የአሜሪካኖች መቀየስና የህወሓቶች ማልቀስ ቀጥሏል!
ስዩም ተሾመ
በተንኮልና በስም ማጥፋት የተካኑትና ጭፍን የህወሓት ደጋፊዎች እና ደቃፊዎችን (ተቃዋሚ መሳይ ደጋፊዎችን) ከፌስቡክ ገፄ ላይ በብሎክ ጠራርጌ ሳስወግድ ከተረፉት ጥቂት ሰዎች ውስጥ
ዳኒኤል ብርሃኔ ከቀድሞዋ የአሜሪካ አምባሳደርና የፖለቲካ አማካሪ ከነበረው ግለሰብ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ነበረው። ነገር ግን፣ የእነ ለማ መገርሳ እና ገዱ አንዳርጋቸው ቡድን የህወሓትን የበላይነት ለማስወገድ መተባበርና መታገል ሲጀምሩ አሜሪካኖች ድጋፋቸውን ከህወሓት ወደ እነሱ ያዞራሉ። በተለይ ደግሞ ህወሓት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በማወጅ የኦህዴድና ብኤዴን አመራሮችን እስር ቤት ለማስገባት የተግባር እቅድ ነድፎ መንቀሳቀስ ሲጀምር አሜሪካኖች በግልፅ መቃወም ጀመሩ። በዚያው ልክ ደግሞ ኦህዴዶችን አቋምና አካሄድ በግልፅ ደግፈው መንቀሳቀስ ጀመሩ። ምክንያቱም ህወሓቶች የራሳቸውን የስልጣን የበላይነትና ዘረፋ ለማስቀጠል ሲሉ ሀገሪቱን ወደ እርስ-በእርስ ጦርነት ሊያስገቧት እንደሆነ አሜሪካኖቹ ተገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ ወደለየለት ግጭትና ጦርነት መግባት የአሜሪካኖችን ጥቅም ይፃረራል። ስለዚህ የህወሓቶች አካሄድ የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የአሜሪካኖችን ጥቅም ይፃረራል። በሌላ በኩል የህወሓትን የበላይነት ለማስወገድ የሚታገለው የእነ ለማና አብይ ቡድን የኢትዮጵያን ጥቅም ከማስከበር አልፎ የአሜሪካኖችን ዘላቂ ጥቅም ያስከብራል። በዚህ መሰረት አሜሪካኖች በግልፅ ኦህዴዶችን በመደገፍ ዶ/ር አብይ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆኖ እንዲመረጥ ቀጥተኛና ግልፅ የሆነ ድጋፍ አድርገዋል።
በአንፃሩ ህወሓቶች የድርጅቱንና የሀገሪቱ ከፍተኛ ስልጣን በኦህዴዶች እጅ እንዳይወድቅ የሞት-ሽረት ትንቅንቅ አድርገዋል። በዚህ ረገድ እንደ ዳንኤል ብርሃኔ ያሉ የህወሓት ደጋፊዎች “የኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር ውስጥ ማንነቱ በማይታወቅ “ህቡዕ” ድርጅት ቁጥጥር ስር ውሏል” በማለት አዲሶቹን የኦህዴድ አመራሮች በአጭሩ ለመቅጨት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተረባርበዋል። የኦህዴድና ብአዴን አመራሮችን ለማሰር የወጣው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውድቅ ሲደረግ አይናቸውን በጨው አጥበው “ፀድቋል” ብለው ተሟግተዋል።
