ግድብ ሳይሆን የሚያስታውሰው  ” Oh እነዛ የህፃን ልጅ ብልት የሚቆርጡት የድንጋይ ዘመን ሰዎች ያሉበት ቦታ ነው? ”  ይላችኋል።
 ዛሬ ቤኒሻንጉል ብልቱ ላይ ሄልሜት አድርጎ እንኳን የሚሄድ ቱሪስት አታገኙም።።
ሲዳማዎች በእነ ሽፈራው ሽጉጤ ምክንያት በራሳቸው እና በወላይታ ህዝብ ላይ ቀፋፊውን የበርሊን ግንብ ገንብተዋል። ይሄን በህዝቦች መካከል የተገነባ የጥላቻ ግንብ ሊፈርስ የሚችለው እንደ ሽፈራው ሽጉጤ ፣ ሲራጅ ፈጌሳ የመሳሰሉት ክሪሚናልስ   በስቅላት ሲቀጡ  ብቻ ነው።
ኢትዮ ሪፈረንስ:-  ቪዲዮው አሰቃቂ አስቀያሚና ዘግናኝ ስለሆነ   ወደ ሰው ልጆች እንዲዛመትና እንዲሰራጭ ባለመፈለጋ ችን አላወጣነውም። 
Filed in: Amharic