>

ዛሬም ሽብር ፣ ግድያ ፣ ደም ማፍሰስ የህወሀት ልዩ መገለጫ! (አለማየሁ ማ/ወርቅ)

ዛሬም ሽብር ፣ ግድያ ፣ ደም ማፍሰስ የህወሀት ልዩ መገለጫ !!!

አለማየሁ ማ/ወርቅ
ሻእቢያ ፣ ኦነግ ፣ አርበኞች ግንቦት ሰባት…. ሁሉም የጦር መሳሪያ አስቀምጦ የሰላም ዘንባባ ይዟል፤
እንግዲህ የሚቀሩት የቆሰሉት ጅቦች ህወሀቶቹ ናቸው! ዛሬም ካደጉበት ፣ ጥርሳቸውን ከነቀሉበት፣ ከሰለጠኑበት የደም ማፍሰስ አባዜያቸው ውጭ የተሻለ ነገር ማሰብ የማይችሉ የአእምሮ ድኩማኖች የሀገሪቱን እና የህዝቧን ተስፋ ለማጨለም እንደ ምኞታቸው “ኢንትራ ሀምዌይ” በዝህች ቅድስት ሀገር ለማምጣት በየጎሬአቸው ሆነው በተላላኪዎቻቸው ሰይጣናዊ ቅዠታቸውን ለማሳካት እየተጉ ነው!!!
ህወሀቶቹ ይሄ ከደማቸው የተዋሀደው ከአያት አባቶቻቸው የወረሱት ባንዳነት፣ የአገር እና የህዝብ ጥላቻ ነገም ይህን የህዝብ የተስፋ ሻማ ለማጥፋት እንደማይተኙ አመላካች ነውና ዶ/ር አብይ  ለፍቅር፣ ለይቅርታ፣ ለሰላም የተዘረጋ እጅ ብቻ ሳይሆን ከሰብአዊነት ውጭ የሆኑ አውሬዎችን ለመቅጣት የሚያስችል የእሳት ልምጭ እንዳለውም ሊያሳያቸው ይገባል!!!
 ሙከራው ጠ/ምኒስትሩን ለመግደልና ሽብር ለመንዛት ቢሆንም ያ አልተሳካም የኢትዮጵያ አምላክ የት ሄዶ!!
ለጥቂቶች ህልፈተ ህይወት እና መቁሰል መንስኤ ከሆነው የግድያ ሙከራ በኋላ ዶ/ር አብይ ይህን ነበር ያሉት:-

“ፍቅር ፣ ይቅርታ ያሸንፋል፤ መግደል መሸነፍ ነው፣ መግደል መዋረድ ነው!!!

ጠቅላይ ምኒስትር ዶ/አብይ
— ጥላቻን ፣ክፋትን በተባበረ ክንድ ስላሸነፋችሁ እንኳን ደስ አላችሁ። ይህች ቀን ኢትዮጵያውያን ተደምረው በፍቅር፣ በይቅርታ በሰላም ሲተሙ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ፍቅር እንዲዘንብ ያደረጉበት እለት ቢሆንም ይህን የማይፈልጉ አካላት በተጠና በታቀደ መልኩ ፣ ሙያን ታግዘው ይህን ደማቅ ስነስርአት ለማደፍረስ ፣ ለማበላሸት፣
— የሰው ህይወት ለመቅጠፍ፣ ደም ለማፍሰስ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል።
—አጠቃላይ አላማቸው የጨነገፈ፣ የወደቀ፣ የከሰረ ቢሆንም ጥቂት ኢትዮጵያውያን እንዲጎዱ ሆኗል። ህይወታቸውም ያለፈ ጥቂት ሰዎች አሉ።
— በመጀመሪያ ለእዚህ ክቡር አላማ፣ ለኢትዮጵያውያን ፍቅር እና ይቅርታ ሲሉ ህይወታቸውን ላጡ ወንድም እና እህቶቼ ፣ ለቆሰሉ ወገኖቼ ቤተሰብም መጽናናትን እየተመኘሁ የዛሬው መስዋእትነት ለኢትዮጵያውያን ፍቅር እና ሰላም፣ አንድነት የተከፈለ እና ሁሌም የምናስታውሰው ይሆናል።
— ኢትዮጵያውያ ይችን ቀን ያመጣነው በመስዋእትነት ብዙዎችን ገብረን ስለሆነ ዛሬም ዋጋ እየከፈልን እንጠብቀዋለን።
….የሆነው ሆኖ ዛሬም ለኢትዮጵያውያን ወንድሞቼ ላበስር የምፈልገው ፍቅር ያሸንፋል፣ መግደል መሸነፍ ነው፣ መግደል መዋረድ ነው!!! ….።
Filed in: Amharic