በመጨረሻም የኢህአዴግ ሊቀመንበር ምርጫ ከመካሄዱ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ የኦህዴድ አመራሮችን ለማሰር የእስር ማዘዣ ማውጣታቸው ይታወሳል። የእስር ማዘዣው የወጣ ሰሞን የቀድሞ የደህንነት ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ኦቦ ለማ መገርሳን “እስር ቤት ትገባታለህ!” ብሎ እስከ ማስፈራራት ደርሷል። ይሁን እንጂ፣ ህወሓቶች እስር ቤት ሊያስገቧቸው የነበሩት ኦህዴዶች አሸናፊ ሆነው ወጡ። ዶ/ር አብይም የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ።
በእርግጥ ዶ/ር አብይ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆኖ ከመመረጡ በፊት አሜሪካን ሄዶ ከሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በሚስጥር መገናኘታቸው ይታወሳል። ጠ/ሚኒስትር ከሆኑም በኋላም ከአሜሪኮኖች ጠንካራ ድጋፍ ማግኘቱ ይታወቃል። በዚያው ልክ ደግሞ ህወሓቶች ላይ ፊታቸውን አዙረዋል። ይህ እንዳይሆን ህወሓቶች አቶ ሽፈራው ሽጉጤን የኢህአዴግ ሊቀመንበር ለማድረግ፣ የእነ ለማ መገርሳን ያለመከሰስ መብት በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ በመግፈፍ እስር ቤት ለማስገባት ቆርጠው ተነስተው ነበር።
ይሁን እንጂ፣ ለእስር ቤት የታጩት ቤተ-መንግስት ሲገቡ ላለፉት 27 አመታት ፈላጭ-ቆራጭ የነበሩት አንጋፋ የህወሓት አመራሮች ከቤተ መንግስት ተባረሩ። ህወሓቶች በዚህ መልኩ ተገዝግዘው ከመውደቃቸው በፊት የእስር ማዘዣ የወጡባቸውን የኦህዴድ አመራሮች ለምን አላሰሯቸውም? እንዴት ህወሓቶች ለ27 አመት በተጫወቱበት ሜዳ ላይ እንዲህ ሊሸነፍ ቻለ?
እዚህ’ጋ ብዙ ሰዎች የተለያዩ ምክንያቶች ሊያነሱ ይችላሉ። ነገር ግን፣ ዋና እና ቁልፍ የሆነው ምክንያት የአሜሪካኖች ጣልቃ-ገብነት ይመስለኛል። በዚህ ረገድ የአሜሪካን ኮንግረስ የኤች-አር-128ን መፅደቁ ሊጠቀስ ይችላል። ምክንያቱም በዚህ አዋጅ (ሕግ) ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሚሆኑት የህወሓት ባለስልጣናት መሆናቸው እርግጥ ነው። ይህ አዋጅ ተግባር ላይ ከዋለ ህወሓቶች ሀገሪቱን ከመምራት በተለያዩ የዓለም ሀገራት መንቀሳቀስ፣ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በመዝረፍ በውጪ ሀገራት ባንኮች ያስቀመጡትን ገንዘብ ማንቀሳቀስ አይችሉም። በዚህ መልኩ በስልጣን ላይ መቆየት ሆነ ሀገሪቱን ማስተዳደር አይችሉም። ከዚህ በተጨማሪ የአሜሪካን ደህንነት መስሪያ ቤት (CIA) በህወሓቶች ላይ ከፍተኛ ጫና ሊያደርግ እንደሚችል መገመት ይቻላል።
በአጠቃላይ አሜሪካኖች ህወሓትን አንቅረው ተፍተውታል። ስለዚህ አሜሪካኖች ኢትዮጵያን በተመለከተ ምንም ነገር ቢናገሩና ቢያደርጉ እነ ዳንኤል ብርሃኔን ክፉኛ ያበሳጫል፥ ያነጫንጫል። ባለፈው ዳንኤል ብርሃኔ “ዶ/ር አብይ ከተመረጠ በኋላ ሀገሪቱን በእጅ-አዙር እያስተዳደሩ ያሉት አሜሪካኖች ናቸው” በማለት የሉዓላዊት ጥያቄ ሲያነሳ ነበር። ዛሬ ደግሞ የአሜሪካን ምርመራ ቢሮ (FBI) በመስቀል አደባባይ የደረሰውን የቦንብ ፍንዳታ ለማጣራት አዲስ አበባ መግባቱን አስመልክቶ “